እኔም #ጦርነት #በቃንን! በድፍረት የምገልጸው የውስጤ #ቃለ #ምህዳኔ ነው። ዘገባው #የBBC ነው
እኔም #ጦርነት #በቃንን ! በድፍረት የምገልጸው የውስጤ #ቃለ #ምህዳኔ ነው። #ግንንንንንንን -----------------ግን ኢሠመኩ #ትርታው አለችን? #ነፍስ #ይማር #ብዬ ነበር። በነገራችን ላይ ዘገባው #የBBC ነው። የጭንቅ ሂደቱን ዘገባ ሊንኮችን አያይዤ አቅርቤያለሁ። ሰሞኑን ስለፃፍኳቸው ዕይታ መሠረት ስለሆነ መረጃው። የመነሻ ዘገባውን ግን ሙሉ ዝርዝሩን #የBBC ከሥር አቅርቤያለሁኝ። ዛሬ #የድሮን ዘገባ አለ። የጦርነቱ ሂደት እያደገ መሆኑን ያሳይ ይመስለኛል። " #ጦርነት በቃን!" የሚሉም ሰልፎች በቲክቶክ ላይ አይቻለሁኝ። ይህ የመላ ኢትዮጵውያን ድምጽ እንዲሆን እመኛለሁኝ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ሥርጉትሻ 31/01/2026 =====================///////==============---- «በአላማጣ እና ኮረም የተከሰተው ምንድን ነው?» BBC. • https://www.bbc.com/amharic/articles/c5y5z0360qro 30 ጥር 2026 "የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ኃይሎች ከአላማጣ እና ኮረም ከተሞች መውጣታቸውን እየተዘገበ ባለበት ወቅት ነዋሪዎችም ለደኅንነታቸው በመስጋት እየሸሹ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገለጹ። ግጭት ይቀሰቀሳል በሚል እና ታጣቂዎች "የሚወስዱት እርምጃ ስጋት ፈጥሮብናል" ያሉ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች አካባቢዎች በመጓዝ ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአላማጣ ነዋሪ እንዲሁም የቀድሞ የአካባቢው ባለሥልጣን እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር ሥር የአላማጣ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ዝናቡ ደስታ በከተማው ውጥረት መኖሩን እና ነዋሪዎች እየሸሹ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀ...