#ኢሠመኮ የት ነው ያለው? የተቋሙ #ነፍሱ አለን? ለመሆኑ አዲሱ የኢሠመኮ አመራር #ይተንፍሳልን???
የሁሉም በሽታ መነሻ የአንጀት ጉዳይ ይመስለኛል። አንጀት ደህና ከሆነ ሌላው አካልም ደህና ይሆናል ብየ አምናለሁኝ። የአንጀት በሽታ ከባድ እና ውስብስብ ነው። የአንጀት በሽታ መለያው ገረጭራጫ የሆነ #ባህሬ #ቢስም ነው። የአንጀት በሽታ #ጠቡ ከምግብ እና ከመጠጥ ጋር ነው። ካልተበላ እና ካልተጠጣ ደግሞ የሰው ልጅ ህይወቱ አይቀጥልም። አንድ የአንጀት በሽተኛ #ይርበዋል። ሲበላ ደግሞ ስቃዩ ይጨምራል።
አንድ የአንጀት በሽተኛ ይጠማዋል #ሲጠጣ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ስቃይ ነው። አንድ የአንጀት በሽተኛ በተሟላ ኑሮ እንኳን እያለ #ያሻውን አይመገብም። ሁልጊዜ ታጥቆ ስንዱ ሆኖ #በጥንቃቄ ነው የሚኖረው። አንድ የአንጀት በሽተኛ ሲጓዝም ከመገብ ይልቅ #እርሃቡን ይመርጣል። ስቃዩ #አሰቃይ ነውና።
በዚህ ላይ የሃኪም ክትትል #መከልከል፤ በተጨማሪም ውስብስቡ የእስር ቤት ህይወት ጋር #የአንጀት ህመም ፈታኝ ገጠመኝ ነው። ስቃዩን የሚያውቅ ያውቀዋል። እስር ቤት ሆኖ የአንጀት በሽተኛ መሆን የቅጣቱ መልክ እና ይዘት እጅግ #የከፋ ይሆናል።
አባት ታዲዮስ ታንቱም #የአንጀት በሽተኛ ናቸው። ቆሎ ብቻ ይመገቡ እንደ ነበር ባለፈው ከእስር ሲፈቱ ሲገልጹ ሰምቻለሁኝ። ቢያንስ እስር ቤት ለሚገኙ፤ በእጁ ላይ ባሉ ህሙማን #እርህርህና በአንድ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ ስለምን #እንዲሰደድ ይፈቀድለታል። አንድ ህሙም ስለምን ህክምና #ይነፈጋል? ለምን? ሰው በአገሩ መንግሥት የህክምና አገልግሎት ሳያገኝ ተጨማሪ ስቃይ እንዲያገኘው ማድረግ አሰቃቂው የታሪካችን ገጠመኝ ነው።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት ትጉህ ሞጋች ሲገጥመው ሊደሰት እንጂ ሊከፋ ፈጽሞ አይገባም። እርግጥ ነው አቶ ክርስቲያን ታደለ ርትዑ ተሟጋች ነው። አንድ ሞጋች የእኔ ብሎ ያን መንግሥት ስለሚያዳምጠው ነው የሚሞግተው። #በአሉታዊም ይሁን #በአወንታዊ፤ አንድ መንግሥት የሚያደምጠው ሲያገኝ አድማጩን በተለያዬ ስልት #መበቀል የተገባ አይደለም። የአቶ ክርስትያን ታደለ እስር #ህግም #ተጥሶ ነበር የታሠረው።
ህግ አስከባሪው መንግሥት እራሱን #ሲጥስ ህግ አክባሪ፤ ህግ ተቀባይ ትውልድ ለመፍጠር #ጋዳ ይሆንበታል። ልጆች ከሚሰሙት ይልቅ ዕለት ተለት በሚዩት ላይ እምነት ስለሚያሳድሩ። አክሰሱ ላላቸው ልጆች ይህ መስመር እጅግ ጎጂ ነው። አሳሳቢም ነው። ከዚህ ቀደምም አንድ የአማራ ባንክ ሠራተኛ እስር ቤት ውስጥ መታመሙ ሳይሰማ በሥጋ ተለይቶናል።
ይህ ጉዳይ ሥልጣን ላይ ያለው አቤቱ የብልጽግና መንግሥት ሊጸጽተው፤ ድጋሚ ግድፈት ላለመፈጸም ትምህርት ቤቱ በሆነ ነበር። የሟች ቤተሰቦች እኮ የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው። የእነሱ የዜግነት ክብር ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። ሥርዓት አልበኝነት አይደለም ለመንግሥት ለግል ኑሮም የሚናፈቅ ጉድ አይደለምና።
አሁን ደግሞ በአቶ ክርስትያን ታደለ የገጠመው ሁነት ተመሳሳይ ችግር ከፈጠረ ለኢትዮጵያ ታሪክ ፈተና ይሆናል። የታሪክ ጠባሳ ታቅዶ መፈጸም የተገባ አይደለም። አንድ የፖለቲካ እስረኛ ለምን #ህክምና ይከለከላል? ለዛውም የአንጀት በሽታ? በአንጀት በሽታ የሚሰቃይ ህሙም ተደራቢ ስቃይ መጨመር የበዛ ጭካኔ ነው። የአንጀት በሽታ በየሰከንዱ #ኢመርጀንሲ ነው። በጣም ነው የሚያጥድፈው።
ወንድሜ አቶ ክርስቲያን ታደለ እግዚአብሄር አምላክ ምህረቱን ይላክልህ አሜን። የእግዚአብሄር ታምር ይበልጣል። #አይዞህ! የእኔ ድንግል ጥበቃዋ አይለይህ አሜን። ጸበል፤ ዕምነት እስር ቤት ለማስገባት የሚፈቀድ ከሆነ ቤተሰብ ይህንኑ ቢፈጽም ጥሩ ይመስለኛል። ጸሎትም - ያግዛል። በጸሎት መተጋገዙን የፈቀዱ አቅም ያላቸው ንጹኃን የእነሱንም ድርሻ በዘርፋም ቢወጡ መልካም ነው።
እጅግ የሚናፍቀኝ፤ በአጽህኖት እምመኜው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም የፖለቲካ እስረኛ እንዳይኖር ነው። ዘመኔን ሁሉ የበላውም በዚህ መሥመር ያለኝ ተከታታይነት ያለው ትጋቴ ነው። አቤቱ ህወሃት ከመንበሩ ፈቅዶ ከተሰናበተበት በኽረ ጉዳይ አንዱ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ እና እስረኛች ይደርስባቸው የነበረው ስቃይ፤ ዱላ ነበር። ይህ ጉዳይ እንዲህ ተመልሶ ማየት ድካማችን መፍሰሱን ያመለክታል። ለአቤቱ ብልጽግና ቀጣይ የሥልጣን ዘመኑ ምኞትም አንዱ ሳንክ ይኽው የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ይሆናል።
የምህረት ቸር ዜና ምንጊዜም እጠብቃለሁኝ። አዲስ ዓመት ላይ ጠብቄ ነበር። ምህረት፤ ከእራስ ጋር መታረቅ፤ ታጋሽነት፤ የበዛ #ሰፊነት ከነጠፈ ለትውልድ፤ ስለትውልድ ነኝ ብሎ አንድ መንግሥት ደፍሮ ለመናገር ይከብደዋል።
የሆነ ሆኖ ዶር ዳንኤል በቀለ በነበሩ ጊዜ መልካም ሲሰሩ ሳመሰግናቸው ትከፋብኝ ነበር። የአሁኑ ኢሠመኮ እኮ ያረገ ነው የሚመስለው። ዶር ዳንኤል በቀለ ኢሠመኮን ሲመሩ ሙግት ሲያስፈልግም እሞግታቸው ነበር። በሳቸው ጊዜ እስረኞች ኢመርጀንሲ ላይ ሲሆኑ ወይ እሳቸው፤ ወይንም ቲም ይልኩ ነበር። ያን ዕውቅና መስጠቴ እማልጸጸትበትም ነው። የአሁኑ የተቋሙ ጉዳይ ግን የተቆለፈ ነገር ነው። ቢያንስ ለታሳሪ ህሙማን እርህና እንደምን ይፈራል????
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄ ይስጥልኝ።
ቸር ያሰማን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/09/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ