ልጥፎች

ከጁላይ 3, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

፬ቱ ባለ፬ ዓይናማ ኢትዮጵያዊ ልቅናወች። (ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ፥ ዶር እንዳወቅ ይዘንጋው፣ ዶር. ጥላዬ ታደሰ፣ ዶር....

ምስል

#መሻቀል ይታገት።

ምስል
  #መሻቀል ይታገት። "ትካዜዬ ሁሉ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬ ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ! ከባህር አሽዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና፤ ስለዚህ ቃሌ ደፋር ሆኗል።" (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፩ - ፫)     የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘሃ ግራው መሻቀል ነው። ስለዚህም ደንጋጣ እና ያረገረገም ነው። ቱማታ እና "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል" የሚሉትም ዓይነት ነው። ስለሆነም ውድቀቱ እንደ መድህን ቆጥሮ ቸበለው ይለዋል። የሚለው ግን አውሎ የሚያሳድር በቂ ኦክስጅን የለውም። በጥቁር ቀን ተከቅልሎ ጢስን እዬመገበ በቀውስ በጀት የሚተዳደረው ኦነጋዊው የ፬ ኪሎ ቤተ መንግሥት ድል ቀንቶኛል ሲል ዓዋጅ ያስነግራል። ይህም ብቻ አይደለም ከሁሉም አለሁ በሚለው የዝልኝዲፕሎማሲያዊ ጉዞም ትርፋማ እንደሆነ ይዘባበታል። በምንምመለበጥ፤ በምንምወጌሻ ሊጠገን የማይችለው የፋንታዚ ጉዞ ወፈፌ ነው። ዕለታት የሚሻቅሉት። መሻቀል ዬአለመርጋት ምልክት ነው። በሁለገብ የታቀደ ጥፋት የዳነም የተገነባም አገር የለም።   የማድመጥ አቅም የሚጠይቀው ብሄራዊ ብቻ ሳይሆን አህጉራዊዓለማቀፋዊምነው። አንድን ውድቀት ለማከምሌላ ውድቀት በማጨት የሚገኝ የተረጋጋ ሥርዓት አይኖርም።   በትንሽ የእፎዬታ አዬር ሚሊዮን ትእቢትን ፀንሶ መንጎድ እራስን አጉብጦ ከማሰናበት ውጪ ትርፋማ መንገድ አይደለም። ለኦነግ ፖለቲካ ኢንትሪግ፤ ማምታት ዶግማው ነው። ይህን ግን ለቀኑ ቀን ሲሰጠው የዶግአመድ ይሆናል።   እንኳንስ ተጠማኙ የኦነግ ፖለቲካ በራሱ ዛቢያ ተመሥርቶ እራሱን ለመራ ስኩን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞችም ይህ ዲጅታል ዘመን ፈታኝ ነው። ሥርዓት የገነቡ አገሮች ምን ያህል ፈተና ውስጥ እንዳሉ እናያለን።   መከራውን ችሎ ያለው ከሊቅ እስከ ደቂቅ መቻል የሰጠው የኢትዮጵያ ህ

በማምሻ ከብት ግባት ጀንበር ስታዘቀዝቅ ምዕራፍ ፲ን አህዱ አልኩ። - ምን አጉደልን? ቀጣዩ ጭብጤ ይህ ነው። (ምዕራፍ ፲)

ምስል
በማምሻ ከብት ግባት ጀንበር ስታዘቀዝቅ ምዕራፍ ፲ን አህዱ አልኩ። - ምን አጉደልን? ቀጣዩ ጭብጤ ይህ ነው። (ምዕራፍ ፲) ክብሮቼ እንዴት ናችሁ? እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት አላችሁ?      በሲቃ ነው እምጥፈው። እምነግራችሁ ተረብ እንዳይመስላችሁ። ዕንባ - ይተናነቀኛል። ሳግ - ይፈትነኛል። ሆዴን ባር ባር ይለዋል። ልቤ #ይሻቅላል ። ትርታዬ - ይጨምራል። ትርታዬ - ቁርጥ ቁርጥ ይላል= መቼ እና መቼ? ዜና ላደምጥ ቴሌቪዢኔን ስከፍት። የምነግራችሁ ዕውነት ነው። በጣም ደንጋጣ ሁኛለሁኝ። የሚፃፋ፤ የሚዘገቡ፤ የሚደመጡት ሁሉ ያስፈራሉ። እኔ በእኛ ዘመን ያበቃል ያልኩት የጦርነት ሲቃ ዛሬም??? ህልማችን ተስፋችን የዕውቀት ጥማታችን በሰላም እጦት ጨንግፎ ቀረ እንደ አቀረቀረ ስለ እኛ እኛን ስለአጣ። ዛሬም??? ያማል። የሚያጽናና የሚያረጋጋ አይዟችሁ የሚል መንፈስ ክው ብሎ ደርቋል። የዜናወች ዕርዕስ ቀለም፤ የቃላት ምርጫ ሁሉ ያስደነግጣሉ። የሚፃፋበት ቀለም እራሱ አለርም። ህም። እናም ቁጭ ብዬ እራሴን ስሞግት ሰነበትኩኝ። አልፎ አልፎ ብቅ እላለሁ። ግን ውስጤን የሚጨነቅበትን ነገር ለመፃፍ አቅም አጣለሁ። በፍጥነት ግጥምጥሞሹ ይደመጣል፤ ፍጥምጥሙ ሳይከወን ፋክክሩ አና ይላል። በዚህ ማህል ትውልድ ይባክናል። ምጥ። በወል ውርጅብኙ በረዱን ይለቀዋል፤ አውሎውን ይልከዋል፤ አቤቶ ስክነት አቤት ያንት ያለህ የእኛ ጌታ የህዝብህ እንባ ሆነ ከርታታ እያለ ወደ እዮር ሲጮህ ይሰማኛል። ፍጥነቱ፤ እሩጫው፤ ጥድፊያው ከዬት ተነስቶ የት እንደሚከነዳ ይፈትናል። ፈተና ለፈተና ግብዣ ሠርግ እና መልስ፤ ግጥግጥ እና ቅልቅል። #እህ ። ልርገመው _ እላለሁ። ልውቀሰው _ እላለሁ። ልቆጣው _ እላለሁ። ለዚህም አቅም አጣለሁ። ልርገመው፤ ልቆጣው፤ ልገስፀው የምለው ባላወቅኩት፦ ከእሳ

ምን አጎደልን? ከምንስ ጎደልን? ምንስ ይሙላው? ለመሙላትስ አቅሙ አለን ወይ?

ምስል
  ምን አጎደልን? ከምንስ ጎደልን? ምንስ ይሙላው? ለመሙላትስ አቅሙ አለን ወይ? "ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ!" (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፪) እንዴት አደራችሁ ውድ ቤተሰቦቼ?       ፱ኛው አሳቻ ዘመን ይቃኝበታል። ጥበብ በሙሉ አቅሙ ዝም እንዳይል ስጋት ስለታወጀበት። ጥበብም ዴሞግራፊ ይሠራበታል የሚል ምፅዓት ያለው ዘመን ተደርሷል። መኖር ዴሞግራፊ፤ መኖር የሰጣቸው ገፀ በረከቶች ሁሉም በጥላቻ ተፈርጀው ነቀላ ላይ ላለው ዘመነ አሳቻ መትከል ሳይሆን የተተከለን መንቀል ቀላሉ ድርሻዬ ብሎ ተያይዞታል። የሆነ ሆኖ የእነኝህ የጥበብ በዝምታ ተጋድሎ ጉዳይ የት ደረሰ? ከመድረኩ አሉ ወይንስ እንደተሰወሩ ይሆን? ዝም ማለት፤ ፀጥ ማለት፤ ጭጭ ማለት በማይፈቀድባት ኢትዮጵያ ጥበብ ተለጉመሽም ገጽሽን ዓይን ላፈር የወፈፌወች የባንድ ኳኳቴ ነው። እነሱ ፍርሻ፤ በደል፤ ጭንቅ አምርተው በማከፋፈል ላይ ሲሆኑ፤ ይህ አልተመቸኝም ያለችው ብጡሏ ጥበብ ደግሞ ባይሆን ግንባሬ ወክ ያሰኜዋል፤ እጄም አቤቱታ ስትል ታገደች። የአገዷት ኮሽ ባለ ቁጥር ድንግጥ ድንግጥ የሚሉት የዓለሙ የሰላም ሎሬት ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ጠረኑ የእኔን ፍርሻ አቤት ወዴት የሚል አዲስ ብይድ ቋንቋ ጥበብሻም ታምርት ዓይነት ነው። በዝግ ውስጥ ትንሽም አዬር አይግባ ብሎ የበዬነው ኦነጋዊው አስተደዳር ምን ሲባል ሞትን፤ መጎዳትን፤ የባሩድን እሩምታ ታሳጣላችሁ ሲል ባሳዬው ቁጣ እንሆ አዲስ አደዮችን ማዬት እንዳይቻል የቅበር ተልዕኮውን ከውኗል። ይህ ዘመን ሁሉንም ነቅሎ ልስን ባዕዳዊ ልጥፍ ለመለጣጠፍ አና ብሎ በጀመረው ዘመቻ በ፭ ዓመት ዬ50 ዓመን ፋንታዚውን እያሳካ ነው። አቶ ሽመልስ አብዲሳ በ2014 ዓም በነበረው የሬቻ ዋዜማ ላይ የተሰጠንን 5 ዓመት በ5 አባዝተን የ25

ባለ #ንቃቃቱ ቀንበር። መሪነት ትራጀዲ ወይንም ኮመዲ ወይንም ሲቃ፤ ወይንም የኳስ ሜዳ አይደለም።

ምስል
  ባለ #ንቃቃቱ ቀንበር። መሪነት ትራጀዲ ወይንም ኮመዲ ወይንም ሲቃ፤ ወይንም የኳስ ሜዳ አይደለም። "መከራዬ ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!" (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፮፮ ቁጥር ፪)     ቀንበር የሆነ ሥርዓት ቀንበሩን እንደ ድሎት ብቻ ሳይሆን እንደ ክብር ቆጥሮ ሲንከላወስ፦ ቀንበሩ የጫነው በራሱ ላይ ስለመሆኑም ያመላክታል። ቀንበር ጫኞች ቀንበሩ እነሱንም እንደሚያካት አለማወቃቸው የቆባ እኩይነት ነው።   #ግን ። ማስተባባያው ተምን ይመደብ።?።    ይህ ክብር ሆኖ አንገትን ቀና አስደርጎ ጉዟችን ትርፋማ ነበር የሚያስብል ነበርን? በሂደቱ እና በክስረቱስ ፌስታ የሚያስቀምጥ ነበርን? ወይንም ውርዴቱ እንደመዳሊያ ሊያስቆጥር ይገባ ነበርን?   #ዝም #ብዬ ።   ሁሉንም - አዳመጥኩኝ። ሁሉንም - መዘንኩት። ሁሉም ለሁሉም እራስን ማድመጥ ያቃተው ስለመሆኑ ገባኝ። #ግንን ልድገመው። አዎን ግን ሁለት ጊዜም ከፈረንሳይ ጉዞ መልስ ቀውስ ማስከተል ………   የዛሬ ሦስት ወር ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በደም አላባ በጽልመተ በኦነጋዊው የሲኖዶስ ግልበጣ የመንንግሥት ውንብድና እዬተዋከበች ሦስተኛ የነነዌ ፆም ላይ ዕለተ ሮብ ላይ ነበርን። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ፈረንሳይ ፓሪስ መግባታቸው የተደመጠው። ጉዞው ሽሽት ነበር። ጣሊያን ደርሰው ወደ ፈረንሳይ አቀኑ።    ከፈረንሳይ ሲመለሱ ፈረንሳይ የሁለት ዓመት የጡሮታ ጊዜ ተራዘመ ብሎ በሰላማዊ ሰልፍ ተናጠ። እግረ ደረቅ። አሁን የዛሬ ሳምንት ደግሞ ፈረንሳይ የዓለምን ኢኮኖሚ ያማከለ ግሎባል ጉባኤ አካሄደ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እዛው ነበሩ። ሲመለሱ ያ ህውከት በፈረንሳይ ቀጠለ። ዕውነት ምንድን ነው ጉዱ አሰኝቶኛል። ምንድን ይሆን የተሸከሙት መንፈስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ