የአቶ ለማ መገርሳ ለህዝባቸው ሥነ - ልቦና ያላቸው ጥንቃቄ ሲሰፈር ሲከነዳ?
እንኳን ደህና መጣችሁልኝ ምርመራ። ክፍል አምስት። „እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“ መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮ የሥነ - ልቦና ጉዳቱ ከቶ መለኪያ ይኖረዋልን? ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። · በ ሥነ ልቦና ጉዳት እና ጥገና … „ከእስር ቤት የተፈታው ሰው ብዛት ሶስት ሺህም ይሁን አስር ሺህ፣ ዋናው ቁምነገር እሱ አይደለም፡፡ እስር ቤት ያለን ኦሮሞ ከእስር ቤት ማውጣት ማለት፣ ውጭ ያለን ኦሮሞ ከእስር መፍታት ማለት ነው፤ ወኔ እንዲያገኝ፣ ሞራል እንዲያገኝ ማስቻል ማለት ነው፡፡“ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ። መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ ( ዶ / ር ) April 1, 2019 | Filed under: ነፃ አስተያየቶች | Posted by: ዘ - ሐበሻ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94532#respond የሥነ - ልቦና ጉዳይ እጅግ በተመሰጠ ሁኔታ ገልጸውታል። ከመሰከረም ጀምሮ የአዲስ አበባ ህዝብ ልቡ ተንጠልጥላ ጭንቅ ላይ መኖሩስ በምን ሚዛን ሊታይ ይሆን? ነፍሰ ጡር እናት ምጥ ውስጥ ሆና...