ልጥፎች

ከኦገስት, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሊመራ የሚገባው #ሰብዓዊነት እና #ተፈጥሯዊነት ሊሆን ይገባል።

  የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሊመራ የሚገባው #ሰብዓዊነት እና #ተፈጥሯዊነት ሊሆን ይገባል።   "ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው፤ እቀኛለሁ፤ በክብሬም እዘምራለሁኝ።" (መዝሙር ፻፯ ቁጥር ፩።)   ትናንት የአማራ ፖለቲከኞች እስር እና የፍትህ ውሳኔ ሃሳቡን ሙሉውን፤ የእኔ ሃሳብ ሳይታከልበት ከBBC ያገኜሁትን መረጃ ሼር አድርጌ ነበር። #ሳስበው ነው ያደርኩት።    የተጠየቀውን ቅድመ ሁኔታ ያልተቀበሉ ፖለቲከኞችን ሊስቱን ትናንት አላገኜሁም ነበር። አሁን ከአቶ ዳንኤል በቀለ ፔጅ የተገኜ። አመሰግናቸዋለሁኝ።   #ምዕራፍ ፲፱።   ጉዳዩን ከህግ አንፃር የመፍትሄ አቅጣጫው ከድንጋጌወች ጋር አዛምደው ቁልፋን የሚፈቱት የህግ #ባለሙያወች ናቸው። ለዚህም ነው ከአስተያዬት የተቆጠብኩት።   በሌላ በኩል ውሳኔው የእኛ ዕይታ ሳይሆን #እንግልት ላይ የሚገኙት የፖለቲካ እስረኞችን ውሳኔ ብቻ ነው ሊጠብቅ የሚገባው። እስረኞች ከጠበቆቻቸው ጋር፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መክረው፤ ጉዳዩን አስበውበት የሚፈጽሙት ቢሆን የተሻለ ነው። ሃሳባቸውን የሚያባትል ዕይታ ከማንኛውም ወገን መቅረቡ ጥሩ አይደለም። ከእኛ ምንም ተጨማሪ #ጫና አያስፈልጋቸውም።    ጠቃሚውን እና ጎጁን መስመር የመወሰን አቅም የባለ ጉዳዮቹ ጉዳይ ነው። እንደ እኔ ያለ ፍትህ ፍለጋ በቋሚነት #መባተል ነው። እስረኞች #እንዳይዘነጉ #አዌርነስ መፍጠር ነው። በመሪው በብልፄው ላይ #ጫና መፍጠር ነው በብዕር እና በብራና አጋዥነት።    የእኔ ንጹህ ፍላጎት የሃሳብ አፍላቂ ሞጋቾችን መመከት እንጂ ህሊናን ማሰር አያስፈልግም ባይ ነኝ። በኢትዮጵያ #አንድም የፖለቲካ #እስረኛ እንዳይኖር ነው እምተጋው። ሙሉ ዕድሜዬ ...

#መቼ ይሆን - #የሰላም #መቼቱ #በጦቢት?

  • #መቼ ይሆን - #የሰላም #መቼቱ #በጦቢት ?   ጦቢት እንዴት አደርሽ?    እንዴትስ አረፈድሽ? መቼ ነው ቀጠሮሽ #የወኽታ ቀንሽ? ናፈቀኝ ማዕልትሽ የሰላም እንብርትሽ።   "ሃሌ ሉያ። እግዚአብሄርን የሚፈራ፥ ትዕዛዙንም እጅግ የሚወድ ሰው ምስጉን ነው።" (መዝሙር ፻፲፩ ቁጥር ፩)   እባክህን አማኑኤል ሆይ! የሰጠህንን #የውስጥህን #ሰላምህን በህሊናችን #ዘርተህ #አብቅል ! አብቅለህም #አስብልልን ። አሜን። ጭንቀትን፤ ስጋትን ከምድራችን አጥፋልን። #መጨካከን አቁርልን። አሜን።   በነጋ ጠባ ጥቁር ዜና፤ በየለቱ መርዶ፤ በየማዕልቱ ዕንባ መፈጠርን ተፃሮ በቆመ ክፋ ሃሳብ የአንድ እትብት ልጆች እንዲህ መሆን ያሳዝናል።   #ንጋት ሆይ! የተስፋ #ወጋገን ሆይ! አቤቱ #የሳቅ - ዘመን ሆይ! መቼ #ትመጣላችሁ ????? ማህበረ ሰብአዊነት እንዴት አደራችሁልኝ።    ሥርጉትሻ 13/08/026. #የሚናፍቅስ #ሰላም #ብቻ ።    https://www.bbc.com/amharic/articles/c4gx835q9gwo «በመተከል ዞን ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ» 12 ነሐሴ 2026 የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ «በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።   ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 6/ 2018 ዓ. ም. ጠዋት 12 ሰዓት ላይ በዞኑ ዋና ከተማ ግልገል በለስ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እና መናኸሪያ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።   ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪ "ሕይ...

#ዘመነ #ሰማዕትነት በየለቱ #በየባዕቱ። #በዚህ መሰል ሂደት መሬትም --- ታዝናለች። አየሩ --- ያዝናል። ተፈጥሮ --- ያዝናል። ዘመንም --- ያለቅሳል። ፈጣሪም ይከፋል።

  #ዘመነ #ሰማዕትነት በየለቱ #በየባዕቱ ።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የምህረት፤ የይቅርታ፤ #የይቅርባይነት ልቦና ፈጣሪ ለሁላችንም ይስጠን። አሜን።    #ምዕራፍ ፲፱።   ሰማዕታት በዘመኑ በርካቶች ናቸው። ጥቂቶችን ብቻ ነው ያቀርብኩኝ። ሁሎችም ምንም #ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት ዬሌላቸው #ባተሌወች ነበሩ።   ሁሎችም እናት አላቸው። ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ይጨንቀኛል። ሴቷ ካረሳሁት ዕጸገነት የምትባል፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ #ሙሽራም የነበረች ነበረች።    ታዳጊ ወጣቱ ወላጆቹን እየሠራ የሚረዳ ነበር። በዚህ ዕድሜው የቤተሰብ #ኃላፊነት የወሰደ ትጉህ ነበር።   እስር ቤት ውስጥም #ሰማዕትነት የተቀበሉ የባንክ ሠራተኛም አሉበት። በአማራ ፖለቲካ ይመስለኛል ታሥረው የነበሩት።   ፈውስ፤ መፍትሄ፤ መዳን፤ ርህርህና፤ ዕውቀት ሁሉም ነገር እንዳልነበረ የሆነበት የሃኪሞች ጉዳይ የኢትዮጵያ የተስፋዋ #ውጋት የሆነ ገጠመኝ ነበር፤ የሁሎችም ሰማዕትነት በአማራ ክልል የተከወነ ነው።    "ህወሃት በፖለቲካ የበላይነት" በሚመራበት የአማራ ክልል ይህን መሰል #ጥቃት የሚጠበቅ ነው።   በሱር ኮንስትራክሽን በማዕከላዊ ጎንደር ለመጀመሪያ ጊዜ 80ሺህ ተፈናቃይ እስከ ስሜን ፓርክ ቃጠሎ ድረስ የተከወኑት አሰቃቂ፤ ሰላም ነሽ ጉዳዮች ባለቤቱን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም #የተቀየጠ ስለሆነ።    ለነገሩ አቤቱ ህወሃት ናፍቀህናል #ና እባክህ #ናልን መባሉን እያዳመጥን ነው።    የሆነ ሆኖ በሁሉም ሂደት የሰው ልጅ እንዲህ በየለቱ ተስፋውን ማጣቱ እጅግ …… እጅግ ያሳዝናል። ዕድሜው እንዲህ መቀጨቱ። ...

አዲስዬ #የእግዚአብሄር እጅ ያለባት ከተማ ናት። አዲስና #ምሩቅ መንፈስም ናት።

ምስል
  አዲስዬ #የእግዚአብሄር እጅ ያለባት ከተማ ናት። አዲስና #ምሩቅ መንፈስም ናት።   "ጎለመስኩ አረጀሁም፤ ፃድቅ ሲጣል፤ ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።" (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር ፳፭።)   https://www.youtube.com/watch?v=Bjs7wTqjs8E «በአዲስአበባ ጉዳይ አስደንጋጭ ጉድ ተሰማ! | የአዲስአበባ እጣፈንታ ተወሰነ? | ወይ አዲስአበባ! አፋጀቻቸው!| Ethiopia»   #ምዕራፍ ፲፱።   ሊንኩን መለጠፌ የተረጋጋ ውይይት ስለሆነ ነው። ቁጣ የለውም። ብስጭት የለውም። ገረጭራጫ መንፈስ የለውም። የእቴጌ #ጣዩቱ ከተማ መነሻዋ፤ ታዳጊነቷ፤ ወጣትነቷ፤ ጎልማሳነቷ፤ አዛውንትነቷን ገለጣው ይተነትናል ውይይቱ።    ለምን እሷን የመሰለ ከተማ መፍጠር አልተቻለም ሲል ትንተናው ይጠይቃል። ከተፈላጊነቷ #ዝቅ የማድረግ ፕሮጀክት ሊኖር እንደሚችል ኢትዮጵያዊው ጉግል አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጠው ነበር። የሸገር ሲቲ እኮ ከዛ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል። አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ ጥንስስም ለዛ ይመስላል። ግን አሁንም ጉምጅቱ ተጧጡፏል።    ግን ኦህዴድ ድሬን፤ ደብረዘይትን፤ ናዝሬትን፤ ጅማን የከፋን፤ ሚዛን ተፈሪንም፤ ኢሊባቡር መቱን፤ ባሌ ጎባን፤ ወለጋ ነቀምትን፤ አርሲ አሰላን፤ ሻሸመኔን ጠቅልሎ ተሰጥቶት ግን የአዲስ አበባ #አቻ ለመፍጠር ምን ተሳነው?።   ስንት ዓመት? ከ30 ዓመት በላይ። ጅማ እማ በሚያሳዝን ሁኔታ እንደ ነበር ሰምቻለሁኝ። ድሬም እንዲሁ። ከእጅ የገቡ የቀድሞ ስንት የክ/ ሃገራት ከተማ ለኦህዴድ ተሰጠው??? ግን ምንም …… በተሠራ ነገር ላይ ብቻ #የእኔን ገነባበት። በዚህ መፈተን ይቻላል።    በሌላ በኩል አይደለም ከአዲ...