ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 30, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ከመጋቢት 24 ጀምሮ የተጠለፈው የሴራ ጉንጉኑ ሊፈታ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል

ምስል
የወለም ዘለም ዘለበት የተስፋ መባቻ ክስመት። „የማይታዬው፤ ከዚህ የሚበልጠው ፍጥረቱ ግን ጥቂት ብቻ ነው።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፫ ቁጥር ፴፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 30.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ዛሬም እዛው አቶ ጃዋር መሃመድ ሰሞነኛ መግለጫ ሁለቱን ብቻ አነሳለሁኝ። እርግጥ ተያያዥ ሁኔታዎችን ማንሳት ግድ ይላል። የተለመደው የጭንቅ ጊዜ ዓመት ድገሙ እያለን ስለሆነ። መጋቢት ደግሞ ተመልሶ በወርሃ መሰከረም ዱብ ብሎ ጭንቀትን ያስኮተኩተናል።  ስለምን በሰሞናቱ ነገር ምነው ዝምታ ተብያለሁኝ። የኦሮሞ 5 ድርጅቶች ሚዲያቸው እና ተከሳሹ ኢሳት እስከ ግንቦት7 ያለውን ሙግት ሁለቱም በአካል መሬት ላይ ስላሉ ተከታዮቻቸውም ሙሉ ስለሆኑ እንደ ቀደመው ጊዜ ተጠቃ የምለውን ወገኜ ሙግቱ ይብቃኝ ስላልኩኝ ነው። አዬሁት እስኪበቃኝ። ሁሉም ለወገኑ እንጂ እንደ እኔ ያለው ተማላ ገብቶ ከሳት መረመጥ ከምንም የማይቆጠር እንዲያውም በተደጋፊው አቅም ልክ ደጋፊውን በዘመቻ የሚያጠቃ ስለመሆኑ ተማርኩበት። እንኳንስ ደጋፊን ዕውቅና ሰጥቶ ማገዝ ቀርቶበት ሌላ የማጥቃት ዘመቻው ቢቀር በስንት ጣዕሙ። ለዚህ ብልሁ ወያኔ ብቻ ነው። ደጋፊዎችን ጥሎ አይጥልም። ስለመሆኑም ዝምታ በስንት ጣዕሙ በሚል መነካካት አልሻም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አምስግኑኝ እንጂ ውቀሰኙ ብሎ ፈቅዶ አያውቅም። ተመስግኖም አመስጋኙን ሲያጠቃ ነው የኖረው። ወደፊትም ጉዞው እንደዛው ነው። ·        ሁለት ሀሳቦች ይነሱ። በዚህ በሰሞናቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ መግለጫ የዶር አብይ አህመድ ሙሉ ደጋፊ እንዲያውም ተሟጋች እና ተቆርቋሪ ሆኖ ቀርቧል። የለውጡም ሐዋርያ እና ለውጡን በማስቀጠል እንደሚታገም ...