ልጥፎች
ከጁላይ 5, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
#ፈለገ ሰላማዊቷ - ሲዊዝሻ። ቅን ነሽ እና ይቅናሽ። አሜን። #መልካም #ዕድል ልባሟ ሲዊዝሻ። አሜን።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
Viel Erfolg. Ich hoofe es. Stolz. #ፈለገ ሰላማዊቷ - ሲዊዝሻ። ቅን ነሽ እና ይቅናሽ። አሜን። ነገ 06.07.2024 በጀርመን ዶርቱሙንድ ላይ ሲዊዚሻ ወሳኝ ጨዋታ ልክ 18.00 #ከእንግሊዝ ጋር ግጥሚያ ይኖራታል። መልካሙን ሁሉ ለቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ ዲስፕሊንድ ለሆነው የእግር ኳስ ቲም እመኛለሁኝ። እርግጥ ስጋት አለኝ። ጨዋታው #ከተራዘመ ፤ በተራዘመው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ግብ ማስቆጠር ካልተቻለ #ፔናሊቲ መለያው ከሆነ ስጋቴ ከፍ ያለ ነው። የእንግሊዝ ቲም በጥሎ ማለፋ ጨዋታ የአጨዋወት አርቱ ፈፅሞ አልገባኝም ነበር። ይህም ሆኖ እግዚአብሄር አድሎት ለነገው ፍልሚያ ከሲዊዚሽ ጋር ደርሶታል። ለቅኒት ሲዊዝርላንድ ከስንት ጊዜ #ትዕግሥታዊ #ጥበቃ በኋላ የተገኜ #ዕንቁ ዕድል ነው። ሲዊዝ ለሰው ልጆች ሁሉ የምታበረክተው ታላቁ ስጦታ #የሰላም ፍለጋ መንፈሳዊ ብቃት ለዓለማችን ሰፊውን ድርሻ የያዘ የጎላ ሚናም ነው። ዛሬ ዓለም በሚታመስበት የጦርነት ስጋት ውስጥ የበዛ #ቁጥብነቷ ለግሎባሉ ትውልድ ታላቅ ተቋም ነው ብዬ አስባለሁ። ቅድስት አገር ሲዊዝ ውስጥ የጥይት ድምጽ የማይሰማበት ምድራዊ #ገነት ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የጥይት ድምጽ ሰምቼ አላውቅም። ሌላው ቀርቶ በአዘቦት ቀን ፀጥታው ይደንቃል። እኔ ከቤቴ ውስጥ ሆኜ ነው ራዲዮ ፕሮግራሜን እማሰናዳው፤ አውዲዮም ለዩቱብ ቻናሌ የምሠራው። የምኖርበት አፓርትመንት ውስጥ ጎረቤቶች አሉኝ። #ልጆች አሉ። በአቅራቢዬ ኮሌጅ አለ። ግን #ፀጥ - #ረጭ ያለ ነው። አንዳንድ ቀን የክሪስመስ ዋዜማ ምሽት ይመስል ፀጥታው #በግርማ መንፈስን ይገዛል። እኔ ፀጥታ ነ...