ልጥፎች

ከማርች 17, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የመኖር (የሕይወት) ፍልስፍናዬ በጥቂቱ። 17.03.2021

ምስል
ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ   ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ ሮቡ ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ እንዳልጠግብ፣ እንዳልከዳህም “ ( ምሳሌ 30 ቁጥር 8) • ዕ ፍታ። ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ ፈንገጥ ያሉ ዕይታዎቼ የሚቀርቡበት ነው። የሃሳብ ቀን። • የመኖሬ ፍልስፍና። ፍኖተ ካርታ ልንለው እንችላለን። ህይወቴን እምመራበት በርካታ መርሆዎች አሉኝ። ዝርግነት አልወድም። ዝርግ ሰውም ክፍሌ አይደለም። ልሙጥነትም ተጠግቶኝ አያውቅም። ጠፍጣፋነትንም እጠዬፋለሁኝ። ውራጅ ሰብዕና የለኝም። ራሴን ተውሼም አልኖርኩም። ልብ እንዲገጠምልኝ አልፈቅድም፤ ምን እንዳለኝ፤ ምን እንደምችል፤ ምን እንደሚፈቀደልኝ፤ ምን ደግሞ እንደማይፈቀደልኝ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። በሚገባ። እራሴ ተቋም ነኝ። ዝንቅ ያልሆነ ወጥ አሻረም አለኝ። (1) መ ኖር ነፃነት ሊኖረው ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። (2) ለ ነፃነቱ ደግሞ መታመን። (3) ለ መታመኑ ተፈጥሯዊነት። (4) ለ ተፈጥሯዊነቱ ጥሩ አስተዳዳሪነት። (5)     ለ ጥሩ አስተዳዳሪነቱ ጥሩ አድማጭነት። (6)    ለ ጥሩ አድማጭነት ጥሩ ዕውቅና። (7)    ለ ዕውቅናው ውስጥን ሳይሰስቱ ወይንም ሳይነፍጉ መስጠትን። (8)    መ ስጠትን በተሰጠው ልክ ሚዛኑን አስጠብቆ እራሰን ሳይሸሹ ወይንም ከራስ ጋር ድብብቆሽ ...