Shaqiri und Xhaka, Stolz!
Shaqiri und Xhaka, Scholz! ሻካና ሸኪሪ ኮራሁባችሁ! ከሥርጉተ© ሥላሴ 22.06.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። "እግሮች እንዳይናወጡ አረማማዴን በመንገድህ አጽና።" (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፭) ጭመቷ ሲዊዝ ዛሬ ጭምትነቷን ገፋ አድርጋ መኪኖች ሁሉ አደባባይ ወጥተው ሙሻረውን ድል እንኳን አገኘህን እያሉት ነው። ደግነቱ ቀኑ አርብ ነው። ህዝቡም በዬበረንዳው በዬመስኮቱ ሆኖ እያጀበ ነው። ሲዊዝ ድብልቅልቅ ብላላች አልልታ በእልልታ እሰዬ … የሲዊዝ ህዝብ የሞራል ልዕልና እኮ የተለዬ ነው። ሱቅ ላይ ቀላል ዕቃ ከያዛችሁ በርከት ያለ ዕቃ ለመግዛት የተሰለፈው ያሳልፋችሁዋል። ከዬትም አገር ቆይታችሁ ሲወዝ ስትገቡ ሻንጣ ማውረድ ካቃታችሁ ይረዱችኋዋል። ልዩነቱን በደንብ ታዩታላችሁ፤ ሌላ ቦታ እኮ ትዝ አትሏቸውም፤ ሲዊዝ ግን ጠረኑ የተቀደስ ነው። እናቶች ህፃናትን ጋሬ ይዘው ብቻቸውን ባቡር ላይ አያወጡም አያዋርዱም። ባልተፃፈው ህጋቸው የተከለከለ ነው። መኪና ያላቸው ከሌላ አገር ወደ ሲዊዝ ሲገቡ ቀድመው እንዲሄዱ ይፈቅዱላቸዋል። ዲታውም ደሃውም ራሱን ዝቅ አድርጎ ምንም የሌለው መስሎ ይኖራል በልክ። ሁሉም ነገር በደንበር እና በዝምታ ውስጥ ነው … ለጠብ አይተጉም። ዛሬ የምር ከልቤ አለቀስኩኝ። እዚህ ከኖርኩበት ዘመ...