ቅንነት ሲከብደን ተስፋችን እዬራቀን ይሄዳል!

ቅንነት ሲከብደን ተስፋችን እዬራቀን እንደሚሄድ ልብ አላልነውም።
ከሥርጉተ ሥላሴ 22.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)



„በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራዕይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እንሆ እዬበረረ መጣ፤ 
በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።“ (ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፳፩)

„የ40 ቀኑንም መንገድ 40 ዓመት አታድርጉት። የባለቅኔው ጠ/ሚር አጽህኖታዊ ቃለ ምህዳን።

እንዴት ግን ይክበደን ቅንነት? ተሸከሙኝ አላለም እኮ። እዘሉኝ አላለንም እኮ። እቀፉኝ አላለንም እኮ። አሽኮኮ አድርጉኝ አላለንም እኮ። ቅንነት አይከፈልበት፤ አይወጣ አይወረድበት። ወረፋ አይጠበቅበት። ውቅያኖስ አይሻገሩበት። ራሽን አይመደብበት ግን ስለምን ከበደን?

ግን እኛ ስለሰው ልጅ ስንፈጠር፤ እኛም ሰው ናችሁ ስንባል ግን ስለምን መልካም ነገርን መድፈር ተሳነን? ቅን ብንሆን ምን ይቀርብናል? ሰዎች ሲገናኙ ጨጓራችን አቃጥለን። ሰዎች ሲሰባሰቡ አንጀታችን ቆርጠን። ሰዎች የውስጥ ሰላማቸው ሲመልስ ራስ መርዘናችን ተነስቶ ግን እኛ ምንድን ነን?

እውነት ለመናገር የእኛን ህዝብ ከመምራት ምን እንደሚሻል መድፊያውን ጨረሱልኝ በሥርጉተ ሞት።

አንድ ቅን ባተሌ በሥንት ዘመን ኢትዮጵያ በቃሽ ብሏት ፈጣሪ አምላክ፤ በዚህ በተዘባረቀ ውጥንቅጡ በጠፋበት ጨቀጨቃማ ዘመን ሙሴ ሰጥቷት ለሁሉም በቃሉ መሰረት ልቡን ሸልሞን፤ ህሊናውን አብርክቶን፤ ወጣትነቱን ሰጥቶን፤  እኛ ግን የሰጠንን ቅንነት መልስን መመገብ ቀርቶ ቅንነቱን ማድመጥ ተሳነን። በቃኝ እንደፈለጋችሁ ሁኑ ቢለን ምን ልናመጣ ይሆን? መከራ፤ ስቃይ እንደ ገና ናፈቀን። የሰቆቃ ጊዜ እንደገ ና እራበን? የዕንባ ዘመን እንደ ገና ናልን ብለን ስንት እርብራብ መሰናክል ደረድርን ግን የእውነት እኛ ምኖች ነን?

አሁን የሲዳማ ህዝብ የኢትዮጵያ ማዕከል በተባለ ማግስት ያደመጥኩት ነገር እጅግ ይገርማል። እሳት የለበሰ፤ እሳት የጎረሰ መንፈስ በፌስ ቡክ ሰራዊት የተጀበጀበ ጦርነት ነበር የታዬው። ጠበንጃ ቢገኝ ቅንነት ተደብድቦ በሞተ ነበር። ተወግሮ በመዶሻ ነፍሱ ባላፈ ነበር። በደቡብ ህዝብ አቀባበል ስንቶች እንደ ቀኑበት እነሱ የት አውቀውት? እነሱ የት አዳምጠውት? ለዶር አብይ አህመድ ሌላ ቦታ ላይ ቤተሰቦቼ የተከፉበት አቀባበል ስለ ነበር ካሳን አዋሳ ነበር ያሉት በአዋሳ ኮራን ነበር ያሉት።

ሌላው ይቅር በስንት ዘመን ህዝብ እና መንግሥት እንዲህ ሲገናኝ ሁሉም ጦሩን፤ ጋሻውን፤ ስለቱን አንግቦ መሆን ነበረበትን? አሁን እኮ የሱባኤ ጊዜ ነው መሆን የነበረበት። ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ሲሰጣቸው እኮ በሱባኤ ነበር የተቀበሉት። አሁን እኮ ለተዋህዶ ልጆችሐዋርያት መታሰቢያ ጾም ላይ ነን። ስለምን የፈጣሪ ጸጋ በረከት ረድኤት ካልተጠቀሙበት ስለሚተን፤ ስለሚበን።

አሁን ይህን የመሰለ ቅዱስ መንፈስ መግፋት፤ መገፍተር፤ ሰባራ ሰንጣራ እዬፈለጉ ማስከፋት ይፈለግ ነበርን? እኔ በአንድ በኩል ደስ ሲለኝ ችግርን ቅንነት ለማድመጥ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ እናት ብር ብሎ መሄዱ፤ መፍቀዱ ወላፈኑ ግን ይጋረፋል። ይከረፋል።

እንዴ ምን ግድ አለባቸው / ሚር አብይ አህመድ። ፍዳቸውን ከፍለው ያሳደጓቸው እኮ ቤተሰቦቻቸው ናቸው። ቅንነት እንዲህ ከብዶን 27 ዓመት የተጨራረስንበት ያልጠቀመንምየነፍጠኛ ፖለቲካስሰማ ተጸዬፍኩት። ማስጠጋት አልቻልኩም። በዚህ ፖለቲካ ማን አተረፍ? ተጎዳ የሚባል ማህበረሰብ ካለ አማራ ነው፤ ግን የሰማይ ጽድቅ ነው። ሰማዕትነትም ነው። ሁሉም በዬተራ ድርሶታል። ይህን ዕድል ብናሾልከው ሁሉም በዬተራው በእጥፍ ድርብ ይደርሰዋል።

እኔ በዚህ ጉዳይ 2013 ጽፌበት ነበር። ዘሃበሻ ተባብሮኝ አውጥቶልኝም ነበር። የሚቀር የለም ብዬ። እንዲያውም ያን ጊዜ የጥቁሩ ሰው ካሴት ያነገግር ስለነበረ ያልተጠበቀ መከራ ሊያመጣ ይችላል፤ ትምህክት ጥሩ አይደለም ብዬ ሁሉ ሌላም ጽፌ ነበር። እግዚአብሄር ቅጣቱ ረቂቅ ነው። ለሃጣን የመጣው ለጻድቃን መሆኑ ደግሞ ልብ ልክ ነው።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሆነ ልግመኛውን የኢትዮጵያ የሴራ ፖለቲካ አታውቁትም። በፍጹም አታውቁትም። ለነገሩ አሁን እኮ ፖለቲካኛ ነኝ ለማለትም ማፈር አለበት ሊሂቁ ሁሉ፤ ተንታኙ ሁሉ ጋዜጠኛው ሁሉ ዛሬን ቀድም ለማዬት አልተቻለም ነበር። ብዙ ዝርክርኮች ነው የነበሩት።

አሁንየነፍጠኛ ፖለቲካመንፈሱ እንደገና በዚህ ዘመን መደመጥ ነበረበትን? „አኖሌ“ ሲነሳ እንዴት እኔ እንደምቃጠል። ቅንነትን ተጋፊ ነገሮች ሁሉ የዲያቢሎስ ስለሆኑ። እግዚአብሄር የለም ብሎ የሚያምን ንድፈ ሃሳብ ነው „የነፍጣኛ ፖለቲካ“። እግዚአብሄር የለም ብሎ የሚያምነው ደግሞ ሰውም ተፈጥሮም አጀንዳው አይደለም። አማላኩ፤ ታቦቱ፤ ጸበሉ፤ መስቀሉ፤ ጸሎቱ ድዋው ወረቅት ነው። ወረቅት ደግሞ ሲያጋድል የኖረ የፍዳ ጦሮ ነው። አብሮነትን በ“ቸ“ እና በ“ሸ“ ሲበትን የኖረ የመከራ ዘመን ነው። ተሰደን እንኳን መከራችን በልተን ነው የምንኖረው።

በዛ „በነፍጠኛ ፖለቲካ“ ብጥስጥስ ብሎ የሚገኝ ተረፈ ምርት ከኖረ እኮ ታይቷል። በቀን 700 ሺህ ህዝብ መፈናቀል። በቀን 600 ሬሳ በአቧራ ልብስነት ማፈስ በቃ ይሄው ነው ትርፋችን። የውስጣችን ሃዘን እና የፊታችን ገጽ ብታዩት ይህ ሰው፤ ይህቺ ሴት አውሮፓ ይኖራሉን ነው የምትሉት። በአንድ ቀን ያቺ የፈረደባት እና 600 ልጅ ሬሳ ሰትረከብ። እንደ ወጣ/ እንደ ወጣች ስትቀር ሙሽራዋ። መከራ ግን ስለምን ይናፍቀናል? ግን እኛ ሰው ነን? አሁን ወ/ሮ ታደሉን ያዬ ያነን ይመኛል። የነቀምቱ ጉዞ እኮ ያን ቀጥሉልን ነው። ማስተዋል የሚባል ነገር ሰርቶልን ግን ልንጠቀምበት አልቻልንም።

ቅን መሆን ነገሮችን በቅንነት ማዬት ሊሂቁ ይነሰው እንዴት ህዝብ በወል በቅንነት ላይ ያድማል። እንዴት ህዝብ በቅንነት ላይ ፊቱን ያዞራል። የት ነበር እስከዛሬ በጅማለ ዘመነ ሞት፤ በጀምላ ዘመነ እስራት። አሁን ዶር አብይ አህመድ ለ27 ዓመት መከራ ተጠያቂ መሆን አለባቸውን? ማተበ ቢስነት። ገና እኮ ሦስት ወር እኮ በወጉ አልሞላቸውም። ቀን ስንቆጥር አስረኞች ሳይፈቱ ሰከንድ አለፈ እያልን ስናጣውር አልነበረንም? እከሌ ቢዛ ተከለከለ እክሌ ትክት ተነፈገ ...  አጀንዳ ጠፋ አሁን ደግሞ አዲስ አጀንዳ „ክልል“ እንሁን ነው። ይሄ ሳቢያ እንጂ ምክንያቱ ሌላ ነው። ስንተዋወቅ ነው። ጀብጃቢው ማን ስለምን እንደ ሆነ ይታወቃል።

ይህን የገዘፈ መከራ አሳልፈው ያሸጋሩ በዬነጥብ ጣቢያው ፌስ ቡክ የፈጠረውን የእኔ እብልጥ የእኔ በልጥ የኮፒ ራይት ሽሚያ የሚፈጥረውን ፉክክር ለማስታገስ ይሯራጡ። በዬደራጀው እኮ መሪ አለ። በዬደራጀው እኮ አካል አለ። ዛሬ አድማጭ አለ። በወጉ በሥርዓቱ መጠዬቅ ይቻላል። መላ ጠፋ …
 
ወያኔ የሚሠራውን ሥራ እዬሠራህ ወያኔን ታወግዛለህ። በምን ሞራል? በምን ህሊና? አንተዋወቅምን? መጀመሪያ በእጅ ለላው ቅንነት እጅ እንንሳ፤ ከውስጣችን እንለወጥ። ከነዘለበው የክፋት፤ የምቀኝነት፤ የሴራ ሸንኮፍ ጃኬታችን ጋር ይህን ንጹህ አብያዊ መንፈስ ለመቀላለቀልም አንሰበው።

 መሆን አለመቻል ነው ሲያጓጉሰን የኖረው። አውንተኛም እንሁን። ውሸት አታጋያችን አይሁን። ለነገሩ ለውሸት ካደረ ቅነነትን ላምጣው ቢባል እንዴት ብሎ። ዝርፊያ የገንዘብ ብቻ አይደለም የታሪክ ሽሚያም ዝርፊያ ነው። ሌቦች የፍቅረ ንዋይ ጥመኞች ብቻ አይደሉም። የሥም እና የከንቱ ውዳሴም ጃንደራባዎች ሌቦች ናቸው። የሌላቸውን አለኝ እያሉ ሲያታኩሱ በስደት ላይ እንኳን ኢትዮጵውያኑን ሲበትኑ የተነሮበት በዬለም የተባዛ ፖለቲካ የመንፈስ ሌብነት ነው ለዛውም ቅንነት የጎደለው።

ቅን ለሆነ ሰው ውሸትም አያስፍልገውም፤ ሸርም አያስፍለገውም፤ ሴራም አያስፈልገውም፤ በሰው ደም እንድርቺ እንድርቺም አያስፈልገውም፤ ቅን ሰው ንጹህ ውሃ ነው። ቅን ሰው ቅኖችን ለመቀበል የቁጥር ተማሪ፤ የፍልስፍና ዕወቅት አያስፈልገውም። ቅን ሰው ቅደመ ሁኔታ አያስፈልገውም። ከዬትኛውም የሰው ዘር ቅን የሆነን መንፈስ ለመቀበል የሚችለው ቅን ሰው ብቻ ነው። ለቅን ሰው ደንበር የለውም። ቅንነት ለላቸው ሚደያዎች፤ የጥበብ ሰዎች በሩ ክፍት ነው ቅን ከተሆነ። ህሊናው ለመማር ዝግጁ ስንዱም ነው። መፈረጅ የቅንነት ደሃዎች ዕለታዊ እስትንፋስ ነው።
  • ክውና ለቅኔዎቹ ቅኖቼ!

የለማ ገዱ አብይ አንባቸው መንፈስ አገር ሽው እንድትለን ያደረገው በተስፋ ጣዝማ ነው። ዛሬ ለህትም ከበቁት ግጥሞቼ በ2005 እ.ኢ.አ በጸጋዬ ራዲዮ የሰራሁትን ስዳዊ ግጥም በድምጽ አሁን ፖስት አድርጌዋለሁኝ። እርግጥ ያን ዕለት የስትዲዮ በር ብልሽት ገጥሞት የቢሮ ድምጽ ቀልቤን እዬሰረቀው ስለነበር የድምጽ ምት ውጣ ውረድ፤ የፈደል ግድፈት አለበት። ለዚህ ታላቅ ይቅርታ እዬጠዬቅኩኝ ግን ትዝታን በምልሰት ጋብዠችሁአለሁኝ - ለቅኖች። 

ቅኖች አገሬ መሬት ላይ ስለበረከቱልኝ ደስታዬ ዳርቻ የለውም። ነፍሴ በሐሤት ሰገነት ፈርሻለች። እናም ነው ዳውን ሎዱ ረጅም ጊዜ ቢፊጅም ግን ታግሼ ፖስት ያደረኩት -ዛሬ። ለግድፈቶቼ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ በትህትና። ይሄውና ምርኩዙ ዘንከት ባለ ኑሩልኝ ምስጋና ታክሎበት መልካም የትዝታ ጊዜ እንሆ … 

ናፍቀሽኝ አገሬ።


8ቀን ለሚባክን ሙሴ ቅን እንሁን!
የማነውቀው አገር አይናፍቀን!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።