ኢትዮጵያ የገነፈለ ሁሉ #ፍላት ማጠራቀሚያ በርሚል አይደለችም። ሁልጊዜም "ማህረቤን ያያችሁ" ሰለቸን። ገለማን!
ኢትዮጵያ የገነፈለ ሁሉ #ፍላት ማጠራቀሚያ በርሚል አይደለችም። ሁልጊዜም "ማህረቤን ያያችሁ" ሰለቸን። ገለማን! "አቤቱ ንጹህ ልቦና ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፯ #ጠብታ ። የኢትዮጵያን ልኳን በልኳ ልክ መጠኖ መነሳት ይገባል። ለኢትዮጵያ የክት እና የዘወትር፤ የእዳሪ እና የቤት፤ ምርጥ ዘር እና አልባሌ፤ ዓይነታ እና አሰርውሃ የሚባል ጉዳይ የለም። የዜግነት እርቦ እና ሲሶ የለውምና። ሺ ሚሊዮን ጊዜ ይመስጠር፤ ይከደን የሃቅ አቅም ይንደዋል። ሁልጊዜ ልበጣ በስልቃ #ቃ ያለ ጉዞ ነውና። #ኢትዮጵያ ለከበደችው ስኬቱ አይደለም ተሸፍኖ፤ ገሃድ ሆኖም ጋዳ ነው፤ ገድጋዳ - ገዳዳም። ሰሞኑን የልጅ ሞገስ ሚዲያ እንደ ነገረን፥ ሰነዱንም አንብቦልናል፤ አሜሪካ ላይ የተቋቋመው ልክ ግንቦት 7 "አገር ማዳን" በሚል ለዛውም ግለሰቦችን ሳይሆን ግንቦቲዝም ተቋማትን ነበር ያሰባሰበው። ያው በአሰልቺው ድግግሞሽ "ኢትዮጵያን ማዳን" በሚል እራሱን #የፈራ ፤ እራሱን የሸሸ ቡድን "አገርን ስለማዳን" ቅርንጫፋን አውሮፓ አምስተርዳም ላይ እንደ ፈጠረ ዜናውን ነግሮናል። ልጅ ሞገስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ በትጋት እየተሳተፈ፤ አውሮፓ ተቀምጦ ስለምን እንዳላከሉት አላውቅም። የሆነ ሆኖ በግልጽ ቀርቦ ቀጥተኛ ፍላጎትን፤ ዓላማ እና ግብን ማሳወቅ የቲሙ መብት ሳይሆን ግዴታው ነው። እነኝህ ክንብንብ ያሰኛቸው እነማን ናቸው??? ኢትዮጵያ እኮ ሉዓላዊ የተከበረች አገር ናት። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ዕውቅና ላላት አገር፤ በገሃድ ላለች፤ ዓለም በብዙ ሁነቶች ለሚያውቃት ቀደምት አገር በስውር ቲም ትንሳኤሽን እናመጣለን #ጠብቂኝ የገ...