ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 27, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ገበሬው የህግ ባለሙያ አቶ ብዙአዬሁ ታዬና የአይዋ ዘመን ፍጥጫ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ያፈዛልም ያደነዝዛልም ። „ አንተ ፈጣሪያችን ግን ቸር ነህ፣ ይቅር ባይ ነህ፤ የምትታገስ ነህ።   ካህሊነትህን እያወቅን ብንበድል ባንበድልም፤ ያንተ ወገኖች ነንና   በቸርነትህ ሁሉን ትሠራለህ። ነገር ግን የ አንተ ወገኖች እንደሆን እናውቃለን። አንተን ማወቅ ፍጹም ክብር ናትና። አንተንም ማወቅ የነፍስ ህይወት ናትና።   መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ  ፲፭ ከ፩ እስከ ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመዝምታ ከሲዊዘርላንድ። ነፃነት! https://www.satenaw.com/amharic/archives/62780                            በመለስ ሞት ስቀሃል ተብሎ ከዳኝነት ስራው ተባሮ ወደ ግብርና የገባው ብዙአዩው  ምን አለ መኖሩን የተቀማ ሳይንቲስት ፈለስፋ ፕሮፌሰር ጸሐፊ ገበሬ? አውሮፕላን አብራሪ ገበሬ? ዛሬ ደግሞ ዜናው የሚነግረን የህግ ባለሙያ ገበሬ? ? ? ምን ላይ ይሆን የቆምነው? የምንቆመውስ? ህም! ስንት ጊዜ እናምጥ? አጥንት እርግዞ መኖር ግን እስከ መቼ? ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? እንደምን አላችሁ? ዛሬ ትናንት የተጀመረ ጹሑፍ ነበረኝ ወደዛ ላመራ አቅጄ ነበር። ነገር እንደ ተለመደው የነፃ ሚዲያ በር የሆነውን ሳተናውን ደህና ማደሩን ብቻ ለማረጋገጥ ስገባ አዲስ ዜና አገኘሁኝ። አዲስ ዜና ከኖረ እሱ ደህንአ ነው ማለት ነው። በ አጋጣሚ ያዝነኩበት ዜና ዛሬን ለዚህ ጉዳይ ማዋልን ወሰንኩኝ።  „የአንዱን ሲሰሙት ያፈዛል የሌላው ያደነዝዛል“  እንደሚሉት ነው የሆነበኝ። ከሰሞናቱ እኒያ የአገር እጬጌ የፍልስፍና ፈላስፋው፤ የአንትሮፖለሎጂስት ሳይንቲስቱ