የአቶ ለማ መገርሳ ለህዝባቸው ሥነ - ልቦና ያላቸው ጥንቃቄ ሲሰፈር ሲከነዳ?

እንኳን ደህና መጣችሁልኝ
ምርመራ።
ክፍል አምስት።
„እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“
መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮

የሥነ - ልቦና ጉዳቱ
                    ከቶ
መለኪያ
           ይኖረዋልን?

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።



·       ሥነ ልቦና ጉዳት እና ጥገና …

„ከእስር ቤት የተፈታው ሰው ብዛት ሶስት ሺህም ይሁን አስር ሺህ፣ ዋናው ቁምነገር እሱ አይደለም፡፡ እስር ቤት ያለን ኦሮሞ ከእስር ቤት ማውጣት ማለት፣ ውጭ ያለን ኦሮሞ ከእስር መፍታት ማለት ነው፤ ወኔ እንዲያገኝ፣ ሞራል እንዲያገኝ ማስቻል ማለት ነው፡፡“ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ።

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ

የሥነ - ልቦና ጉዳይ እጅግ በተመሰጠ ሁኔታ ገልጸውታል። ከመሰከረም ጀምሮ የአዲስ አበባ ህዝብ ልቡ ተንጠልጥላ ጭንቅ ላይ መኖሩስ በምን ሚዛን ሊታይ ይሆን? ነፍሰ ጡር እናት ምጥ ውስጥ ሆና ነው ዛሬ አዲስ አባባ ላይ እያማጠች በዬሰከንዱ የምትኖረው ዘጠኝ ሙሉ ወሩን ስለሆኑስ? ዜጋው የመኖር ዋስትና የለውም። የመኖር ዋስትና ከሌላ ደግሞ ማሰብ፤ መመራመር አይቻልም። ስሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሥነ - ልቦና ጉዳትስ ማነው ተጠያቂው?

የአዲስ አባባ ህዝብ ነጋ ጠባ በሽብር የሚናጥበትን በሚመለከት ምንድነው የድርጅታቸው አቋም? ሙሉ 6 ወር በስጋት፤ በሽብር፤ በፍርሃት ውስጥ ነው የአዲስ አባባ ህዝብ። ይህን ባሊህ ቢሉት መልካም ነው የሶስቱ የሲኦል መንገደኞች። ያው መከላከያው ማዳፋችን ውስጥ ነው ስላሉ … አወቃቀሩን አደራጀጀቱን ኦዴፓ መራሽ መሆኑ የታወቃ ነውና። በክፍል አራት አብራርቸዋለሁኝ።

ሚዲያውም ኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ሰብሳቢው ኦሮሞዎች ናቸው፤ የአዲስ አበባውን በክፍል አራት ገልጨዋለሁኝ። ገንዘብ ሚኒሰተር እሱም ዋነኛው ሰለባ ነው። ባንክን በተመሳሳይ ሁኔታ ነው። ኤኮኖሚና ፓለቲካ መዳፍ ውስጥ ነው።

ስለዚህ እንዳሻ በህዝብ ሥነ - ልቦና ላይ መረመማድ ምቹ ሆኗል ማለት ነው። ህወሃትስ ከዚህ ሌላ ምን ፈጸመ? ጌዲኦ፤ ጋሞ፤ ጉራጌ፤ አማራ፤ ሱማሌ፤ ባስኬቶ ሲፈናቀል ሲሳደድ ሥነ - ልቦናው ስለመጎዳቱ አልታሰበበትም። በዚህ ውስጥ የኦሮሞ ልዕልና እንዲጠበቅ የሚፈለገው በሰው ዘር ጭካኔ ዶግማ ተመስርቶ ነው።

ሰው ተዝቅዝቆ ሲሰቀል? ሰው ተገድሎ ሲቃጠል የታዬው በዚህ ዘመን ነው። ይህን ተከትሎም በአማራ ክልል ሰው በድንጋይ ተቀጥቅጦ ያዬነው በዚህ ዘመን ነው። አሁን አሁን አሁን ሳስበው ይህን ለውጥ 666 የሚመራው ይመስለኛል። ምክንያቱም ከጥሪት፤ ከቅርስ፤ ከትውፊት፤ ከሰውኛ፤ ከተፈጥሮኛ ጋር ነው እና ግብግቡ። ጌዲኦ ደግሞ በካንፕ ውስጥ ተከዝነው እንዲያልቁ ነው የተፈረደባቸው። ስለ እነሱ ነፍሶች ደግሞ ... እዬሰማን ነው ... 

ዘፍጥረትን የሰረዘ መንፈስ ዛሬ በአዲስ አዲስ አባባውዩንቨርስቲ የክብር እንግዳ ሆኖ ገላጭ ይሆናል።  የባቢሎን ግንብ ከንቱ ፋላስፋ ...በ02.04.2019


Ethiopia: ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News April 1, 2019


ሰው ይከበር ላለ ደግሞ ማስፈራራት፤ በመሳደድ፤ በዛቻ በይፋ በአደባባይም በማገድ እያዬን ነው። ኢትዮጵያ በጭካኔ በተሞላ ባርባርያን ዘመን ላይ ነው ያለችው። ጨካኞች አረመኔዎች ጎሽ ቀጥሉ የሚባሉበት፤ የገፉ ወገኖች ደግሞ የ ወዮላችሁ የሚባልበት። ለመሆኑ ጀግና ወ/ሮ ሰናይት በህይወት ይኖሩ ይሁን? ዳግሚያ ጣይቱ ከቶ እንዴት ውለው አድረው ይሆን?

የባለአደራው ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል አንድ Ethiopia: Ethiopis


Published on Apr 3, 2019
 
በዚህ ውስጥ እኔ ያዬሁት መሪ አድርገን የተቀበልነበት አመክንዮን ታማሚ መሆኑን ነው። በፕሬዚዳንት ለማ በውሳጣቸው ፈጽሞ እኛ የለንም። በውስጥ መኖር ሳይቻል ተስፋ ማድረግ ደግሞ ጉም መዘገን ነው። የዚህ የዴሞግራፊው ጉዳይ ብቻ አይደለም። ጠቅላላ አዬሩ ህውከት ያለበት ነው። አግላይ ነው። ሆድ እንዲብስ ያደርጋል። ተስፋን አድራቂ ነው። መጪው ዘመን ከህወሃት በከፋ ምልኩ ድቀድቅ ነው። 

ማናቸውም የበቀል እርምጃዎች በስልት እና በዘዴ ነው የሚከወንበት። ስለዚህ ህወሃት አድፍጦ ጉድቡን ይዞ የተቀመጠበት መንገድ ቢያንስ በሌላው ክልል የሚገኙ ወገኖቹ አንጻራዊ ጥበቃ እንዲደረግላቸው አስችሏለኝ። ለዚህ ነው በአንድም በሌላም ጥቃት ሳይሆን ጥበቃ እዬተደረገላቸው ያለው። የሚገረመው ባህርዳር ላይ ለውጥ ግምገማ ታዳሚው ተሰብስቧል። በዚህ ውስጥ የህውሃት መሥራቹ ዶር አረጋይ በርሄም ተገኝተዋል። ምነው ብአዴን ተዚህ ላይ ወገኖቼን ስለጨፈጨፍክልኝ ወረቅ ካባ ልደርብልህ አለማለቱ ግን ደንቆኛል .. ዋናው የጠ/ሚሩ አማካሪ እሳቸው ናቸው ... 

አማራ ለ አለቃው ለኦዴፓ ስታፈረሰኝ ስለባጀህ እናመሰግንህአለን ሊል ይመሰለኛል ይህ ጉባኤ እያስተናገደ የሚገኘው፤ ከዬትኛውም የ አገሪቱ ሥፍራዎች የተፈናቀሉ አማራዎች ባህርዳር ቤተክርስትያን መጠጋት አይችሉም፤ ከሱማሌ የተፈናቀሉት ደግሞ አዲስ አባባ ዙሪያ በክብር ተቀምጠዋል። 

ኬለላ ከተማ የመጡ ደግሞ አዲስ አባባ ውስጥ መታወቂያ እየተሰጣቸው ስለመሆኑ አዳምጠን ሲነቃባቸው ደግሞ አሁን ባሉበት መታዊቂያ ተሰርቶ እዬተላከላቸው ስለመሆኑም እያዳመጥ ነው። 

አዲስ አባባ ከተማ ውስጥ 6ሺህ አሰገብተናል ሲሉ ዙሩያው 500 ሺህ ግማሽ ሚሊዬን። በዚህ ውስጥ የምናዬው የአንዱን ሥነ - ልቦና ተረገጠህ ለሌላው የሥነ ልቦና ጥንቃቄ በማድረግ የተጠመደው የአብይወለማታከለ ጥምረት የንጉሱወአዲሱ ሴራ ይፋ የሆነ የዘር የማጽዳት ቅንብር የተደራጀ፤ የተቀነባረረ ዘመቻ ስለሆኑ ማዬት ይቻላል። ይህን በሽሙንሙን ያቃላት እሰጣ ገባ መለጠፍ አይገባም። ይቅርታ የተጠዬቀው የ ዓለምን ሚዲያ በመፍራት ነው። ጠንክሮ ከቀጠለ የ ኦነግ ዓላማ አከርካሪው ስለሚሰበር። ለዛ ትንፋሽ ለመሰብሰብ ነው የሰሞኑ ዘጭ ዘጭ ... 

በዚህ ውስጥ መታወቂያ እሰከ ቤታቸው ድረስ ስለመላኩ መረጃውን ታገኛላችሁ ቅኖቹ።

እሳቸው ጭንቅ ጥብብ የሚሉት ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ ነው። ይህ መብታቸው ነው። መብታቸው የሆነውን ነገር ግን እኛን በተገለበጠ ተረዱኝ የሚቻል አይሆንም። እሳቸው ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ ተጨናቂነታቸውን እያዩ እዬሰሙ ደግሞ ግድ አቅርበኝ፤ ግድ ውደደኝ ግድ አዳብለኝ የተገባ አይመሰለኝም። አሁን የብአዴን ችግር ይኸው ነው። 

እነሱ አይፈልጓቸውም እነሱ ደግሞ ተጠብቃዋል … ተንከርፍፈው … በገርባቤ ... ቆፍጣናነት በነነ።

ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ አምጥቶ ሲያሰፍር ኦዴፓ ብአዴን ጉዳዩ አልነበረም። ባህርዳር ቤተ እግዚአብሄር ላይ የተጠጉትን ሲያፈናቅል ግን ክብሩ ጌጡ ነው ለብአዴን። እኔ ይህን የማዬው አሰገድዶ የመድፈር ያህል ነው። ፍቅር የውዴታ እንጂ የግዳጅ አይደለም። ፍቅር ስትሰጠው ፍቅርን አክብሮ መስጠት ካልቻለ አንተ ስለምን በትውሰት አመክንዮ ራስህን ታታልላህ? ለዚህ ነው እኔ የሰሞኑ የግራቀኙ አፍዝ አደንዝዝ ንግግር ከልቤ ሊገባ ያልቻለው። ይለቅ ቀሚሴን አበሰበሰው... እዬፈሰሰ ... 

ሰው አንድ ጊዜ ነው የሚሞኘው። እዬሠራንልህ ነው የሚሉት ማህበረሰብ ስለሚሠራለት ያቀስስ፤ ያንግሥ፤ ያመስግን። እኛ ግን አብሶ በሰብዕዊ ጉዳዮች ላይ የምንሰራ ሰዎች እንደ ሰው ማክበሩን ባንነፍጋቸውም ግን በለበጣ፤ በመላጣ እራስን እያፈረሱ መፍቀድ ግን ሬሳነት ነው። 

የሰው ልጅ ጤናማነቱን ለማረጋገጥ ሰው ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ራሱ የመቻል አቅም አለው። እናስተውል! ፉከራ አይደለም ሁሉን እንመርምር ለማለት ነው። እኛው እራሳችን እያፈረሱን ነው።  

ለኦነግ ዓላማ ስኬት፤ ለአማርኛ ቋንቋ ክስመት አብሮ መቆም ለእኔ እብደት ነው። ለውጥ የሚባለው ኢትዮጵያን በቀደመ ክብሯ ማስጠበቅ መቻል እንጂ ኢትዮጵያን ተፎካክሮ አፍርሶ ለመስራት ከሆነ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ በአፍንጫዬ ይውጣ …

ምክንያቱም እነሱ በበታችነት ችግር ባመረቱ ቁጡር እኛ እራሳችን ማባከን ያለብን አይመስለኝም። ችግር አለባቸው። ችግራቸው ደግሞ የመነሻ ታሪክ ጉዳይ ነው። የመነሻ ታሪክን „ሀ“ ብለው መጀመር ፈልገዋል። ያ ደግሞ አይቻልም። ኢትዮጵያ እነሱ ከመፈጠራቸው በፊት የተፈጠረች አገር ናት። ኢትዮጵያ የድንቅነሽ የዓለም እናት ናት።

ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ሥልጣኔ፤ ለዓለም ሥልጣኔ ብርቱ ገናና ተፈሪ አገር ናት። ይህን ገናና ተፈሪ አገርንቷን አፍርሶ በኦሮማማ እንደገና ለመሥራት ትልም ቅንጣት የመንፈስ አቅም መዋጣት የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ይህ ፌክ ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያን እዬነቀለ ሌላ የሚተክል ስለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል።

ስለሆነም ሰሞነኛው የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር ማላገጫ ነው ለእኔ። ያው ግርባውን ብአዴን ያስድሁት በለመደባቸው የፌክ ቅኝት … እሱም ራሱን ችሎ መቆም ስለማይችል ጢባ ጢቦ ይጫወቱበት በባለንባራሱ የኦዴፓ ሰክሬታርያት በካህዲው በአቶ ንጉሡ ጥላሁን አማካኝነት።

የሰሞነኛውም አፍዝ አደንዝዝ ንግግር ርዕዮት በንጽጽር አቅርቦታልይህ ቀረህ አይባልም። የሁለቱንም የቤተመንግሥት አዛዦች ቃላዊ ዕድምታ ስለሆነ ከልብ ትከታተሉት ዘንድ እጋብዛለሁኝ በአክብሮት። ሌላው ደግሞ የተተረጎመውን ቃል በቃል ስንኝ በስንኝ ሐረግ በሐረግ አጣጥሙት ከውስጥ አድርጋችሁ መርምሩት። 

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ

እንደወረደ መቀበል መቆም አለበት። በውሸት እዬተጣፈ የልብን እዬከወኑ ማዳዳጥ እዮርን አስቆጥቶ ነው አሁን ሊዳፈሩት፤ ከቶውንም ሊፈቱት ከማይችሉ ከታላቁ አገር ከአሜሪካ ጋር ቀዝቃዛው ጦርነት ላይ የሚገኙት።

ይህ የሰው ጥበብ አይደለም … የፈጣሪ ነው። እግረ ደረቁ የ አዬር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባ ዱላ ገመዳ እና የ ኦዴፓ የሥ/ አ/ኮሜቴ አባልና የፌድራል አቃቢ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬም የቦርዱ አባል ናቸው። ኢትዮጵያ እንዲህ በለበጣ እንቆቆ ስትጠቀለል ፈጣሪ አራሳትም እና ትምክህታቸው ይፈተን ዘንድ መጠራቅቅ ውስጥ ናቸው። ውስጥ ለውስጥ እዬተንተከተከ ነው። እኔ በተከታታይ ጽፌዋለሁኝ ይሄ። 

እነሱ አንድ ብዕረኛ ጋራ እሰጣ ገባ ሲሉ የማይገሰስ ሃይሉን በእለቱ ገልጧለኝ። ኢትዮጵያ አምላክ አላት። ትናንት አንድ አመት ሆናቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እኔ መሰናዶ ነበረኝ በባለቤትነት ስሜት እከታተለው ስለነበር በበዛ ቅንነት እና የዋህነት ሁለመናዬን ሳለሰስት ሰጥቼ። 

ኢትዮጵያን ርዕሰ መዲና አልባ ብቻ ሳይሆን ዲስክርሜነሹኑ በራሱ አቅም አሳጠኝ እና ድፍን አድርጌ ተውኩት። ብዙ መልካም ነገሮች ነበሩበት። እነዛ መልካማ ነገሮች ግን መንገድ መጥርጊያ ለኦሮማማ ሥርዓት ግንባታ ስለመሆኑ መላሾ ቢጤ ስለመሆኑ በአንድም በሌላ አስተውያለሁኝ። ለነገሩ እኔ ከሐምሌ 19 ጀምሮ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ስላዬሁት ብዙ አይደንቀኝም … መንፈሱ ተጥልፏል። ጠላፊው ደግሞ ራሳቸው ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ናቸው።

የሚገርማችሁ ነገር የትናንቱን የሚሊዬነም አዳራሽ ቆይታ ሙሉውን አልተከታተልኩትም። በቅንጫቤ ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ ለማድረግ በልጆች ሥነ ልቦና የቃጡትን ነቀርሳ አዳምጨዋለሁኝ። የልጆች ነገር ስለማይሆንልኝ። ያረጋገጠልኝ ግን አቶ አዲሱ አረጋ ሦስቱ ተግተው እዬሠሩበት ስላለው መሰረታዊ መሰሪ በሚገባ ልጅቱ አመሳጥራለች። 

ነገ ደግሞ ተዋናይ ሆና እናያለን ሦስቱን የሲኦል መንገዶች በሚገባ አድሬስ አድርጋለች፤ አዲስ አባባ የ ኦሮሞ ስለመሆኗ ገልጣለች። አቶ አዲሱ አረጋ የነገሩን ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ እና ጠ/ሚር አብይ አህመድ የካዱትን ጭብጥ በሚገባ አመሳጥራለች።

Ethiopia /ሚኒስቴሩን በሳቅ ያፈረሰችው ህጻን አስገራሚ ንግግር - ህዝቡን ከመቀመጫው ያስነሳ ንግግር

Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡


የሁለቱ አድሬሲንግ የተደረገበት ሁኔታ እና ስልቱ ነው የሚለዬው። አንዱ „ሆድ ያባውን ብቅል ሲያወጣው“ ሌላው „ሙያ በልብ ነው።“ እኔ ደግሞ አንድ ልባም ነገር ልከል „ልብ ያለው ሸብ“ ልበል እንደ ጎንደሮች። ለነገሩ የፊደል እናት የሆነው የጎንደሮች ትሩፋት ትውፊት ናቸው ዘያቸው እስከ ቃናቸው። 

·       /ሚር አብይ አህመድ ወዘተረፈ ሆኑብኝሳ?

ልጅቱ ያነበበችው ቅኔው የባለቅኔው የጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደሚሆን ነው እኔ እማስበው። ሁለቱንም ሚዲያ የሚመሩት እሳቸው ናቸው። ግን እሳቸው ስንት ናቸው? ወዘተረፈ ሆኑብኝ። አንድ ሶቆቃ የተቀናበረ ዶክመንተሪ ነበር ከሜቴክ ጋር ተያይዞ የወጣ ቅንብር፤ ያ ጹሑፍ በፊትም ገልጨዋለሁኝ የሳቸው ነበር። 

የሳቸውን ብዕር ልሳን ቄንጠኛ አጠቃቀም ለማወቅ ኦህዴድ ወደ ኢትዮጵያዊነት መጣሁ ባለበት ጊዜ የተሰሩ በርከታ ዶክመንተሪዎች …OBN የሠራቸውን ልባችን ወከክ ያደረገውን፤ ትክለኛ ቋንቋ የተሰለብንበትን በምልሰት መቃኘት ነው … አይደክሙም ከብረት ቁርጥራጭ ነው የተሠሩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይህን ለኦነግ አላማ እንዲያውሉ መንፈሳቸውን የዘረፈው ደግሞ የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ መንፈስ ነው። ወንበሩ ግን ባዶ ነው። 

ጠርዝ ላይ ተንጠልጥሎ ኤሉሄ ኤሉሄ እያለ እሳት ይፈናዳል ያን ሲያድፍን ውሎ ያድራል … ጥበቡ የምህንድስናው ይኸው ነው። እሳቸውን ብቻ አይደለም፤ አንቱ የተባሉ የጥበብ ሰዎችን ገናና ጀግና ጋዜጠኞችን ሳይቀር ወደ ካድሬነት መለወጣቸውን እያዬን ነው … ያልተበገረው አንድ ለ እናቱ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ብቻ ናቸው ከጉልሆቹ ማለት ነው … እናማን ናቸው ለሚለው አይታችሁ ፍረዱ … ለዛሬው በድፍኑ ልተው ሌላ ጊዜ ይብራራል

… የእውነት አርበኛዋ ክብርት ወ/ሪት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ግን ታሳዝነኛለች። መጠራቅቅ ውስጥ ናት። ጠንቃቃዋ የፋክት ልዕልት ምን ትሁን እያልኩ አይደለም፤ ድንግል ትጠብቃት … እንጂ። እነዚህ ሰዎች ቤተ መንግሥት ለማስረከብ ዝግጁ አይደሉም … በፍጹም፤ በፍጹም፤ በፍጹም … የጠ/ሚር አብይ አህመድ ስልጣንም ፌክ ነው። ኢትዮጵያን እዬመራት ያለው ኦነግ ነው። በህወሃት ዘመን ያልተቻለውን ራቁቱ የቀረው ኦነግ አሁን ዲል ባለ ድል ላይ ይገኛል።  

ንጽጽር። ህሊና ላላቸው እውነትን ለወገኑ ... 

እነኝህን ሁለት ሊንኮች ምን ዓይነት ትውልድ በባላይነት እና በበታችንት፤ በገዢ እና በተገዢ እንደተፈጠረ አዳምጡ እና ወስኑ። „ፍርድ ለራስ ነው“ ይላሉ የጥብብ አውራ ቤተኞች የሊቀ ሊቃውንት መሰረት ጎንደሮች …


Ethiopia /ሚኒስቴሩን በሳቅ ያፈረሰችው ህጻን አስገራሚ ንግግር - ህዝቡን ከመቀመጫው ያስነሳ ንግግር

 

የሚገርመኝ ዩቱብ ላይ የሚለጥፉ ሰዎች ናቸው እራሳቸው የጻፉትን ነው ያስነበቡት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ምን ከመቀመጫ ያስነሳቸዋል? እራሱ አለባበሱ እኮ አዬሩን በምን ያህል ዲግሪ ኦነግ እንደተቆጣጠረው ያሳያል፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ልሳኑ ተዘግቷል። ለዚህ ደግሞ አቅም እንዲያገኝ ያስደረገው „አክ ወሬ“ ዘመቻ ነበር።

በሌላ በኩል ከልጅነት አንጻር ብቻ ሳይሆን በዘመነ አብይወለማወታከለወንጉሡወዲሱ የልጆች የሥነ - ልቦና ቅጥቀጣ ደግሞ ይታይ ይፈተሽ ተዚህ አንጣር …


"ስመለስ ወላጆቼን አጣቸዋለሁ ብዬ ስለምፈራ ትምህርት ቤት አልሄድም።" በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ያለ ህፃን


አማራ ዘሩ እንዲነቀል ሲደረግ 27 ዓመት ሙሉ የአሁኑ ደግሞ ሥነ - ልቦናው፤ ባህሉ፤ ትውፊቱ በፍጹም ሁኔታ የማጽዳት ዘመቻ ነው የተጀመረው። ይህን እያዳመጠ የሚያለመጥ ካለ እሱ ደመነፍስ መሆን ይኖርበታል … 


የወልቃይት፤ የጠገዴ፤ የራያ፤ የመተከል ጥያቄም ጊዜ መብያ ነው። ኦሮማማ ማንፌስቶ መሠረት እስኪይዝ ድረስ። የሚገርመው ብአዴን ክኒኑን ዋጥ አድርጎ ነው የኦሮማማን አዴፓ የሆነው ተዚህ አንጻር ነው። ለዚህ ነው እኔ ስጽፍ በቀደመው ሥሙ እምጠራው። ሰዎቹ ስንት ነገር ከውነው ሁለመናው ተቆጣጥረው እሱ ቫልዬሙን ዋጥ አድርጎ አታፍቶ እጅ ይነሳል 

… አሁን ደግሞ አንዲት ቅንጣት ውጤት ሳያመጣ እንግዳ በመቀበል እና በመሸኘት ባጅቶ ባዕል አክበሪ ሆኖ አረፈው … ወይ ነዶ!90ሺህ ተፈናቃዮችን ሜዳ ላይ በትኖ ይህን ለውጥ አንጋሽ እና አውዳሽነት ለ እኔ እብንነት ነው … በህወሃት ቤት ይህ ቀልድ አይሞርም … ለነገሩ የብአዴን ሊመንበር ስለመሆናች ጠ/ሚ አብይ ነገረውናል … በውነቱ ይህ ዝግጅት ዓመቱን ሙሉ የፌድራለሁ ስብሰባ በባጀበት አደማ ላይ ነበር መከወን የነበረበት፤ ግን ወንድ ቆፍጠን ያለ ሲገኝ ነው …


እነሱ የሚጠዬፉትን የስሜን ፖለቲካ ምድማዱን ለማጥፋት ይጣደፋሉ አያ ሆይ ብአዴን ደግሞ እራሱ ጠረኑን ማሽተት አይፈልግም። የፈለገ ድርጅት የፈለገ ኮሚሽን ይቋቋም አንድም ቦታ ሰብሳቢ አማራ ሆኖ አታዩም። አንድም ቦታ። ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ቀላል ሰው አይደሉም።

 ምህንድስናቸው ከሄርድስ መለስ ዜናዊ በላይ ጥልቀቱም ምጥቀቱም መለኪያ የለውም። ትቅማጥ እንደያዘው ሰው ነው አዬተጠደፉ ያሉት። ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ከመቋቃማቸው በፊት። ህጎች ሊሻሻሉ ወዘተረፈ ይባላለ በሁሉም ቦታ ሰብሳቢው ኦሮሞ እንዲመሆን መንፈሱም ኦሮማማ ስለመሆኑ እኔ ለደቂቃ አልጠራጠርም።

  በስልት የያዙት ጉዳይ ሁሉንም ከነሰብዕናው የሚደረምስ ነው። የበላይ አድርጎ ማውጣት የሚፈልጉት ደግሞ በሁሉም ዘርፍ ኦሮማማን ነው። ይህን መፍታት የተሳነው ባለቅኔ ሰኔል እና ቹቻውን ገዝቶ ለሽ ይበል መሬቱን ቆፍሮ … አፍ ባለው መቃብር መከዘኑ ዛሬም አልገባው ብሎ የልቡን ለሰራ ካቢኔ አሁንም ራሮት ያደርጋል።

ንግግሩንም የልጅቷንም ሥነ ግጥም ሥራዬ ብላችሁ መርምሩት። በአንድ ዓመት ይህ ሁሉ ሁለመናን እርስት ማድረግ ከተቻለ በቀጣይ ዘመን መከራው በጣም በጣም ተራራ ነው … „ልብ ያለው ሸብ“ ይላል የጎንደር ሰው። የሰው ልጅ ከብት አይደለም በአሞሌ የሚታለል … ኢትዮጵያን አፍርሶ ለሚሰራ ብልጥ ፖለቲካ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ማለታይን ነው ለእኔ ዛሬ ላይ …

ኢትዮጵያ ባለቤት የላትም። ባለቤት ለመሆን ደግሞ ፈቃደ እግዚእብሄርን መጠዬቅ ነው። ጨርሶ ጠረኑ የኢትዮጵያን ቀደምትነት ተፃሮ የተነሳ ነው። እንጥፍጣፊ የዝና፤ የሙገሳ፤ የውዳሴ ከንቱነት ለሚፈልግ ምቹ ጊዜ ሊሆን ይችላል። ለመራራው እውነት ግን ገራራ ጊዜ ነው።

የተቀማነው ሁለመናችን ነው። የተሰለበው ሁለመናችን ነው። ስለምን? ታማኞች ስለሆን። ግን በመታመናችን ቀጣይ መከራን ለመሸከም የፈቀድነው ስለሆነ ሊጎረብጠን አይገባም። ቁምነገሩ ከሸክሙ ለመውጣት፤ ህሊናችን በማዳዳጥ ፖለቲካ ያዛልነውን አሰርተን ፈጣሪ አዲስ አቅም እንዲፈጥርልን፤ አዲስ መንገድ እንዲከፍትልን  በአጽህኖት መለመን ነው … ቢታደገን …

ቁርጥ ያጠግባል!

ቁርጣችን አውቀናል። ስለዚህ ስለ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ቀጣይ አገዛዝ ከእንግዲህ ከብት ስላልሆን አሞሌ አለመፈጋችን ግን በአክብሮት ቢደርስልኝ እሻለሁኝ።

 እርጋታቸውን፤ የአነጋጋር ዘያቸውን ሥነ-ምግባራቸውን አከብረዋለሁኝ። ወስጣቸውን ግን ተስፋ አላደርገውም። እኔ እንዲያውም በስሜን አሜሪካ ጉብኝት ወቅት ደርበብ ባለ ሙቀት ቆይቶው ሜኖሶታ ላይ እንደዛ ሲፈነድቁ ከቤተሰብ ጋር ተነጋግረንበት ነበር። ምን በድላናቸው ነው እንዲህ ያራቁን ብዬ ሁሉ? ምንስ አጠፋን? ታግተው የቆዩ እኮ ነው የመሰሉት ብዬ ሁሉ ነበር

እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ያየነው አይተን የሰማነውን ሰምተን የታዘብነው ታዝብን እንደ ሬሳ ግን መንፈሳችን መሬት ለመሬት እንዲጎተት አንፈቅድም። ለኦሮሞ ወገኖቻቸው ይኑሩላቸው። ያሰቡትን ምህንድስና ያሳካላቸው ብለን ስንል አኛ ግን እንቆቋችን ተግተን መሆን ይነርበታል። መራራ ስለሆነ።

በሰጠነው ትህትና፤ በሰጠነው ንጹህ ፍቅር፤ በሰጠነው አክብሮት ደግሞ አንጸጸትበትም። ኢትዮጵያዊነት ያ ስለሆነ። ማፈር፤ መሸማቀቅ ያለበት ከዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ለወጣ ካህዲ ነፍስ ብቻ ይሆናል። ቅንነታችን በፈጣሪ ዘንድ በረከት ቢያሰጠን እንጂ የሚያስቀንስብን አንዳች ነገር የለም። ለውላታም አልነበረም። ለሹመት ለሽልማትም አልነበረም።

ድምጣቸው ሲጠፋ እንኳን እኔ በግሌ ጭንቅ በጭንቅ ነበር እምሆነው። ውርስ ኦነግ ያደረጉትን ሚዲያቸውን ሳይቀር ጎራ ብዬ እፈትሻዋለሁኝ። አሁን ከዚህ ሁሉ ስላዳኑኝ አመሰግናቸዋለሁኝ። ሃሳብም፤ መንፈስም ህሊናም አቅምም አይባክንም። ኢትዮጵያን እዬመራት ያለው ዘመን ያለው ኦነግ ነው።

ይልቅ ሃዘን እጠብቃለሁኝ የአማራ አክቲቢስቶች፤ የአማራ ጦማርያን፤ የአማራ የሚዲያ ሰዎች፤ የአማራ ጋዜጠኞች አዲስ አባባ ላይ ምን እና ምን ይሆኑ ይሆን እንዲህ በቀል በሳንጃ አንቱ ሲሆን እላለሁኝ። እፈራለሁኝ። ማህዲሱ አይማረኛ ላልምርህ ከቤተ መንግሥት መንፈሴ የወጣ ዕለት ስላለ … ስጋቴ ከባድ ነው። ጠረኑን እያፈነፈነ አደናው ይቀጥላል … ሊንኮቹ ደጋግሞ መለጠፋቸው የተገባ ነው ... ደጋግሞ ማድመጥ አላምጦ መዋጥ ለዚህ ዳጥ እና ምጥ ዘመን መስተዋል ቢሰጠን በሚል ነው ... 
ይህቺ ትኩስ ዜና ናት

የተከሰከሰው የኢትዮጲያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ የመርማሪ ቡድኑ ቅድሚያ ሪፖርት ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!

የኔዎቹ እውነትን እንወግን እባካችሁን?
መሸቢያ ጊዜ ኑሩልኝ!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።