ሃይማኖት ብሄር የለውም!
የጅጅጋው ጥቃቱ ከብሄርሰብ ጋር መያያዝ አይገባውም። „ድሀና ግፈኛ ተገናኙ እግዚአብሄር የሁለቱንም ዓይን ያበራል።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፲፫። ከሥርጉተ ©ሥላሴ 06.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት አመሻችሁ ዋላችሁ አደራችሁ። የጸና ደስታ የጸና ሃዘን ሁለቱም ሲያሰኛቸው በፈረቃ፤ ሲሻቸውም ደግሞ በአንድነት እዬሰላለቁን አመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ይቀረዋል። ባለፈው ዓመትም ይህን ሰሞን እስከ ፆመ ጽጌ መፍቻ ድረስ መሰሉ ፈተና ገጥሞን ነበር። የዛሬው የታቀደው የቅድስት ተዋህዶ እና የእስልማና ሃይማኖትን ምክንያት ፈልጎ አጋጭቶ አገራዊ ብጥብጥ ለማስነሳት ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ እርቀ ሰላሙ የውስጥ እሳት የሆነበት የመቀሌው መንግሥት አቅዶ የከወነው ነው። ይህን ፍርድ ሰጪው መዳህኒዓለም ነው። ለዚህም ነው እኔ ግንቦት 7 ሆነ ኢሳት አገር ቤት መሄድ አይኖርባቸውም የምለውም ። የአብይን መንፈስ መቀበል መልካም ነገር ነው፤ ይሄው ብራናው አርፏል። ህውከት የለውም። እናግዘው ይህን መንፈስ ከተባለ ሳሄዱ ውጭ እያሉ ብዙ ተግባራትን ሊከውኑ ይችላሉ ግንቦቶች እስከ ሚዲያዎቻቸው ድረስ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቂመኛ ነው። የፈለገ ይቅርታ ቢባል፤ ፍቅር ቢባል ልባችሁን አውልቃችሁ ብትሰጡ አይቀበለውም። ሌላውም እንዲሁ ነው። ይህን በሚኒ መንትዮሽ ጉባኤ አይተነዋል። ስለምን ልባችን ድፍን አድርጎ እንደ ፈጠረን ይጨንቀኛል። ሌላው ይህ እልቂት የአማራ ጥቃት ብቻ አይደለም። ሃይማኖት ዘር እና ጎሳ የለውም። ቅደስት ተዋህዶ የመላው ኢትዮጵውያን ቤት ናት። የሁሉም ዓውደ ምህርት ናት እንጂ አንድን ዞግ ወይንም ብሄር ብቻ እምታሰባስብ አይደለችም። ጥቃቱ የሁሉ...