#መጠሪያችን ማን ይሆን ዘንድ ከቶ ፈቀድን???? #ጦርነት እኮ #የሞት #ዓዋጅ እኮ ነው። ይህ በፍቅር እፍ ያደርገናል።

 

#መጠሪያችን ማን ይሆን ዘንድ ከቶ ፈቀድን????
#ጦርነት እኮ #የሞት #ዓዋጅ እኮ ነው። ይህ በፍቅር እፍ ያደርገናል።
ጦርነት እንደ እኔ #ቤርሙዳ #ትርያንግልም ነው። ይህ በመውደድ ያከንፈናል? ግን እኛ ምንድነን።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
#ግን እኛ አድራሻችን ፍጥረተ ነገራችን ከያት ይሆን?
#ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዮን ወገን ያለን --- - እኛ
#ለአንድ ሰዓት እንኳን የሚያቆይ የለት ደራሽ የምግብ ክምችት የሌላቸው በሺህ የሚቆጠሩ ቤተሰብ ያለን --- - እኛ ---
#የሚሠሩ እጆች እያሏቸው በራህብ ምክንያት ቀያቸውን ትተው የሚሰደዱ ሺህ ወገን ያለን --- - እኛ
#ልቀቁልን ተብለው ከባዕታቸው የተነቀሉ ሁነኛም የሌላቸው የሚሊዮን ዕንባ ቤተኞች የሆኑ ወገኖች ያለን --- - እኛ ---
#በየዘመኑ በፖለቲካ ቀውስ የሚሰደዱ፤ የሚታሠሩ፤ የሚበተኑ ቤተሰቦች፤ የሚፈርሱ ጉልቻወች ያለን -- - እኛ ---
#በኑሮ ደረጃ በነፍስወከፍ ገቢ ከዓለሜ ይሁን ከአህጉራችን መጨረሻወቹ የአፍሪካ ተርታወች ውስጥ የምንገኜው -- እኛ
#በተፈጥሮ ይሁን በሰው ሠራሽ አደጋወች የወጣትነት ተስፋቸው ተጎሳቁሎ ሙሉ አካላቸውን ያጡ በርካታ ልጆች ያሉን ---- እኛ ---
#በአንድም በሌላም ሰርክ የትርታችን ትንፋሽ ሞት፤ መርዶ ስንቃችን እንዲሆን የተፈረደብን የዚህ ትውልድ ቤተኞች ---እኛ ---
#ለወቀሳ መቅድምነትን የምንሻ፤ ለመወቀስም ሽሽትን የምናጣድፍ እራሳችን በራሳችን የተቃረን - እኛ ……-
#ለውዳሴ፤ ለመሞካሸት፤ ለጭብጨባ ግን በጥድፊያ ላይ የምንገኝ ---- እኛ
#የትውልድ ማገዶነት ፈጽሞ የማይሰለቸን --- እኛው --
#ወጣት ጡረተኛ አብዝት የሚናፍቀን -- እኛ
#በግለሰብ ሰብዕና ግንባታ ላይ አቅማችን ሁሉ የምንደፋ፤ ለቋሚ ሰውኛ፤ አጽናኝ ቋሚ የተፈጥሮ ተቋማ ለመፍጠር የማንተጋው -- እኛ
#ሰውኛ ተብለን ተሸልመን፤ ባለማዕረግ ሁነን፤ እራሳችን ተፃረን የቆምን --- እኛ ---
#መጠሪያችን ማን ይሁን? መጠሪያችን ምን ይባል?
 
ትናት ጦርነትን ማቀድ መፈጸም -- ዛሬም ጦርነትን ማቀድ መፈጸም እንደ ትውልድ አባልነታችን አብረን ሁላችንም #ልናፍረበት የሚገባ የእኛው የራሳችን ገመናችን ነው። 
 
#ዛሬ ዕንቅልፍ አልተኛሁም።
* እንዴትስ ዕንቅልፍ ይውሰደኝ?
** ሁልጊዜ ሃዘን?
*** ሁልጊዜ መርዶ፤
**** ሁልጊዜ ሰቀቀን፤
***** ሁልጊዜ ጭንቀት????
ትናንት #የራህብ *ዜና፤ በማግስቱ #የባሩድ ፋክክር ዜና??? ኧረ ምን ጉዶች ነን??????
እራሳችን --- መምራት፤ ውስጣችን ማጽዳትም ማረም ያቃተን - እኛው፤
በመካሰስ ብቻ ዘመንን #በመሸንገል የክብር - የዝና - ምኞተኞች - ምቾቶኞችም --- እኛው???
ከሊቅ እስከ ደቂቅ እራሳችን ፈቅደን እስኪ --- እንፈትሸው? እስኪ ---- እንረመውም። #አረም አሳቦችን ከውስጣችን እናጽዳ። እግዚአብሄር የሸንጋዮች አይደለም። እግዚአብሄር የፃድቃኖችን ዕንባ ለመስማት ጆሮውን ያዘነበለ ቀን መካሰሱ ቀርቶ፥ ሁሉም እግሬን አውጬኝ ይሆናል። የፈጣሪ ውሳኔ ከሰው ልጅ #የስልጣኔ አቅም ነው። 
 
* ቅንነትን ገፍተን፤
** ርህርህናን ገፍትረን፤
*** ሰውኛነትን አሽቀንጥረን፤
**** አይዟችሁ!------- ባይነትን አልይህ ብለን፤
****** አጽናኝነትን ተጠይፈን የምናተርፈው ብሩክ ትውልድ አይኖርም። እራስን ማዬት ውስጥን ለማረም መወሰን፤ ከራስ እራስን ሃግ ለማለት ከሊቅ - እስከደቂቅ የመወሰን አቅም ይኑረን። ዕውነት ከቦታው ለቆ አያውቅም። ዕውነትን - እንድፈር። ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም ነው። 
 
እንዴት አደራችሁልኝ ክብረቶቼ?
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©ሥላሴ
30/01/2026
ልቦናችን ሁሉ ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን። አሜን።
ደክሞኛል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።