"የሰው ልጅ ለአንድ ዓመት በማርስ ላይ መቆየት ምን ሊመስል ይችላል?" BBC
https://www.bbc.com/amharic/articles/cp38kpn71n8o "የሰው ልጅ ለአንድ ዓመት በማርስ ላይ መቆየት ምን ሊመስል ይችላል?" ከ 3 ሰአት በፊት "ከጥቂት አስርት ዓመታት በፊት ወደ ቀይዋ ፕላሌት ማርስ የሚደረግ ጉዞን በልቦለድ ፊልሞች ብቻ የምንመለከተው ነገር ነበር። ዛሬ ላይ ቴክኖሎጂ ዘምኖ፤ የተመራማሪዎች እውቅት እና ፍላጎት ዳብሮ ወደ ማርስ የሚደረግ ጉዞ እውነት ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ አለ። ለዚህም ቅድመ ዝግጅት በሚመመስል ሁኔታ የሰው ልጅ ወደ ማርስ ለመጓዝ ቢነሳ ረዥሙን ጉዞ እና ተስማሚ ባልሆነ ቦታ መኖርን ለማላመድ አራት ሰዎች በማርስ አምሳያ ወደተሠራ ቦታ ከዓመት በፊት ተልከው ነበር። ከአሜሪካ የሆኑት ኬሊ ሃስተን፣ ሮስ ባሮክዌል፣ ናታን ጆነሰ እና አንካ ሴላሪዬ የአንድ ዓመት የማርስ ቆይታቸው ምን ይመስል ነበር? የናሳ ሳይንቲስቶች በሂዩስተን ቴክሳስ በሚገኝ የጠፈር ምርምር ማዕከል ውስጥ ወደፊት ተመራማሪዎች ወደ ማርስ ሲጓዙ ሊገጥማቸው የሚችለውን እንዲሁም ኑሯቸው ምን ሊመስል እንደሚችል ለማሳየት የማርስን አምሳያ ፈጥረዋል። በማርስ አምሳያ ወደ ተሠራው ስፍራ የተላኩት አራት ተመራማሪዎች ለአንድ ዓመት ያክል በስፍራው ቆይተዋል። በዚህ ወቅት ተመራማሪዎች የአራቱን ግለሰቦች አካላዊ እና አእምሯዊ ጤና በቅርበት በመከታተል የተለያዩ ግዳጆችን እንዲፈጽሙ ያዟቸው ነበር። አራቱ ግለሰቦች ለመጨረሻ ጊዜ ሰማይ ከተመለከቱ ዓመት አልፏቸዋል። ከሚወዷቸው ወዳጅ ዘመዶችቻው ተለይተው 12 ወራቶችን አሳልፈዋል። ። ለ370 ቀናት ከተቀረው ዓለም ተገልለው በማርስ ሊኖር በሚችል ሁኔታ ውስጥ ቆይተዋል። ይህ ቆይታቸው ናሳ ካካሄዳቸው የጠረፍ ጉዞ ቅድመ ዝግጅቶች ረዥሙ ነው። የዚህ ጥናት ዋነኛ ዓ...