ልጥፎች
ከጁላይ 21, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ሰው ኖሯል የሚባለው ምን አድርጎ ሲያልፍ ነው? || ዶ/ር አብርሃም አምሃ እና ገነት አህፈሮም
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። በተለይ ሰውን ማዕከል በማድረግ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። በተለይ ሰውን ማዕከል በማድረግ። እንዴት ነው ሪኮመንድ የሚደረገው? እራስን #በመምረጥ ? የራሱን ከተንቆናጠጠ በኋላ ሌላውን እንደ ሥልጣን #ጥመኛ በማዬት? ለምን? ሌላው እኔ #እመጥናለሁ ወይ ተብሎም እራስ አይጠየቅም። #ፕሮቶኮሉንስ እችለዋለሁን ብሎ ማሰብም ይገባል። አሁን ጠቅላይ ሚር አብይ ንግሥናውን ሲመኙ #ፕሮቶኮሉን ጭራሽ አላሰቡበትም። ለዚህ ነው ብዙ ነገር #ልቅ የሆነው። ይህን የሚከታተል አካልም ያላቸው አይመስለኝም። #ሲነሪቲም አለ ሥርዓት ባለው መንግሥታዊ አወቃቀር። ይህን ጠሚር አብይ ልብ ያሉት ይመስለኛል። #ቀደምቶችን #ይሸኛሉ ። የሳቸውን ተሿሚወች መርጠው #እንዲያመልኳቸው ያደርጋሉ። አዲስ ነገር ፈጥረው። " #ፊልድ ማርሻል" እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። ልቅና በልዕልና የነበራቸው ቀደምት የኢትዮጵያ ጀግና መኮንኖች መ እንኳን ያልተሰጣቸውን ነው የተከወነው። የሆነ ሆኖ መሪነትም እራስን፦ አቅምን እመጥናለሁ ወይ? ብሎ መጠዬቅን ይጠይቃል። ተያያዥ ጉዳዮችም። ሥርጉትሻ 2024/07/20
#ብልጠት እና #ስልት።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ብልጠት እና #ስልት ። በ2014 እ.ኤ.አ በደጉ ሳተናው ድህረ ገጽ ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ነጥቡን አንስቼ ሞግቼበት ነበር። ጽፌበት ነበር። የሆነ ሆኖ ለመቆናጠጫ #ብልጠት ደራሽ፤ ቅጽበታዊ ሲሆን ለእኔ ሳላሞላቅቀው ቁልጭ ያለ #ማጭበርበር ነው። ታሪክም አልቦሽ። መስዋዕትነቱም የገዘፈ አስታዋሽ አልቦሽ የውሻ ደም ሆኖ ቀሪ። ስልት ግን በጠራ ዓላማ እና ፍላጎት የታነፀ፦ በቀነሰ መስዋዕትነት፤ እንዲሁም መስዋዕትነቱን #ዕውቅና #በሰጠ በተደራጀ የሃሳብ #ብቃት በስክነት የሚከወን የአቅም ልዕልና ከፍ ያለ ደረጃ ነው። ስልት የላቀ የሥራ ባህል ጥበብ ነው። የታወቅም // የተሰወረም ታክቲክ እና ስትራቴጂ በጊዜ፤ በሁኔታ፦ በአቅም የሚታሰቡ ትልሞች የሚቀመርበት። አቅም መዋለ ንዋያዊ ብቻ ሳይሆን የሰውን የህሊና እና የጉልበት ችሎታን፦ በተጨማሪም ልምድን፦ ተመክሮን፦ ክህሎትንም ሁሉ ያካትታል። የነፃ አገልግሎትንም ይጨምራል ተመን የለሽ ቢሆንም። ሥርጉትሻ2024/07/20