ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 13, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኢትዮጵያ ባላባራ ጦርነት ተበልታለች፤ በቃትም!

ምስል
አውሬነት? "በውን ጽድቅን የሚጠላ ይሠለጥናልን?" መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፲፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 13.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። መነሻ ምርኩዝ። https://www.youtube.com/watch?v=6vi9PgOzwEQ Ethiopia ዶ / ር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ ያደረጉት ሙሉ ንግግር ሰላም የጽድቅ መንገድ ነው።! ·        እፍታ። እግዚአብሄርን አመስግኜ ልነሳ። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ዶር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋዋላ እንደ ዜጋ ፓርላማን እንዲህ በመደበኛ እምከታተለው። በቀደመው ጊዜ ስለምን ይህን ያህል አገለልኩት ብዬ ሳስብ፤ ግብረ ምላሹ ውስጤ ባይታዋር ነበር ማለት ነው።  ውስጤ ባይታዋር ለሆነበት ጉዳይ ጊዜ አላጣፋም። የመስማት አቅሙም ስሌለኝ። ሰሞኑን እህቴ የሳጅን በረከት ስሞዖን መጽሐፍ ተለቋል እና አንብቢው ስትለኝ ሴራ ት/ ቤት ለመግባት አላነበውም ነበር ያልኳት። የዶር አብይ አህመድን የቀደመውን ንግግር አብዛኛውን ቃል በቃል አውቀዋለሁኝ ስለምማርበት። ·        የወ ግ ገባታ።   አሁን የጹሑፌ ታዳሚዎች ለምን ስለዚህ፤ ስለዚያኛው ድርጅት አትጽፊም ይሉኛል። ስሰማው ነው ያን ድርጅት ወይንም ቃለ ምልልስ ያን ውይይት እምሞግተው ወይንም ደግፌ እምጽፈው። ጹሑፍም ሲሆን ሳነበው ነው ሞግቼ ወይንም ይጠናከር፤ ወይንም በትርጉም ይቃና ብዬ እምጽፍለት። የፖለቲካ ድርጅቶች ደግፎ መጻፍ መስዋዕትነቱ አይደለም ክፋቱ እንሱም እዬደገፋችሁዋቸው ግን ማህበራዊ መሰረታችሁን እርቃኑን ያስቀሩታል በጎን። ይህ የግንቦት 7 ካድሬዎች ሌጋሲ ነው። ለዚህ ነው እኔ ኢሳትን ከጅምሩ ሳልቃወመው ግን ምንም ጊዜ ላባክንለት ያ