ልጥፎች

ከጁን 11, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የተፃፈው ሁሉ እየሆነ ነው || ዶ/ር አብርሃም አምሃ

ምስል
ፈቃዱ ዛሬ ነበር። ቤቴ ውስጥ የተከወነውን ልክደነው። ዊዝደም ለናፈቃችሁ የዕውቀትም የርጋታም የኔታን እንሆ። መጨረሻ ላይ አለቀስኩ። ስለእኛም ስለኢትዮጵያም። በርቀት ስለ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራም አሰብኩ። ሥርጉትሻ ደህና እደሩልኝ። ሰላም ካደርኩ ነገ አገኛችሁአለሁ። 11.06.024

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶር ዳንኤል በቀለ፦ ይድረስ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋች ክቡር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፦

ምስል
  ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶር ዳንኤል በቀለ፦ አዲስ አበባ። ይድረስ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋች ክቡር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፦ ካሉበት። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     ጉዳዩ፦ የሰማዕቱ ኢሳያስ በላይ ቤተሰቦችን እና አብረው እስረኛ ስለሆኑ ጓዶቻቸው #ቀጣይ #ሕይወት ይመለከታል። አሁን በመረጃ አቀራረብ ጥራቱ እና ቅልጥፍናውም፦ በሚዛናዊነት አቅሙም ተስፋ ከማደርግበት ሚዲያ አንዱ ኢትዮ ኒዊስ ነው። ከደማችን ጋር እንዲዋህድ በተገደድነው #ዘወትራዊ " #ሰበር " #አስደንጋጭ ዜና እንደ ተለመደው በዛሬ ኢትዮ ኒዊስ ረፋድ ዜና ደነገጥኩኝ። ሰውነቴም #ተንዘፈዘፈ ። መቀመጥ ተስኖኝ ጋደም ብዬ ነው የምጽፈው።   ሰማዕቱ ሟች አቶ እያሱ በላይ አሰቃቂ በሆነ ድብደባ እና ዘለፋ በታከለበት ሁኔታ ህይወታቸው ማለፋን የእሥር ቤት ጓዶቹ መሠከሩ ይላል ዘዬዘገባው ዕድምታ። #አስፈሪው ጉዳይ ተረኞች ሊኖሩ እንደሚችሉም #ዛቻ እንደሚደርስባቸው የእስር ጓዶቻቸው ገልፀዋል ይላል ኢትዮ ኒውስ በስደት ባለበት አገር አሁን በሰማሁት ዘገባ።   #ህም ! #አማጥኩኝ ።   1) እነኝህ ዛቻ ስንቃቸው እንዲሆን የተገደዱት እስረኞች ለቀጣይ ህይወታቸው ማን ዋስትና ይስጥ? እንዴትስ ማፍትሄ ማግኜት ይቻል ይሆን? 2) ቁጥራቸው በውል ለማይታወቀው የአማራ ህዝብ ሊቃናት እና ሊሂቃን እስረኞች በቀጣይ እንደምን ጥበቃ ሊደርግላቸው ይችል ይሆን? ስጋቴ አይሏል። 3) በሻለቃ ናሆሰናይ ጉዳይ የታሰሩት ባለፈው አጭር ዘገባ በመንግሥት የተሠራባቸው ወገኖች እና እስሩም በዚህ ዙሪያ ከቀጠለ ልቁን ጭካኔ ማን ሊገድበው ይችል ይሆን?   4) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቁ ሆነ መቀጠሉ መቼ ነው ይፋዊ መግለጫ በጠሚር አብይ መንግሥት አገዛዝ የሚገ