ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 9, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እልልልልል

ምስል
የመልካምነት  ቤተ -ክብረት! „አግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤  እርሱ ለቅኖች ደህንነትን ያከማቻል፤ ያለነውር ለሚሄዱት ጋሻ ነው፤  የፍርድ  ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል።“  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፮ እስከ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 10.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።               ሃይማኖቴ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሆይ! ኮራሁብሽ! ተመስገን! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቤተክርስትያን „አገር ናት“ ያሉት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በ50 ዓመት ታሪኳ ለአንድ የአገር መሪ ጸጋን ስትሸልም፤ ልቅናን ስታከብር የመጀመሪያዋ ነው።  ይህቺ መከራ ፈተና እና ፍዳ ተልይቷት የማታውቀው ቅድስት ቤተክርስትያን ምን ያህል ከውስጧ የዘለቀ የማስተዋል ጸጋ እንደተሰጣት በዚህ ብቻ ማመሳከር ይቻላል።  ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሰላም አብነት ተቋሙነቷን የረጋገጠችበት ማዕልት ነው ማለት እችላለሁኝ - እኔ። ይህ የክብር ዕውቅና ምርቃትም ነው። ምርቃቱ ለትወልዱም፤ ለአገርም፤ ለማህበረ - ምዕምኑም፤ ለአገልጋዩም ለመልካ ምድሩም፤ ለተፈጥረዊ ጸጋውም ጭምር ነው። ይህ ትውልድ ሆነ ማህበረ ምዕመናኑ ለነፃነቱ ተጋድሏል፤ ሙቷል፤ ታሠሯል፤ ተሰዷል፤ አካሉን አጥቷል፤ ክብሩ ተገፏል፤ ባዕቱን ተነጥቋል። ማንነቱን ተቀምቷል። ይህን ሁሉ ችግር ተሸክሞ ደግሞ አገራዊ፤ ብሄራዊ ግዴታውን ሲወጣ በትጋት ቆይቷል። ሃይማኖታዊ ቀኖናው እና ዶግማው የሚፈቀድለትንም አማኙ ሲከውን ኖሯል። በሃይማኖቱም ተሳዷል፤ ተነግላቷል። ሁሉንም እንደ አዬመጣጡ ታግሶ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዛሬዋ እሸት አንበጥ ዘመን ደርሷል። መልካሙ ነ

ሳተናው ድህረገጽ የ2010 ምርጤ ነው።

ምስል
ምርጤ!                               "ጥበብ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።                                በሃይማኖት ስማቸውን ላስጠሩም ሰዎች ትንቢትን                                  ታስተምራለች፤ ወደ ነብያትም ምሳሌ ታገባለች።                                    የተሠወረውንም ምሳሌ ትመረመራለች፤                                      ንባቡንም ወደ ትርጓሜ ትመልሳለች።“                                  መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ከቁጥር ፩ እስከ ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.09.2010 ከጭምቷ ሲዊዘርላድ።  የሳተናነት ማር ወለላ አዎንታዊነትን ሲያበላ የቅንነት ነፃነት ገላ የቤተ አብርኃም ፍሬ ዘለላ የጥሪት ቅኔ ፈርጣዊ ዛላ። የሁለመና ህብረ ዜማ ረቂቅ የሁለንትና ነባባተ ብርቅ የተግባር አናባቢ ንዑድ ድንቅ ሳተናው አንደስምህ ወርቅ! ሳተናው ድህረ ገጽ ለቀንበጥ ብሎግ የ2010 የዓመቱ ምርጥ ሚዲያ ነው። ምርጥነቱ ቅንነቱ፤ አሳታፊነቱ፤ አቃፊነቱ እና ሚዛናዊነቱ ልዩ ጣዕም ያለው፤ እውነት የፈለቀበት ከመሆኑ ላይ ነው። ሳተናው ድህረገጽ የሃሳብ ሙግቶችን ያለ ተዕቅቦ የሚስተናግድ  ለኢትዮጵያ የሚዲያ ህይወት እና ታሪክ አዲስ በር የከፈተ ልዩ የሚዲያ ነፃነት ምዕራፋችን ነው። ሳተናው ደፋር ነው። ድፍረቱ ሰውነትን በመቀበል እረገድ ነው። እኔ እንደ እሱ ሰውነት የሚቀብል ሚዲያ አይቼም፤ አድምጬም አላውቅም። ሁሉ በተመሠረተብት ማንነቱ ወይንም ዞጉ ላይ የተመሠረተ ነው። ሳተናው ድህረ ገጽ ለጥብብ ያለው ክብር እና