ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አደብ ለወዘተረፈ።

ምስል
ወዘተረፈ። „የእግዚአብሄረ ቃል ወደ ሰለሞን መጣ፤ --- እንዲህ ሲል ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት በሥርዓቱ ብትሄድ፤ ፍርዴንም ብታደረግ ትመላለሰብትም ዘንድ ትእዛዜን ሁሉ ብትጠብቅ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ።“ መፅሐፈ ነገሥት ምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፲፩ እስከ ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 31.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        መ ነሻ። „Hiber Radio: የአቻም የለህ ታምሩና የሁንዴ ዱጋሳ ሞቅ ያለ ውይይት ( ክፍል አንድ ) ያድምጡት ያሰራጩት“ http://www.hiberradio.com/?p=5047 መነሻዬ ይህ ነው። በዚህ ቃለ ምልልስ መነሻነት ውስጤ የሚለኝን ነገር ለማለት ነው የፈለግኩት። በክርክሩ ላይ አልታደምም። ነገር ግን በዚህ ውስጥ ያሉ ቁምነገሮችን በማስተዋል ማዬት ይገባናል ብዬ አስባለሁኝ። ክፍል ሁለትን መጠበቅ አላስፈለገኝም። ምክንያቱም ሙግቱ ጠቅላላ ይዘቱን አይደለም እኔ ልሄድበት የፈለግኩት። እኔ አስተያዬት ልሰጥ የምፈልገው የሥር - ነቀል ለውጥ ፍላጎት እና ያለው ተጨባጭ አቅም ስለገረመኝ ብቻ ነው ይህን መጻፍ የፈልግኩት። የምንፈልገው እና አለን የምንለው ነገር ይገረመኛል ሁልጊዜ። የውይይቱ መንፈሱ ኢህአዴግ ራሱን አፍርሶ እንዬው ስለሆነ ያ በመዳፋችን ካለው አቅማችን ጋር ሚዛን ውስጥ ለማስቀመጥ የሚቸግርበት አመክንዮ መኖሩ ብቻ ሳይሆን በመቻቻል እና አፍርሶ በመገንባት ያለውን የራሴን ዕድምታ ለማቅረብ ነው። ይልቅ የአክቲቢስት ሁንዴ ዱጋሳ የጭብጥ መነሻ ለእኔ ስሜት ቅርቤ ሆኖ አገኝቻለሁኝ። አሁን ኦነግ አረካሁም ስላለ ትጥቅ አልፈታም ብሏል፤ ውጤቱን አብረን እምናዬው ይሆናል። 27 ዓመት ሙሉ አንድም የነጻነት ሃይል አን

ቤተሰባዊ መሪነት ፍቅር በፍቅር ከስደተኛ ወገኖቹ ጋር። ተመስገን!

ምስል
ቤተሰባዊ መሪነት። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን የቃናለታል፤“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 30.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።           አሁን ያገኘሁት ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጀርመን ርዕሰ መዲናው በርሊን ላይ የጠበቋቸውን ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸውን በፍቅር ተቀብለዋል። ያው ጠ/ሚር አይመስሉም ልክ አብሮ አደግ ጓደኛ ነው የሚመስሉት። መቼም የጀርመን መንግሥት ሳይገረመው አያቀርም።  ዕድሜ ልክ በመቃወም የኖረ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ዛሬ ከሙሴው ጋር እንዲህ በፍቅር እቅፍቅፍ ብሎ ሲሳም ሲታዩ እጅግ ያስደስታል። አብሶ ሥርጉትሻ ሐሴቷ ዝቀሽ ነው። አላሳፈሩኝም።   ባይበላም ባይጠጣም ጥሩ ነገር ነው እንዲህ ቤተሰባዊ መሆን። አብሶ ስደተኛ ብዙ ነገር አጥቶ ስለሚኖር መቼም ይህ የሰማይ ስጦታ ነው። ተመስገን።  እኔ ከስሜን አሜሪካውም ደመቅ ዓውድ ይልቅ ይህ በለጠብኝ አቀራረቡ እና ውስጣዊ እቅቅፉ ይሄ ላቀብኝ፤ የፈንሳዩንም አይቸዋለሁኝ የበርሊኑ ግን እኔ እንጃ ልክ የአገር ቤት ቤተሰባዊ ጠረን አለው።  ያው ከተደጋጋሚ ሞት እና አፈናም ወጥተው ነው ለ ዓይነ ሥጋ የተበቃው። እንደ ገና የመፈጠርም ያህል ነው። ብዙ የተከደኑ ነገሮች እዮር የሚያውቃቸው አሉና። ብቻ ተመስገን ነው። እስኪ ይጨርስለዎት! የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

ኮ/ ጎሹ ወልዴ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ በምድሯ ሲገኙ ምርቃት ናቸው።

ምስል
ኮ/ ጎሹ ወልዴ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ በምድሯ ሲገኙ እዮራዊ ምርቃት ናቸው። „ጥበብስ በቀደሙ ሰዎች ዘንድ ተመረመረች።“  መጽሐፈ ምሳሌ ፴፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  30.102018 ከጨምቷ ሲዊዘርላንድ። መልካም ነገር ኮ/ጎሹ ወልዴ አገር ቤት ገብተዋል። እንግዲህ በሳቸው ጥልቅ የማስተዋል አቅም የመጠቀም የጠ/ሚር አብይ ለማ ካቪኔ ጉዳይ ይሆናል። እጅግ ለረጅም ጊዜ፤ በተደጋጋሚ ጊዜም እንደምገልጠው ኮነሬሉ የተከደኑ የአገር ሲሳይ መሆናቸውን ነው።   እሳቸው የጠ/ሚር አብይ አማካሪ ከሆኑ ብዙ ነገር እንደሚቃለል ተስፋ አደርጋለሁኝ። የተወጣጠረው መተንፈስ የታሳነው አዬር ንጹህ አዬር ያገኛል። ኮነሬል ጎሹ ወልዴ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ እዮራዊ ምርቃት ናቸውና ።  ምርቃትን መጠቀም ደግሞ የዘመኑ መሪዎች ልባምነት ልብ ብርሃንነት  ይወስነዋል።  አላዛሯ ኢትዮጵያ ከልቡ በሳል የሆነ፤ ልበ ሙሉ፤ ጨዋ ምርቁን የዋጠ፤ አማካሪ ያስፈልጋታል። ለዚህ ደግሞ ኮነሬል ጎሹ ወልዴ አብዝቶ የሰጣቸው የማድረግም፤ የመሆንም፤ የመቻልም፤ የመታገስም ባለሙሉ አቅመኛ ናቸው። እኛዊነትን ማግኘት የሚቻለበት አምክንዮ የውስጣቸው ማህተም ነው። ብሩህ ህሊናቸው እና ቅን አመለካከታቸው በራሱ አንድ ትውልድ ይገነባል። እኒህን የአላዛሯ ኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ኢትዮጵያ በ100 ዓመት ከማታገኛቸው ልዑቃን አንዱ ናቸው። ክውን፤ ሽክፍ፤ ጠፈፍ ያሉ ብርቱ እና ጠንካራ አብነትም መሆን የሚችሉ ደርባባ የፖለቲካ ሊሂቅ ናቸው። በወታደራዊው መስክ ሆነ በሲቢሉ በነበራቸው የተባ የተግባር ቆይታ፤ በስደትም አገር ቢሆን ክውን ያሉ ድምጣቸው ተሰምቶ የማይታወቅ የአገር ባለውለታ እና ተምሳሌት ናቸው። ስለሆነም እሳቸው የለውጡ አካልነታቸውን ከተበሰረ መዋለ ዕድሜ

ኦነጋውያን ማቆላመጡን ማብቃት ይገባል።

ምስል
ግርዝዝ። „ይህ ትዕቢት ምን ጠቀመን፤ ከትዕቢት ጋር ያለ የኦሪትስ ባለጠግነት ምን አመጣልን።“ መጽሐፈ ጥበብ ፭ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ  29.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በጠ/ሚር አብይ አህመድ የ100 ቀናት ክንውኖች ውስጥ ተካቶ ከነበረው የጉብኝት ቀጠና ወስጥ አንዱ ደንቢ ዶሎ ነበር ። ደንቢ ዶሎ ላይ የነበረው ህዝባዊ ስብሰባ የኩርፊያ፤ የቁጣ የውጡል ነበር ። ለምን መጣችሁብን ዓይነት ነበር። የሚገርመው እና የሚደንቅው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ ኢህአዴግ የሚያስጨፈረውም ከዛ ሰፈር ትውር አላለም ነበር። በቦታው የተገኙት ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ነበሩ። ታዳሚዎች ግን ውስጣቸው ቅጥል እያለ ነበር ንግግሩን የተከታተሉት። ያቀረቡት ጥያቄ ሁሉ ወልደ ግራ ነበር። ፊታቸውን እንደ ኮሶ ኮስኩሰው ነበር አንግዶችን የተቀበሏቸው ። ፊታቸውን እንደኮሰኮሱም ነበር የሸኟቸው።  እና እኔ እህታችሁ ከልብ ስለሆነ ሁሉንም ነገር የእኔ ብዬ የምከታተለው  ደንቢሻ የምትፈልገው የደንቢን ንጉሥ ብቻ ነው። እዛ ሰፈር ዶር  መርራም አቶ ጃዋርም ቦታ የላቸውም ብዬ በተከታታይ ስቸከችክ ባጀሁኝ። ይህም ብቻ ሳይሆን ግንባር ስለሚባለው ፍልስፍናም የጠብታ ያህል የሚያውቁት ስለሌለ እባካችሁ እዛ አካባቢ ትንሽ የሚላስ የሚቀመስ የህሊና ተግባር ፈጽሙ ብዬ ኦህዴዶችን ተማጸንኩኝ። እርግጥ ነው የለማ ቡድን ሥራ በዝቶበታል። በዛ ላይ ልብ ለልብ የመሆንም አዳጋ አለበት። በተጨማሪም ጥድፊያ ላይም ነው የልቡን ለማድርስ ባገኘው የሥልጣን የበላይነት አጋጣሚ ለማስፈጸም። በዚህ 6 ወር ውሰጥ የሦስት አራት አመት ክንውኖችን ከውኗል። በሌላ በኩል ለውጡ ገና ሳይጠናም ነበር ዶር መርራ ጉዲና እና አቶ በቀለ ገርባ አ

ሥርዓት አልበኝነት ክብር ሳይሆን ውርዴትም ውርዴም ነው።

ምስል
ጨካኝነት ወደ እንሰሳነት የመቀዬር ዋዜማ ነው። „ከቀና ህግ ወጥተን ሳትነ የክርስቶስ ብርሃን ረድኤቱ አልተገለጠልንም፤ ክርስቶስም ለኛ አልተወለደልንም።“ መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።   መቅድም።  በምንም ሁኔታ ጭካኔ ዓይን ሊሰጠው አይገባም። በምንም መስፈረት አረመኔነትን ዝም ልንለው አይገባም። ወንጀልን ወንጀል ስለመሆኑ ልናወግዘው እንጂ ልንከባከበው ወይንም ግርዶሽ ልንሰራበት አይገባም።  ሰባዊነት ነው ሰውን 'ሰው' የሚአሰኘው። የሚያደርገውም። ርህርህና ነው ሰው የሚያሰኘው። አዘኔታ ነው ሰው የሚያሰኛው። የሰው ልጅ ከርህርህና፤  ከአዘኔታ ወጥቶ ጭካኔ መሪው ካደረገ ያ ሰው ወደ እንሰሳነት ተለወጧል ማለት ነው።  ከአዕምሮውም የጎደለ ነገር አለ ማለት ነው። እንደ ሰው ማሰብ ከልተቻለ ወደ እንሰሳነት የመለወጥ መለያነት ነው።  ሰው መሆን ማለት እኮ ከእንሰሳ ዓለም መለዬት ማለት ነው። በሌላ በኩል እናት የምትባል ልዩ ፍጥረት አለች። ሁልጊዜ እናት ልጇ ጎልማሳ ሆነ አዛውንት ልጇ ለእሷ ሁልጊዜ እምታዬው ልክ እንደ ህጻን ነው። እናት አብሶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናት ባላባራ የዘመናት ጦርነት የልጅ ብርንዶ አቅራቢ ናት። መፍትሄ ለሌለው ማናቸውም በትረ ስልጣን ልጇኝ ስትገብር ኖራለች የኢትዮጵያ እናት። እናት የኢትዮጵያ እናት እንጨት ለቅማ ሽጣ፤ ኩበት ለቅማ ሽጣ፤ እንጀራ ጋግራ ሽጣ፤ በቀን ሰራተኝነት ተቅጣራ ላቧን አንጠፍጥፋ፤ የሰው ፊት ገርፏት ወጥታ ወርዳ፤ የረባ ልብስ ሳይኖራት፤ የረባ የለማ የጣመ ሳትመገብ፤ አንጀቷን አስራ፤ ሙሉ ቀን ስትባትል ውላ ስትባትል አድራ፤ ዓመት ይዞ እስከ አመት በታከተ እድል ፍዳዋን