ነገ አምጦ እንዲመጣ ሴረኞች ተግተዋል።
ከበደ ነገ እያማጠ ነው። „እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እንተ እግባለሁኝ። በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“ መዝሙር ፭ ቁጥር፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 18.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ በአንቦ ሌላ የከበደ ዜና ተደመጠ። እርግጥ ነው የተጎዳ ወገን እንደሌለ ዘገባው ቢጠቅሰም ቀጣዩ ግን እጅግ አስፈሪ ነው። በምን ሁኔታ ይህ ዝርግ ፖለቲካ ሊገራ እንደሚችል ፈጣሪ ይውቀው። እዬጨነቀኝ ነው። ከነሴራው የተቀላቀለው መንፈስ ከአገር ውስጥ ሽምቅ ተዋጊው ጋር ተቀይጦ የአጥቂነት ሥራውን እዬሠራ ነው። ንፁሃን ምን አደረጉ? በተበከለ ምግም 2000 ወገኖች ጥቃት እንደተፈጸመ በአንቦ አካባቢ ተገልጧል። በዚህ ዓይነት ስንቱ ነገር ቁጥጥር ተደርጎ ሊደረስበት ነው። አለመደብንም እኛ ሰላማዊ፤ ምህረት፤ ይቅርታ ፍቅር ብሎ መልካምነት። ግድለው፤ እስራው፤ አፍነው፤ አፈናቅለው ነው የተኖረበት። የሆነ ሆኖ ይህ አስደንጋጭ ዜና ነገን እንዲያምጥ ያድርገዋል። ከበደኝ። ይህ ምስኪን ፍጥረት ምን ያድርግ? ከስንት ይቆራረጥላቸው? ያ ሌት እና ቀን ተባክኖ በውጭም በአገር ውስጥም መንፈስን ለማስተካከል የተደረገው ዘመቻ በአዲስ ቀውስ ፈጣሪ እና አምራች ሃይል እና ጉልበት እንዲናድ፤ እንዲቀዬጥ፤ አንድነቱ እንዲበጠበጥ ተተግቶ እዬተሠራበት ነው። ለዚህ እኮ ነው አንድም ተፎካካሪ ፓርቲ ሥራ ሊጀምር ፈቃደኛ ያልሆነው። ውስጥ ለውስጥ አድማው አለ። መፍንቅለ መንግሥት። በሌላ በኩል ከኢትዮ ሱማሌ የተፈናቀሉ ምንዱባን ባህርዳር ላይ የክልሉ የጥበቃ ሃይል ሊያግዛቸው ሲገባ ጥቃት እንዳደረሰባቸው ዘገባው ይጠቁማል። ይኸው ነው ሴራው። ሌላውን ወርቅ ትሸልማለህ፤ ካባ ትደርባለህ በሰላም አገር ሲዘባነን የነበረውን ተመችቶት ደልቶት...