ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 24, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ፕ/አሻግሬ ይግለጡ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠዬቁ፤ የመደመር ፍልስፍናንም ፈቀዱት!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ቀን የሰጠው ዕውነት ! „ጥበብን አ ውቅ ዘንድ፤  በምድር የሚሆነውንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ።“ መጽሐፈ መክብብ ፰ ቁጥር ፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 24.01.2019 የቅኔ ዘጉባኤ። ·        እፍታ።  ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? የአይዋ በረከት ጉዳይ እንዴት ያዛችሁ? ስልኩ የጉድ ነበር አሉ በዬአቅጣጫው አገር ቤትም ውጭ አገርም የእንኳን ደስ አለን። ደስታ ቀላል? ፍትህ በእግሯ ቁማ የሄደችበት ዘመን። ለዚህ ነበር “ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን” ለመቅጨት የወረፋ ሩጫ በነበረበት ወቅት አደብ ግዙ እያልን ስንመክር የነበረው። ጎንደሮች ይህን “የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል” ይሉታል። ይኸው ተጋድሏችን ፍሬ አፈራ እንዲህ ...  አሁንም ቢሆን በላይ በላይ የቤት ሥራውን ከመደርደር ልባሞች ስለያዙት አደብ እንላለን ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ፤ ይህንም ጎንደሮች “የፊት የፊቱን ይላል ጓያ ነቃይ” ይሉታል። ግን ጓያን ታወቁታላችሁን? ጎንደር ደንቢያ አካባቢ የሚበቅል የጥራጥሬ ዘር ዓይነት ነው፤ እንደ ሽንብራ ይቃጣዋል … የጓያ ሰባራም የሚባል አለ፤ ሽፋኑ ለጤና አይመረጠም፤ ብቻ ዘሩ እንደ አንዱ ነው ልክ የቋንቋ ዘርፍ የሴም - የካም - የኩሽ እንደሚባለው ዓይነት … ·        ጠብታ። ለ4 ሳምንታት የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ቃለ ምልልስ ሲያሸን ባጅቶ ዛሬ አጠናቋል። የአውነት ነው ማሸት የሚለውን ነገር የተጠቀምኩት። ልቤ ተንጠልጥሎ ነው የሰነበ ተ ው። ክፍል አንድ አነሰች እንደገና ሳምንት ጠበቅን፤ ክፍል ሁለተም እንዲሁ ... የናፍቁት ነገር ቀርቦ ሲርቅ የደረሰበት ያውቀዋል ...  ብቻ ድምጣቸውን

ይድረስ ለአቶ ጌታቸው ረዳ! (ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ።)

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ይድረስ ለአቶ ጌታቸው ረዳ ! “አውቃለሁ ለኅጣእ ግን ደህንነት የለውም፤ በእግዚአብሔር ፊት አይፈራምና፤ ዘመኑ እንደ ጥላ አትረዝምም። ” መጽሓፈ መክብብ ፰ ቁጥር ፲፫ ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ ጥር 2011 ዓ/ም (ጃንዋሪ 2019) ሲድኒ አውስትራሊያ አቶ ጌታቸው ሆይ - ዕውን የነበረከት እስር ደንቆኃል? ወይንስ ነግ በኔ ታይቶህ ደብሮኃል? አዎ ባንተ ልኬት እነ በረከት በሙስናው ዝቅተኛ ወለል ላይ የሚገኙ ናቸውና የታሰሩበት ምክንያት ፖለቲካዊ ነው ብለሃል። (ይገርማል ደግሞ የዝርፊያቸውንም ልክ ታውቃለህ ማለት ነው?) ለማንኛውም እስራቸው ፖለቲካዊ መሆኑን ለማን ነው የምትናገረው? ለራስህ ከሆነ ዕውነት ብለሃል። አንተና በረከት ሞክሼህ ጌታቸውና ሁላችሁ በህወሃት አቁማዳ ውስጥ ሆናችሁ ከኢኮኖሚው በባሰ በፖለቲካው የሰራችሁትን ሰቆቃ ታውቃለህና! አዎ! እንኳን እኛ ዓለም በረከትን የሚያውቀው በዘር አጥፊነቱ <በናዚስት ጎብልስነቱ> ነው። ስለ በረከት <ናዚስታዊ ተግባር> (የኛን ዝርዝር ለጊዜው አቆይተን) የአውሮፓ ፓርላማን ስመ ጥር አባል ወ/ሮ አና ጎሜዝን ዋቢ እንሰጥሃለን። ክሱ ከምንጠበቀው ከፍታ ላይ እስኪወጣ <አይነኬው> በረከት <በኢኮኖሚም> ቢሆን መታሰሩ ወደ እናንተ መቅረባችን ነውና እኛ ደስ ብሎናል! ደግሞምኮ መንግሥት ነኝ ብሎ ሀገር መዝረፍ፤ የድሃ ጥሪት መግፈፍ ያስቀፈድዳል - በተዘረፈ ሀብትና ንብረት ክምችት መለኪያችሁ ወለልም ላይ ሆንክ ጣራ ላይ!! ዘንድሮ ከነ ጓ ዶችህ አይቀርላችሁም። ረስተኸው ከሆነ <እሳትና ጭድ> በሚለው የዘር ዕልቂት ፕሮፓጋንዳህ ትጠየቅበታለህ/