ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 21, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ማካካሻ። ፲ አለቃ መሳፍንት

ምስል
  #ማካካሻ ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።     ፲ አለቃ መሳፍንት ይመስለኛል ሥሙ። የጄኒራል ሳህረ መኮነን ጠባቂ የነበረ ወጣት ነው። እኔ #ታቅዶ የተመደበ ይመስለኛል። ከእሱ ይልቅ ለመታመን ሌሎች ተመሳሳይ ማዕረግ ያላቸው ነበሩ የወንዝ ልጆች ነበሩና። ጄኒራሉን ለመቅደም #ገዳዩ #ጎንደሬ መሆኑ የትወናውን ሁነት ያብራራል።   በሌላ በኩል አገዳደሉን ማን ይምራው ማን? በፍጹም እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር በሰውኛ #ስሌታዊ አመክንዮውን ስለማይደፈር። ወላጅ እናቱ ክፍትፍት ባለ #ጉሮኖ ይኖራሉ። አሁን በምን ሁኔታ እንደሚገኙ አላውቅም።   የፍርድ ውሳኔው ተሻሽሎለታል። እግሩ እና ዓይኑ ግን #በድብደባ ብዛት እንደተጎዳ ሰምቻለሁኝ። ደብዳቢወቹ ማን ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋክት መረጃ ማቅረብ ባይቻልም፤ በቀልን የጸነሱ፤ መበቀልን በእጥፍ ለመተግረብ የጭካኔ ረሃብተኞች እንደሚሆኑ ግን መገመት ይቻላል። ለኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ልኳ አይደለም፤ ለእኛም አንመጣጠንም የምለውም ለዚህም ነው።   ህወሃትን ያህል የሴራ #ጉድጓድ ተሸክመህ፤ ሌላውን ቤርሙዳ ትርያንግሉን የማህበረ ኦነግን #ትብትብ አቅፈህ ይህ ብላቴና ግርማቸው የሚያስፈራውን መኮነን ደፍሮ ገደለ ለእኔ ብዙም ቅርብ ያልሆነ ሎጅክ ነው።   መሪነት በግርግር ጊዜ ያላጠናቸውን፤ ግን የገደፋቸውን ስርክራኪ ሁነቶችን እንዲህ ቅንጡ ሆቴሎችን ለመመረቅ ሰፊ ጊዜ ሲሰጥ ደግሞ #ተግ ብሎ እንደነዚህ ዓይነቶችን እጅ እና እግር አልቦሽ የሆነ የበቀል መገበሪያ፤ #የቁርሾ ማካካሻ በሆኑ ዕውነቶች ላይ ጥርት ያለ የግንዛቤ ለውጥ አምጥቶ እራስን ማረመን - ይጠይቃል።   ለመሆኑ ይህ ወጣት አሁን በምን ሁኔታ ላ...

ባለቤት #አልባወቹ ምንዱባን። የአዲስ አበባ #ከንቲባ ጽ/ቤት ባሊህ ሊለው የሚገባ በኽረ ጉዳይ።

ምስል
  ባለቤት #አልባወቹ ምንዱባን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ" አሜን።  የአዲስ አበባ #ከንቲባ ጽ/ቤት ባሊህ ሊለው የሚገባ በኽረ ጉዳይ።       1) ቁጥር አንድ ቢጫ ለባሾች በመስከረም ወር በ2011ዓ.ም የታሠሩ ወለዮወች እና ጎንደሮች የደረቅ ወንጀል #ሽፍቶች ናቸው ሲሉ ነበር የጦር መኮንኖች የተናገሩት። የሆነው በቡራዩ በደረሰው ሰቆቃ ለልግሥና እና አክብሮት እጀ - ረጅሙ የአዲስ አበባ ህዝብ ተፈናቃዮችን #አጽናንቷል አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ግንቦት 7 ሲገባ #ስቀህ ተቀብልኃል ዓይነትም ይመስላል። ይህም ብቻ አይደለም በውስጡ የተቋጠረው ቂም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድንም #እልል ብላችሁ ተቀብላችኋል የሚል የውስጥ አርበኞች ጉዳይም ሊኖርበት ይችላል። በተጨማሪም ኦነግ መስከረም ፭ ኢትዮጵያም ሲገባም በነበረው #ድባብ 1300 አዲስ አበባ ያፈራቸው ልጆች ጦላይ ተጣሉ። ፭ የአዲስ አበባ ነዋሪወች በአደባባይ #ተረሸኑ ። ጠቅላይ ሚር አብይ እንደ ለለውጡ መስዋዕትነት እንደከፈሉ ይቆጠራል ብለው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ውሹን ያነሳ የለም።   የሆነ ሆኖ እነኝህ የምታዮዋቸው የመጀመሪያወቹ ብጫ ለባሾች #ከ1300 የአዲስ አበባ ነዋሪወች የጦላይ እስረኞች እንግዲህ #በሃይማኖታቸው ይሁን፤ በዘር ሐረጋቸው በማንነታቸው እስር ቤት ነበሩ። በምን ሁኔታ ላይአሁን እንደሚገኙም አላውቅም። የታሠሩት ከባልደራስ ምሥረታ በፊት ቢሆንም ግን ስለአዲስ አበባ የተደራጀው ባልደራስ አጀንዳው አልነበሩም። እነኝህ ምንዱባን፤ ትናንትም ዛሬም #ለብልጽግናም ምናቸውም የሚያሰጋ አይደለም። ሰላማዊ እና ሩህሩህ ዜጎች ናቸው።    2) ሙሉ ዕድሜያቸውን እስከ ሰማዕትነት ለኢትዮጵያ የገበሩ #የኢህአፓ ...

#ምህረት፤ #ይቅርታ መንገድን ያቀናል - ያቃናልም፤ ዓላማን ያሳካል፤ #ለትውልድ ይሆናልም ከደከምን ላይቀር ለእኩል ሳቅ እንትጋ።

ምስል
  #ምህረት ፤ #ይቅርታ መንገድን ያቀናል - ያቃናልም፤ ዓላማን ያሳካል፤ #ለትውልድ ይሆናልም ከደከምን ላይቀር ለእኩል ሳቅ እንትጋ።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"       #ምዕራፍ ፲፰።   በአብን፤ በባልደራስ መፈጠር በርካቶች ታሠሩ፤ ተንገላቱ፤ ኑሯቸው #ተበተነ ። ለስደትም የተዳረጉ አሉ። ግን ያ ሁሉ መስዋዕትነት በየባዕላቱ በዓድዋ ይሁን በካራማራ የተከፈለላቸው ግብር ምን #አፈራ ??? ምንስ አሳካ??? የፖለቲካ ድርጅቶች አስበው የሚነሱት ትውልዱን ነው። ትውልዱ በየዘመኑ ማገዶ ሲሆን አንድ እስክርቢቶ ገዝቶ ላላስተማረ ሰብዕና ግንባታ ሲል ነው የመፈጠሩን ተልዕኮ የሚገብረው። ይህን ዕውነት ተቀብሎ ለእናት ማህጸን ቢራራለት ጥሩ ነው። ልጅ የዳንቴል ሥራ ውሎ አይደለምና።   ቢያንስ ተው ስንል ቢደመጥ ብዙ፤ በጣም ብዙ ነገር ማትረፍ ሲቻል ጫን ያለ የጭንቀት እና የማቅ ሁነት ተፈጠረ። እራሱ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዱም ብዙ የሚስጥራቷ መድብል ታውኮ ነው የባጀው። ዝም የምለው ሁሉ ነገር ጠፍቶኝ፤ ጉዳቱ ሳይሰማኝ ቀርቶ አይደለም። ከዛሬ ነገ #ማስተዋል ቀን ከሰጠው ብዬ እንጂ። የአማራ ክልል ማቅ መልበስ ውስጤን ያቆስለዋል። ብዙ ወገኖቻችንም ተፈናቅለዋል። የዛ ገራገር ገበሬ ሁነትም ውስጤን ያውከዋል።    ይህ …… #ትናንትም ሆኗል፤   ዛሬም እዬሆነ ነው። ነገም ይቀጥላል። ድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ እናቶች የማህጸናቸው #ቄራነት ይቁም ብለው ብሄራዊ ንቅናቄ እስካልጀመሩ ድረስ። በአዳዲስ ስያሜ፤ በአዳዲስ ውህድነት ወይንም ቅልቅል ማገዶ የሚሆነው ነፍስ እንደ እለት ጉዳይ ይታያል። ገብያ ተሂዶ እንደሚሸመት ሸቀጥም ይታያል።   ከ...

ለጎንደሮች መርማሪ እና ሞጋች ጡሁፍ ከአቶ ለምለሙ ባይህ ፔጅ ያገኜሁትን እንሆ። የእኔንም ዕይታ አክያለሁኝ።

ምስል
  ለጎንደሮች መርማሪ እና ሞጋች ጡሁፍ ከአቶ ለምለሙ ባይህ ፔጅ ያገኜሁትን እንሆ። የእኔንም ዕይታ አክያለሁኝ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       ……… እኔ ደግሞ እላለሁኝ።   "ጽድቁስ ቀርቶ በወጉ #በኮነነኝ " ይላል ጎንደሬ መንገድ ዘግቶ #ጉሮሮዋን መዝጋቱ፤ #ጢስ ጢንቢስ የሚሉ ተቋማት ተቀንቶባቸው #መንደዳቸው ፤ እንደገና አወን #እንደገና የህወሃት ጠቀራማ #ህማማት ዘመን ተናፍቆ ለዛ ናፍቆት ብድግ ቁጭ ማለቱ በቀረባት።   መቸውንም በየትኛውም ሁኔታ ለጎንደር የተሻለ #ጤናማ ዕይታ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቅ ይመጣል ብዬ አላሳብም። በጋሜዬ እና ቁንጮዬ የተጀመረው #የፖለቲካ ህይወቴ ይሁን #በሰርዴታዬ የተዋህድኩት የራዲዮ ጋዜጠኝነት ህይወቴ ሂደቱን በጥሞና ስከታተለው፤ #ለናሙና የማነሳው ስለ ጎንደር ቀና የሚያስብ የፖለቲካ ሊቅ ለመሪነት በሌላው ወገን #የታጨ ወይንም ራሱን #ያጨ አላውቅም። ከሁሉም በዕት #ተገላዮች #በክፋ ዓይን የምንታይ እኛው ነን።   የሚገርመው #የእኛው ሰው የሚያጠቃው እኛኑ ነው። እኔን የሚታገሉኝ እኮ ጎንደሮች ናቸው። አሁን በቅርቡ ስለጠለምት ቅርብ ከሆነ ሰብዕ መረጃ ላይ ስፈልግ ብሎክ አድርጎኛል። ምን አድርጊ ብሎ ብሎክ እንዳደረገኝ አላውቅም። #እርግማን ይሁን ምን አላውቅም። በኪነጥበቡ ነው የሚኖረው። ሲያውቅህ ጥቃቱን አስቀድሞ ነው። የራስ ቤተሰብ ለአገር ሲዘራ ውሎ የሚያድረውን አቅም ከአንተ ሲደርስ ይቆልፈዋል።   ሼር፤ #ላይክ እና #ሰብስክራይብ ብርቅ ሆኖ ከእኔ ፔጅ አንድም እህት ወንድም የለም። ጨርሶ አያስቡትም። አንዳንዶቹ ምን እንደምሰራም ጭራሽ #አያውቁም ፤ ቢያውቁም አጀንዳቸው አይደለም። #አብይዝም...