ልጥፎች

ከኦክቶበር 10, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኮከቧ ኢትዮጵያዊ የR & B ዘፋኝ - የግራሚ አባል ናት፣ ከኩል ኤንድ ዘ ጋንግ እስከ ሀሊዉድ ተዋናይ ጋር መስራት...

ምስል

ፋኖ ባክግራውንዱ "ሽፍትነት" አይደለም። ፋኖ አፈጣጠሩ ሲፈረካከስ ውሎ የሚያድረው የውራጅ ፖለቲካ ርዕዮት አልፈጠረውም።

  ፋኖ ባክግራውንዱ "ሽፍትነት" አይደለም። ፋኖ አፈጣጠሩ ሲፈረካከስ ውሎ የሚያድረው የውራጅ ፖለቲካ ርዕዮት አልፈጠረውም።   ሰማዕቱ የተከበሩ ጄኒራል ሰኃረ መንፈሳቸው ምን ይታዘብ ይሆን????    በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት፤ አሠራር፤ አቅም፤ አመራር እጅግ ጠንቃቃ እና ቁጥብ ነኝ። ዛሬ በዚህ ዕርስ ዙሪያ ስጽፍ የዜግነት #ተጋርቶዬ እራሱ እያሰቃዬኝ ነው። በአንድ ላይ ኢትዮጵያዊ መባል ምን ያህል ፈተና መሆኑን ያዬሁበት አጋጣሚ ነበር።    "አቤቱ ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርለት።"   የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ዘለግ ያለ ሙግት ነው።   የማህበረ ኦነግ ፖለቲካ - ልቅነቱ ብቻ አይደለም የሚያስገርመኝ። ይልቁንም የቁንጮ መሪወቹ የህግ ጥሰት #ህጋዊነት እንጂ። ብልሽቱን እኮ አስተካክሎ ማቅረብ ለካስ ይህም መሰጠትን ይጠይቃል። ሳይመረኝም፤ ሳያንገፈግፈኝም የኢትዮጵያ ኢታማጆር ሹሙ ጄኒራል ብርኃኑ ጁላ ከሉዓላዊ ሚዲያ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ሁለቱንም አዳመጥኩት። መጥኔ ለአንቺ ኢትዮጵያ አልኩኝ።    እነ ክቡር ጄኒራል ፈንታ በላይ እና ፍፁም ድንቅ እና ብቁ ጓዶቻቸው የነበሩባት አገር እንዲህ እና እንዲያ ስትንገላታ፦ ወጀብ ሲንጣት ማዘን የሚለው ቃል አይገልፀውም። አቅምስ አቅልስ የት ይሸመት??? ለምን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በዬጊዜው የሚበውዙት የካቢኒያቸው፤ እንዲሁም "የብልጽግናቸውም" #ኮሚሳርያት አድርገው ደርበው አይሾሟቸውም የኢትዮጵያን ኢታማጆር ሹሙን። የኢትዮጵያ አዬር መንገድን እና የኢትዮጵያ አዬር ኃይልን እንዳጣመሩት።    ሥርዓት ለኦነግ ፖለቲካ አጀንዳው አይደለምና። ወይንም ላም ጣም በሌላቸው የዶር ለገሰ ቱሉን #የኮሚኒኬሽን ቦታን አይሰጧቸው??? አንደበቴ፤ ልሳኔ ስለሆኑላቸው። ለነገሩ ጄኒራል ብ