#ፈለገ ሰላማዊቷ - ሲዊዝሻ። ቅን ነሽ እና ይቅናሽ። አሜን። #መልካም #ዕድል ልባሟ ሲዊዝሻ። አሜን።

 

Viel Erfolg.
Ich hoofe es.
Stolz.
#ፈለገ ሰላማዊቷ - ሲዊዝሻ። ቅን ነሽ እና ይቅናሽ። አሜን።
 May be an image of textMay be an image of textMay be an image of 1 person, playing soccer and playing football
 May be an image of 4 people and text
ነገ 06.07.2024 በጀርመን ዶርቱሙንድ ላይ ሲዊዚሻ ወሳኝ ጨዋታ ልክ 18.00 #ከእንግሊዝ ጋር ግጥሚያ ይኖራታል። መልካሙን ሁሉ ለቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ ዲስፕሊንድ ለሆነው የእግር ኳስ ቲም እመኛለሁኝ። 
 
እርግጥ ስጋት አለኝ። ጨዋታው #ከተራዘመ፤ በተራዘመው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ግብ ማስቆጠር ካልተቻለ #ፔናሊቲ መለያው ከሆነ ስጋቴ ከፍ ያለ ነው። የእንግሊዝ ቲም በጥሎ ማለፋ ጨዋታ የአጨዋወት አርቱ ፈፅሞ አልገባኝም ነበር። ይህም ሆኖ እግዚአብሄር አድሎት ለነገው ፍልሚያ ከሲዊዚሽ ጋር ደርሶታል። 
 
ለቅኒት ሲዊዝርላንድ ከስንት ጊዜ #ትዕግሥታዊ #ጥበቃ በኋላ የተገኜ #ዕንቁ ዕድል ነው። ሲዊዝ ለሰው ልጆች ሁሉ የምታበረክተው ታላቁ ስጦታ #የሰላም ፍለጋ መንፈሳዊ ብቃት ለዓለማችን ሰፊውን ድርሻ የያዘ የጎላ ሚናም ነው። 
 
ዛሬ ዓለም በሚታመስበት የጦርነት ስጋት ውስጥ የበዛ #ቁጥብነቷ ለግሎባሉ ትውልድ ታላቅ ተቋም ነው ብዬ አስባለሁ። ቅድስት አገር ሲዊዝ ውስጥ የጥይት ድምጽ የማይሰማበት ምድራዊ #ገነት ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የጥይት ድምጽ ሰምቼ አላውቅም።
 
ሌላው ቀርቶ በአዘቦት ቀን ፀጥታው ይደንቃል። እኔ ከቤቴ ውስጥ ሆኜ ነው ራዲዮ ፕሮግራሜን እማሰናዳው፤ አውዲዮም ለዩቱብ ቻናሌ የምሠራው። የምኖርበት አፓርትመንት ውስጥ ጎረቤቶች አሉኝ። #ልጆች አሉ። በአቅራቢዬ ኮሌጅ አለ። ግን #ፀጥ - #ረጭ ያለ ነው።
 
 አንዳንድ ቀን የክሪስመስ ዋዜማ ምሽት ይመስል ፀጥታው #በግርማ መንፈስን ይገዛል። እኔ ፀጥታ ነው እምወደው። በመኖር ጥበብ ውስጥ ሁካታ ግጥሜ አይደለም። ድብልቅልቅ ያለ ነገር ይጨንቀኛል። ኳስ ጨዋታ፤ ኮንፍረንስ ዲሞን ማለቴ አይደለም። 
 
ሰንበት ሲዊዝ ላይ እጽዋቱ፤ ወንዙ - ተራራው አዕውፋት ሳይቀሩ #በዓዋጅ ዝም በሉ የተባሉ ይመስላሉ። የሚገርም፤ የሚደንቅ የሰላም አቅም ያላት ባዕት ናት ሲዊዝሻ። አውቶብስ፤ ወይንም ባቡር ውስጥ ህፃናቱ እንኳን ጨዋ የሆነ ባህሪያቸው ይገርመኛል።
 
ሌላው ሲዊዝ ውስጥ ተፈጥሮው የበደለው ካልሆነ በስተቀር መንፈሱ እርጋታን ያፈልቃል። ከሁሉም ከጥቃቅኑ እስከ ገዘፈው ክስተት ድረስ ደስታን በሥርዓት ማስተዳደር የመቻሉ ጥበብ ይደንቀኛል። #ደስተኛ ሰብ ከመጠን ያለፈ ነገር አይፈጽምም፤ በሃብት አቅምም እንዲሁ ስኩን የአኗኗር ጥበብ ህይወታቸውን ይመራዋል። #ጥንቅቅ ብለው የሚኖሩ ዜጎች፦ በሚያስገርም #የዴሞክራሲ ዕውናዊ ሁኔታ የተረጋጋ ማህበረሰብ የፈጠረ ስኩን ሲዊዝሻ። የምትመስጥ ምድር።
 
#እዬኖርኩባት #ዘወትር #ትናፍቀኛለች#አልጠግባትም። ዘወትር #እማርባታለሁ። ተፈጥሮን በርጋታ እንዲህ ማኔጅ የማድረግ ጥበብ መታደል ነው። ሁሉም በልክ ነው። ሁሉም ስኩን ነው። ሁሉም ለፈርኃ እግዚአብሄር የሚገዛ ነው። መንፈሱ ይለይብኛል። 
 
አሁን ነገ ጨዋታ አላት ሲዊዝሻ፦ ከቀደመው የአኗኗር ዘይቤ የተለዬ ነገር አታዩበትም። አብዝቶ #የሰጣቸው፤ ለመሰጠታቸው ዕውቅና ሰጥተው በልኩ #በአቅል ማኔጅ የማድረግ ሙሉዑ አቅም ያላቸው ሞዴል ማህበረሰብ።
 
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
(መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፱)
 
#መልካም #ዕድል ልባሟ ሲዊዝሻ። አሜን።
 
ሥርጉተ@ሥላሴ
Sergute@Selassie
05/07/024
#ለሰላማዊት ሲዊዝሻ ድል ይቅናት። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።