#ወፍሽ።

 

ምዕራፍ ፲፯
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
ቀንሽ ራሄል …
እንደ እኔው ሲዋልል
ጥንካሬሽ ቢያባብል
አሳሩ ግን #ድንብልብል
የመከፋት ተራራ ዝልብልብ
የሂደት ጉዞ ጉስቁልቁል።
ልጄ ልብስ የለው መንገድ አዳሪ
ዋስትና ያጣ መንገድ ላይ ቀሪ።
ሞፈር ቀንበሩ ዝናብ ጠባቂ
ምርተ - ውጤቱ ያልሆነ በቂ፤
#ጀንዴ የሌለው #ተስፋን ናፋቂ
#ገሳ ለባሹ ለራብ ተጠቂ።
ድሆኖው ባዶ ሲሳይ የነሳው
ተምቹ ትንኙ ፋታ ያሳጣው፤
ጥማቱ #ጠኔው የሚነስተው
በሽታ ዱላው የከተከተው።
እልፈተ ቢሱ ያነ………#ገበሬ
ራዕዩን ሁሉ በላበት አውሬ።
ላዋይሽ ራሄል እስኪ ነይ
እባክሽ እናቴ አንድ በይ።
ለምዕተ ዓመታት በአንድ #ከፈን
አቶ #ማለፍን በመለመን፤
እህህ ሆነው የእሱ ዝግን
የበሬው ጌታ ፍሬዘር።
#የእናት አገር ምሬት።
#ህዳር 3 ቀን 2001 ዓ.ም ሲዊዘርላንድ ሄርሽን ሆቴል።
መክሊት የአዋቂወች የግጥም መድብል ከገጽ 98 -99 ለህትምት የበቃ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/10/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።