ልጥፎች

ከማርች 7, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዘለግ ያለ ሙግት ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር። ዕውን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጠሚር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚር ከመሆናቸው በፊት #አያውቋቸውም ነበርን? ኮሚኩ ድራማ። ተያያዥ ጉዳዮችንም አነሳለሁኝ። የእሳቸውን ጉዳይም በዝምታ ነበር ስታደም የባጀሁት። ዛሬ ግን ይደባበስ። በእኔ ቤት እንክህ እንክህ አይታሰብም እና።

ምስል
  ዕውን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጠሚር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚር ከመሆናቸው በፊት #አያውቋቸውም ነበርን? ኮሚኩ ድራማ። ተያያዥ ጉዳዮችንም አነሳለሁኝ። የእሳቸውን ጉዳይም በዝምታ ነበር ስታደም የባጀሁት። ዛሬ ግን ይደባበስ። በእኔ ቤት እንክህ እንክህ አይታሰብም እና።    "አቤቱ አድነኝ፤ ደግ ሰውአልቋልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጎድሏልና።" (መዝሙር ፲፩ ቁጥር ፩)     https://www.youtube.com/watch?v=maffafwButk Anchor Media '' ትልቁ ጥፋታችን ስልጣኑን ለአብይ አህመድ መስጠታችን ነው።'' ዶ/ር ገዱ አንዳርጋቸው   እንዴት ዋላችሁ አመሻችሁም ማህበረ ቅንነት። ደህና ናችሁ ወይ????    ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን በቀደመው ጊዜ የአማራ ክልልን በቁንጮነት ይመሩ ከነበሩት፤ "በሱሴ" ኦሮማራ ዘመን ቲም መሪነት፤ ቀን ቀና ሲልም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ የነበሩት፤ ቀን ደፋ ሲልም የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የደህንነት አማካሪ የነበሩት፤ ቀን ሲያነክስም ከሁሉም የሥልጣን ኃላፊነቶች ጋር ፍች የፈፀሙት ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ክፍል ፩ አዳመጥኩት። ክፍል ሁለት መጠበቅ አላስፈለገኝም። ሳዳምጣቸው ነውና የባጀሁት። አዲስ ነገር የለውም።    ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አቅም ባለው ሁኔታ አልሞገታቸውም። ምክንያት እሱ #ተስፋ ለሚያደርግበት አዲስ የለውጥ ዋዜማ አጓጓዥ በመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ጠቀም ያለ ልምድ ያላቸውን፤ በውጭ የዲፕሎማቱ መድረክም ከሁሉም የተሻለ አጋጣሚ ተፈጥሮላቸው ከነበሩ ፖለቲከኛ የሚገኘውን ተመክሮ ሥራ ላይ ለማዋል ታስቦ ይመስላል ውይይቱ #የቤተ - #ዘመድ ዓይነት ይመስል ነበር - ለእኔ።   ዶር ገዱ ...