ምን አጎደልን? ከምንስ ጎደልን? ምንስ ይሙላው? ለመሙላትስ አቅሙ አለን ወይ?

 

ምን አጎደልን? ከምንስ ጎደልን? ምንስ ይሙላው? ለመሙላትስ አቅሙ አለን ወይ?
"ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ!"
(መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፪)
እንዴት አደራችሁ ውድ ቤተሰቦቼ?
 

 
 
፱ኛው አሳቻ ዘመን ይቃኝበታል። ጥበብ በሙሉ አቅሙ ዝም እንዳይል ስጋት ስለታወጀበት። ጥበብም ዴሞግራፊ ይሠራበታል የሚል ምፅዓት ያለው ዘመን ተደርሷል። መኖር ዴሞግራፊ፤ መኖር የሰጣቸው ገፀ በረከቶች ሁሉም በጥላቻ ተፈርጀው ነቀላ ላይ ላለው ዘመነ አሳቻ መትከል ሳይሆን የተተከለን መንቀል ቀላሉ ድርሻዬ ብሎ ተያይዞታል።
የሆነ ሆኖ የእነኝህ የጥበብ በዝምታ ተጋድሎ ጉዳይ የት ደረሰ? ከመድረኩ አሉ ወይንስ እንደተሰወሩ ይሆን? ዝም ማለት፤ ፀጥ ማለት፤ ጭጭ ማለት በማይፈቀድባት ኢትዮጵያ ጥበብ ተለጉመሽም ገጽሽን ዓይን ላፈር የወፈፌወች የባንድ ኳኳቴ ነው። እነሱ ፍርሻ፤ በደል፤ ጭንቅ አምርተው በማከፋፈል ላይ ሲሆኑ፤ ይህ አልተመቸኝም ያለችው ብጡሏ ጥበብ ደግሞ ባይሆን ግንባሬ ወክ ያሰኜዋል፤ እጄም አቤቱታ ስትል ታገደች።
የአገዷት ኮሽ ባለ ቁጥር ድንግጥ ድንግጥ የሚሉት የዓለሙ የሰላም ሎሬት ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ጠረኑ የእኔን ፍርሻ አቤት ወዴት የሚል አዲስ ብይድ ቋንቋ ጥበብሻም ታምርት ዓይነት ነው።
በዝግ ውስጥ ትንሽም አዬር አይግባ ብሎ የበዬነው ኦነጋዊው አስተደዳር ምን ሲባል ሞትን፤ መጎዳትን፤ የባሩድን እሩምታ ታሳጣላችሁ ሲል ባሳዬው ቁጣ እንሆ አዲስ አደዮችን ማዬት እንዳይቻል የቅበር ተልዕኮውን ከውኗል።
ይህ ዘመን ሁሉንም ነቅሎ ልስን ባዕዳዊ ልጥፍ ለመለጣጠፍ አና ብሎ በጀመረው ዘመቻ በ፭ ዓመት ዬ50 ዓመን ፋንታዚውን እያሳካ ነው። አቶ ሽመልስ አብዲሳ በ2014 ዓም በነበረው የሬቻ ዋዜማ ላይ የተሰጠንን 5 ዓመት በ5 አባዝተን የ25 ዓመት ተግባር እንከውንበታለን ሲሉ ባሊህ ያላቸው አልነበረም። በዛ ንግግራቸው 2500 ዘመን ዘርፈው ወደ አባቶቻችን የ3000 ሺህ የእኛ ዘመን ላይ ነንም ብለው ነበር። የታሪክ ሙሁራኑ አላስቆሟቸውም።
ነገ ይሄ የመማሪያ መጸሐፍ ሆኖ ለህትምን ይበቃል። የማይበክሉት የእኛነት፤ የመኖር ዓውድ የለም። ስለዚህ ወልጋዳውን እያቃኑ ትውልዱ የመንፈስ ብርታት እና ጥንካሬ አግኝቶ እራሱን ሳያጣ እራሱን አስጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ህሊና ተኮር ተግባራትን መከወን ይገባል። ትውልድ ከእነ መልካም ተስፋው፤ ከእነ መነሻው እና መድረሻው አቅጣጫ በቀውስ ማት እንዲናጥ እዬሠሩበት ነውና።
የሆነ ሆኖ ስክነትን የሰነቀ የማድመጥ፤ እርጋትን የዋጠ የማስተዋል ተጋድሎ ይጠይቃል። ለዚህም ከራስ መነሳት አንዱ የዲስፕሊን አንኳር ነው። ወሳኙም። እራስን አዳምጦ መነሳት።
#የጎደለው እራስን #አድምጦ #አለመነሳት ነው። የጎደለውን የሚሞላውም እራስን #አድምጦ #መነሳት ነው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
03/07/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።