የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነትን በቀዝዝቃ ጦርነት እናስረክብ ነው፤ የኮሚሽኑ ልዩ ኮሚቴ ፍላጎት።
የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነትን በቀዝዝቃ ጦርነት እናስረክብ ነው፤ የኮሚሽኑ ልዩ ኮሚቴ ፍላጎት።
"ከንቱ፤ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።"

ጠቅላላ የኢትዮጵያ ተቋማት፤ አህጉራዊ ይሁን ሉላዊ የሥልጣን ቦታወች በገፍ
ለማን እየታደለ እንዳለ ይታወቃል።
ይህም ይሁን ተብሎ ኢትዮጵያዊነት መንበረ - እርካቡን፤ ማዕዱን አስረክቡን "አንገት
የተሰራው አዙሮ ለማየት ነው" ብሂልን ይድጠዋል።
በዚህ ስሌት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር በኦሮምያ አስተዳደር #ሥር ይወድቃል።
ማናቸውም ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ዓለም ዓቀፋዊ ጉባኤወችም በኦሮምያ አስተዳደር ስር
ይወድቃሉ። የተንጠራራ ፍላጎት ነው ያለው።
መግራትም፤ መቆንጠጥም አልተቻለም። ብልፄው እራሱን ፈቅዶ #እየናደ ይገኛል።
ውስጥን በዝምታ ማሸፈት ጠንቁ ለራሱ ነው ለብልፄው አገራዊ ነኝ እያለ ሲደሰኩር
ባጅቶ ዞጋዊ መሆኑን እራሱ እየመሰከረ ነው። ዲስፕሊኑ ሲጣስ ጸጥ ረጭ ብሏል።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት ዲስፕሊኑን መቆጣጠር ከተሳነው አናርኪዝም ይነግሳል። አናርኪዝም
#አንጃ ይፈጥራ። አንጃው ፍርሻ ነው። በኢሠፓ ውስጥ አንጃ ተፈጥሮ ሁለት ዓመት አልቆየም
ኢሠፓ መራራ ስንብት ያደረገው። ወፋ ጥሩ አይደለም።
ኦሮምያ አስተዳደር መንፈሱ ኦነግ #ወረስ ነው። ኦነግ ደግሞ ህልሙም ፍላጎቱም
ከኢትዮጵያ #መነጠል ነው። ይህን ለማስፈጸም ነው "አገራዊ" በሚል የተቋቋመው
ኮሚሽን እያስፈጸመ የሚገኘው።
ዋስትና በአንድ ሉዓላዊ መንግሥት ውስጥ ለሁሉ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ እንጂ ለአንድ
ክልል ሊሸልመው የሚገባ አይደለም። ጉዳዩ ሳናቆላምጠው ኢትዮጵያን #ሽጡልን ነው።
በምንም ዓይነት ታምር የኢትዮጵያ መንበረ * መንግሥት አናት አዲስ አበባ ለማህበረ ኦነግ
በሽልማት ይሁን በስጦታ ገጸ በረከት ሊሆን አይገባም።
ዶክተር አብይ ኢዜማ እና አብን ከእሳቸው ጎን አሰልፈው ሁለቱም ድርጅቶች በሙሉ አቅማቸው ሽፋን
ሲያሰጡ የባጁት ይህን ቀን አልመው ነው። ከምርጫ በኋላ ያለው #የቱማታ ሩጫም ይሄው ነው።
"ከርምጃ ወደ ሩጫ" የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትልማቸው ነው።
#ጠብቁት የአስታራቂነት መዶሻ ይዘው ይመጣሉ።
በማህል ይመጣሉ። አስታራቂ ሆነው ይቀርባሉ። ልዩ ኮሚቲውን፤ የኮሚሽኑን አካላት ሁለቱም
አካላቶቻቸው ናቸው ይሰበስቡ እና "አያ ጅቦ ጅቦ ሳታማህኝ ብላኝን" ይከውናሉ። ያስከውናሉ።
ኖቤል ሲሸለሙ ኦስካር ቢሆን ይሻል ነበር ብዬ ጽፌ ነበር። ምክንያቱም ጥሩ አክተር ስለሆኑ።
ከጥቃቅኑ እስከ ገዘፈው ጉዳይ እሳቸው የማያውቁት፤ ያልወሰኑበት ጉዳይ አይኖርም። እሳቸው
ናቸው ይህን ምስቅልቅል ሁነት እየመሩ የሚገኙት።
የዶክተር አብይ ነፍሳቸው ከምን ጋር እንደ ተጠለፈ እኮ ነገሩን። "ኦሮሞ ኢትዮጵያን ይበልጣል" ብለው።
ጉዳዩን ያመጡበት ያመሳከሩበት ሁነት ትንሽ ውሽክ አድርጎኛል።
ኦሮሞ ብቻ አይደለም ሌላ አገር ውስጥ የሚኖረው። ኩናማ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ይኖራል፤
አፋር ጁቡቲ፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ይኖራሉ።
አሁን አሁን እምሰማው ደግሞ ራሺያ፤ ህንድ፤ ኢራን፤ እስራኤልም ኢትዮጵውያን ይኖራሉ።
እና እኛ ከአገረ እስራኤል፤ እኛ ከአገረ ከህንድ፤ እኛ ከአገረ ራሽያ፤ እኛ ከአገረ ኢራን እንበልጣለን
ልንል አንችልም - ኢትዮጵውያን።
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፍላጎት ከኢትዮጵያ፤ ከኢትዮጵዊነት #በላይ ሆኖ መታዬት ይሻሉ።
ለዚህም ነው ኢትዮጵያን ጎላ ያደረጉ የጥበብ ሥራወችን ዕድገታቸውን ሳያጠናቅቁ እንዲቋረጡ
የሚደረገው። አገር እና ሰው ሊላካኩ፤ ሊመዛዘኑ አይገባም።
ኢትዮጵያዊነት ጭምትርትር፤ ጭምቅምቅ አድርገህ #የምታኮስሰው ማንነት አይደለም። ኢትዮጵያዊነት
የጎላ፤ የደረጄ፤ ሥልጡን፤ ቀደምት፤ አለኝ የሚለው ወዘተረፈ ዕንቁዊ አመክንዮ በመዳፋ ያለ ድንቅ
ገናና ማንነት ነው።
የሆነ ሆኖ ቤቢሲተርነትን የፈቀደው የምክክር ኮሜሽኑ ቀዝቃዛውን ጦርነት ፈቅዶ፤ መወሰን ተስኖት
ትብስብስ፤ ፍትልትል እያለ ይገኛል።
ያ … የወለጋ፤ ያ … የአርባጉጉ፤ ያ … የወትር፤ ያ … የሻሸመኔ፤ ያ … የአርሲ ሰቆቃ በመላ ኢትዮጵውያን
ዘንድ ጭካኔው አዲስ አበባ ላይ #ይሰለጥን፤ ለጭካኔው "ዋስትና" ይሰጥ ዘንድ ነው ድራማው።
ዛሬ የሚሰጠው ዋስትና ሌላ መንግሥት ቢመጣ ይቃጠላል። ወይንም ይሰረዛል። ለነገ ዋስትና
ዛሬ እራስን #ሳይንዱ ያገኙትን ዕድል በጥንቃቄ አክብሮ መያዝ ካልተቻለ አይደለም ዋስትና ነገ
መንበረ መንግሥቱ የአሸናፊው ኃይል ይሆናል። "አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል።" መተውን
ይሆናል አማራጩ።
ቤትህን አፍርሰህ፤ መጠጊያ አልባ ሆነህ፤ ወደ የመጣህበት ተመለስ መገፋትን ሰንቆ፤ ተስፋ ማጣትን
ቋጥር ለሚመለስ ተሳታፊ ዕዳ ከሜዳ ነው።
አዲስ አበባን ያህል የተደራጀች ቅኔ ከተማ ለማህበረ ኦነግ ከማስረከብ በላይ #ክህደት በታሪክ
አልተመዘገበም። አዲስ አበባ ከክልልነት ባለፈ እንደ #ሌሴቶ ልሁንም ብላ ልትጠይቅ ትችላለች።
ማንነት ላላቸው መጠለያ፤ ተስፋ ብቻ ሳትሆን አጽናኝም ከተማ ናት አዲስዬ።
"#ልዩ ጥቅም" የሚባል አለ። ከአገር "ልዩ ጥቅም???"
ከጉልት ገብያ የተሰበሰበ ገንዘብን አቀራምቱኝ መንፈሱ ጤነኛ አይደለም። ነገ ቤንሻንጉል ጉምዝ
የአባይ መነሻ እኔ ነኝ የሚል ኃይል ሊመጣ እንደሚችል በቅጡ ማሰብ፤ በማስተዋል መራመድ ያስፈልጋል።
አዲስ አበባ ፍሳሹ፤ የውሃ አገልግሎቱ ከጎረቤቷ ጋር ያገናኛታል።
የአዲስ አበባ የዘመናት የስልጣኔ ተጠቃሚነት፤ የገብያ ቅርበት እና የህክምና አገልግሎት ማግኜትም
አብሮ ሊታይ ይገባል። እርግጥ ነው የቄሮ ሰማዕትነት፤ የማስተር ፕላኑ እና የገበሬወች ጉዳይ በጥንቃቄ
ሊታይ ይገባል። አዲስ አበባን ለማስፋት በሚደረገው ንቅናቄ ገራገር ገበሬወች ሊጎዱ አይገባም። የሚገባውን
ሊደረግላቸው ይገባ።
በአንድ አገር ልጅነት ይህን መሰል ብልጥነት በውነቱ ከኃጢያቶች የከፋ ገጠመኝ ነው።
ከሁሉም ግን ፍትኃዊነት ኢትዮጵያዊነቱ ለወል መደጋገፍ የሚረዳ መስመር ነው። ይህን ልጫን፤
ይህን ልዋጥ፤ ይህን ልሰልቅጥ፤ ለእኔ ብቻ ይሁን ለዛውም አገር እየመሩ ይሉኝታ ቢስነት ነው።
ሌላው ግን ሞትን ማሰቡ ይበጃል። ዘልግ አድርጋችሁ ሞቱን እሰቡት። ሁሉም ሄጅ ነው። ሁሉም
#ቋሚ ዋስትና ምድር ላይ የለውም። ስንጠራ ለድርድር ኮሚሽን የሚቀርብ ጥያቄ የለም።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
20/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ