ልጥፎች
ከጁን 3, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ድምጽ አልባዋ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ደህና መጡልኝ ድምጽ አልባዋ የኢትዮጵያ እናት ለፖለቲካ አክተሮች የሊኳንዳ ቤት ማዘጋጀት አይታክታትም … ዛሬም። „ብልህ ሰው መጽሐፍን መስማት ይወዳል። የሚጠራጠር በመጽሐፉ የማያምን ሰው ግን በጥልቅ ነፋስ መካከል እንደምትጉላላ መርከብ ይሆናል።“ መጽሐፈ ሲራክ ምእራፍ ፴፮ ቁጥር ፪ የኢትዮጵያ አዬሩ ስትራፓ ያዘው። ጓጐለ። ውዶቼ እንዴት ሰነበታችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? እስቲ ድብርታሙን ዛሬን እንዲህ አብረን እንቃኛው … ስክነት የት ይሆን የሚሸመተው? ውስጥሰ ከእርቃንነት መቼ ይሆን ለእራፊ የሚበቃው? ከቶ በቃን ህውሃት መባልን ትናንት በአኽትዮሽ መንፈስ በወል ማዕዶት የታለፈው ማዕደኝነትንም ጎበኘውን? የትውልዱ የሃሳብ ብክነትስ ማቆሚያ ለመቼ ተቀጠረ? መቼም አዘኔታ የለም ትውልዱን በዬዘመኑ ለቋያ ለመማገድ። ሥልጣኔ የለለን መሆኑን ሳስበው አይሆኑ ሆኖ ነገ ጠቆረብኝ። እንደዚህ ሰሞናት ባዶነት ተሰምቶኝ አያውቅም። እንዳሻኝ እምቀምረው ስፈለግ ግጥሙን፤ ስፈልግ ሀተታውን፤ ስፈልግ ልዩ ሪፖርቱን ስፈልግ ወጉን እንዳሻኝ በብራና ወክ እንዲህ ያላልኩበትን ያህል ሰሞናቱን ግን አልቻልኩም። ድብርት ቤቴ፤ ድብርት በብራናዬ ላይ ተዛናከተባቸው እንዳሻቸው … ክብረቶቼ የቀንበጥ ሚዲያ ታዳሚዎቼ እኔ መጻፍ ሥራ ሆኖብኝ አያውቅም። በህይወቴ ቀላሉ ሥራ መጻፍ ነው። ሰሞናቱን ግን በዬአቅጣጫው ያለውን እብለቱን፤ ፌኩን፤ ንደቱን፤ ቦክሱን፤ ውስጥን ከፍቶ እንዳሻህ መባሉን፤ ቁጥበንት መሸጥ መለወጡን፤ መታቀብ መቀበሩን ሳስተውለው ግን ያ ሁሉ ድካም ለምን ስለምን አስፈለ ገን ይሆን? ብዕሬም ብራናዬም ሱባኤ ላይ ነበሩ … ዛሬ የሙት ሙቴን ተሟግቼ...