ልጥፎች

ዕብለት ተደርሮ።

ምስል
ምሬት። „ቃልህን ወደ ደመናት ታነሳ ዘንድ ትችላላህን።?“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፴፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።                             ልታነጋ የመሸብህ … የሞት ቀጠሮ በስሌት ተቀምሮ ነገን አሳምሞ በሃሞት ተሮሮ ዕውነትም ተማሮ እንዲህ ተክኖ አሮ የሽንገላ አውራ ዶሮ፤ ስላቅን ሰንዝሮ የዝበት መርዶን ድሮ የዕብለት ድርድር በቀረርቶ ተደርሮ። https://www.youtube.com/watch?v=AhlL80R74h4 Ethiopia: የኢንጂነር ስመኘው ሞት ዝርዝር የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ !! [ እራሱን አጠፋ ?] ድንቄም ስንታዬን መግለጫ፤ ለኮሜዲነት ይልቅ ይመቻሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ …. ·        ሥጦታ ለምስክኔታ ሙያዊ የሚዛን ርትህ። ዕውነት ስተፈጠር ማዬት ሽው አለኝ።  

የችሎት ህልፈት...

ምስል
              እስከ ህልፈት ያልቀጠለ የዜግነት ክብር …       የችሎት ህልፈቱ። „የሰጎን ክንፍ በደስታ ይንቀሳቀሳል፤ ነገር ግን ክንፍና ላባዋ ጭምተኛ ነውን?“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የችሎት ህልፈቱ መውደቅ ብልሃቱ የችሎት ንቅዘቱ በዕብለት መፈታቱ የችሎት ጭላጩ ዕውነት መደፋቱ የችሎት ራህቡ ሚዛን ማጣፋቱ የችሎት ጥማቱ ጠያቂ ማጣቱ። ·        ሥ ጦታ ርትህ ለጠማት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ይሁንልኝ። መኖርን ያከበረ ዘመን ይናፍቀኛል። የኔዎቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።

በልጥ መወራረድ? ህም - እም - እህ!

ምስል
ዕውነትን የሚገልጸው ዕውነት እራሱ እንጂ ዓዋጅ አይደለም። „እያሱም ህዝቡን፤--- እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፤ እርሱ ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሄርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላላፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።“ መጽሐፈ እያሱ ወልደ ነዌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፲፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ባለወረፋው ቆፍጣናው ጎንደሬ! ·        ልብ ሊሰጠው የሚገባው የዕውነት አደባባያዊ ፍርድ - በልጥ ተወራረደ። https://www.youtube.com/watch?v=AhlL80R74h4 Ethiopia: የኢንጂነር ስመኘው ሞት ዝርዝር የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ !! [ እራሱን አጠፋ ?] ድንቄም ስንታዬን መግለጫ፤ ለኮሜዲነት ይልቅ ይመቻሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ …. ከአብይ ሌጋሲ የማልጠብቀው እንግዳ ነገር ነበር መግለጫው። የግፍ ችሎት ነበር ፍርዱ። ደመከልብ። ልክ እንደ ፕ/ እምሩ ስዩም። እሳቸውም ተከሳሽ አልነበራቸውም። ችሎቱን ሰጪው ሞት የግፍ ብቻ ነወብ። የሆነ ሆኖ በቆሞስ ስመኘው በቀል አሟሟት ከጅምሩ ሂደቱ የሰጠኝ ጭብጥ ግብረ ምላሽ ቢኖርም ትንሽ ብጣቂ የሚመስል ተለጣፊ ማሰተባባያ ጠብቄ ነበር ግን በረዶ ለቀቀበት። እግዚኦ! ብላለች ልዩ የመንፈስ፤ የታማኝነት ወዳጁ ሥርጉተ ሥላሴ በዘመነ አብይ።  … ከአብይ ሌጋሲ ታማኝነቱን የሚያሰተጓጉሉ ለጠፎች ቁሮዎች ወይንም ቀዳዳዎችን ማድመጥ አልሻም።  እርግጥ ነው ፍጽምና አልጠብቅም፤ ግን በዜግነት እኩልነት ላይ ድርድር አላውቅም። ሲሶ እርቦ ዜግነት መሮኛል፤ ተመልሰሽ ያን ከርቤ እና ሃሞት ተጎንጪ ደግሞ ህልፈቴን መራራ ያደርገዋል። ሞትን ፈርቼው አላውቅም፤ ባሰኘው ቀን እንደሚመጣ ስለማውቅ ተሰናድቼ ነው እምጠብቀው

ሌላስ? ህም ተዚህ፤ ህም ተዚያ፤ ህም ተዚያ ማዶ!

ምስል
  ጭላጭ ሳይስቀሩ …  እም እንዳይሆን ስለ ጸዮን ዝም አልልም፤ ስለ እየሩሳሌም ጸጥ አልልም፤  ጽድቅዋ እንደ ጸዳል፤ መዳናዋም እንደሚያበራ  እስኪወጣ ድረስ።  ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፷፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የሚገርሙኝ ነገሮች የበረከተበት ወር ነበር ነሃሴ። ብዙ ብርካታ የሚባሉ ጉዳዮችን አስተውያለሁኝ። ዛሬም እንደ ትናቱ የሞገድ ጉጉሱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ትልቁ ጥያቄ ግን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው ለእኔ ለህሊናዬ ቅርብ የሆነው፤ ዕውን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ ትልቁ አምክንዮ ነው - ልንዘናጋበት የማይገባው። እርግጥ ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ አንድ ክንፉን ተመቷል ከሰሞናቱ። ችግሩን ከእርሱ ብዙ ማይልስ ርቆ መሬት ሲያስነጥስ፤ የራሱንም ህዝቤ የሚለውን ዕንቁውን ሳያስጨንቅ  በዕንባም ሳያሳጥብ "በሞኝ ክንድ" እንዲሉ መፈተኛው ሌላ ቦታ ነው፤ የምስራቅ ኢትዮጵያን ህዝብን ሲያስለቅስ የቆዬበት ሁኔታ የመፍትሄ አሰጣጥ ዘይቤን ብዙ ሰው አላስተዋለውም፤ ልብም አላለውም፤ አላደነቀውም፤ ዕውቅና ለመስጠት አልደፈረውም እንጂ የኢትዮ ሱማሌ ጉዳይን መስመር ለመሳያዝ የተሄደበት መንገድ እጅግ ዘመናዊ፤ ስልጡን ብቻ ሳይሆን እምነት የሚያስጥል ነው። ዶር አብይ አህመድ የመጨረሻውን የእውቀት ደረጃ ያዋዋሉበት ሙያ የሰላም እና የደህንነት ነው፤ ጥበብ መሬት ላይ በውን በዳግሚያ ትንሳኤነት እንዲታይ የተደረገበት፤ ከተከናወኑት ግዙፍ አገራዊ ጉዳዮች እንደ አንዱ ሊታይ የሚገባው ነው በሥርጉተ ዕድምታ። ልክ እንደ ኢትዮ ኤርትራ። እውነት ለመናገር በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን መሰል የመንፈስ ተረገጥ ልዕልና ይገኛል ብዬ አስቤ አል