"መንግሥት የርዕደ መሬት በታየባቸው አካባቢዎች የጉዳቱን መጠን አሠሳ የሚያደርግ ቡድን ማሰማራቱን ገለፀ" BBC
https://www.bbc.com/amharic/articles/c623m1566m9o "መንግሥት የርዕደ መሬት በታየባቸው አካባቢዎች የጉዳቱን መጠን አሠሳ የሚያደርግ ቡድን ማሰማራቱን ገለፀ" አዋሽ እና በአካባቢው ያሉ ሥፍራዎችን የሚያሳይ ካርታ 4 ጥር 2025, 12:47 EAT "መንግሥት የርዕደ መሬት በታየባቸው አካባቢዎች ከተለያየ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ማሰማራቱን ገለፀ። የመንግሥት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን ቅዳሜ፣ ታህሳስ 26/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ርዕደ መሬቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። መግለጫው አክሎም ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርዕደ መሬቱ በታየባቸው አካባቢዎች ተሰማርተው የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል። በኢትዮጵያ ከ2017 አዲስ ዓመት ጀምሮ በአፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እየተደጋገሙ እና ንዝረታቸውም እስከ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ድረስ እየተሰማ ይገኛል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ መሆናቸውን አስታውቋል።" በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5 ነጥብ 8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ ሲልም ገልጿል። በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ለሊት 9:52 ሰዓት ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍ ያለ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ትናንት ሌሊት የነበረው የመሬት መንቀጥቀጡም በሬክተር ስኬል 5...