#ኢሠመኮ የት ነው ያለው? የተቋሙ #ነፍሱ አለን? ለመሆኑ አዲሱ የኢሠመኮ አመራር #ይተንፍሳልን???
#ኢሠመኮ የት ነው ያለው? የተቋሙ #ነፍሱ አለን? ለመሆኑ አዲሱ የኢሠመኮ አመራር #ይተንፍሳልን ??? "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። የሁሉም በሽታ መነሻ የአንጀት ጉዳይ ይመስለኛል። አንጀት ደህና ከሆነ ሌላው አካልም ደህና ይሆናል ብየ አምናለሁኝ። የአንጀት በሽታ ከባድ እና ውስብስብ ነው። የአንጀት በሽታ መለያው ገረጭራጫ የሆነ #ባህሬ #ቢስም ነው። የአንጀት በሽታ #ጠቡ ከምግብ እና ከመጠጥ ጋር ነው። ካልተበላ እና ካልተጠጣ ደግሞ የሰው ልጅ ህይወቱ አይቀጥልም። አንድ የአንጀት በሽተኛ #ይርበዋል ። ሲበላ ደግሞ ስቃዩ ይጨምራል። አንድ የአንጀት በሽተኛ ይጠማዋል #ሲጠጣ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ስቃይ ነው። አንድ የአንጀት በሽተኛ በተሟላ ኑሮ እንኳን እያለ #ያሻውን አይመገብም። ሁልጊዜ ታጥቆ ስንዱ ሆኖ #በጥንቃቄ ነው የሚኖረው። አንድ የአንጀት በሽተኛ ሲጓዝም ከመገብ ይልቅ #እርሃቡን ይመርጣል። ስቃዩ #አሰቃይ ነውና። በዚህ ላይ የሃኪም ክትትል #መከልከል ፤ በተጨማሪም ውስብስቡ የእስር ቤት ህይወት ጋር #የአንጀት ህመም ፈታኝ ገጠመኝ ነው። ስቃዩን የሚያውቅ ያውቀዋል። እስር ቤት ሆኖ የአንጀት በሽተኛ መሆን የቅጣቱ መልክ እና ይዘት እጅግ #የከፋ ይሆናል። አባት ታዲዮስ ታንቱም #የአንጀት በሽተኛ ናቸው። ቆሎ ብቻ ይመገቡ እንደ ነበር ባለፈው ከእስር ሲፈቱ ሲገልጹ ሰምቻለሁኝ። ቢያንስ እስር ቤት ለሚገኙ፤ በእጁ ላይ ባሉ ህሙማን #እርህርህና በአንድ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ ስለምን #እንዲሰደድ ይፈቀድለታል። አንድ ህሙም ስለምን ህክምና #ይነፈጋል ? ለምን? ሰው በአገሩ መንግሥት የህክምና አገልግሎት ሳያገኝ ተጨማሪ...