ጥምልምል በቁልፍልፍ።
ጥምልምል በቁልፍልፍ፤
ጥምንምን በትልልፍ።
„እግዚአብሄርን በኃጢያታቸው
እንዳሳዘኑት እሱም ቸል
እንዳላቸው
እንደቀደሙ ሰዎችም አትሁኑ በጥፋት
ውሃም ያጠፋቸው
አሉ።“
መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ምዕራፍ ፲፲ ቁጥር ፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
18.09.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።
- መነሻ።
የኔዎቹ እንዴት ናችሁ ኦቦ በቀለ ገርባን ትሁት እና
ታዛዥ አድርገን መሳላችን፤ ለዛም መታገላችን አይቆርቁረን። የሳቸው ህሊና እስከ መቼውም እረፍት የማይሰጠው የመልካም ነገር ዕዳ አስቀምጠናል።
እርግጥ እጅግ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ደግሞ አለኝ፤ ከልዕልት ጽዮን ጋር በነበራቸው ቆይታ ልጆቻቸውንም በሳቸው አምሳል በነፃነት ታገይነት
መንፈስ አስርጸው ማሳደጋቸውን አዳምጬ ነበር።
አሁን እንዛ ቀንበጥ እና ዕንቡጥ ልጆች ያስስቡኛል
የነገ ዕጣ ፈንታቸው። ምክንያቱም ዛሬ እምናያቸው ኦቦ በቀለ ገርባ ልጆቻቸውን እንዴት እንዳሳደጉ እንዴትም እንደቀረጹ አስተርጓሚ
ስለማያስፈልገኝ። ሌላው አሁን እሳቸውን እንደ ኢትዮጵያ የመፍትሄ አካል አድርጎ የማዬቱ ለሳቸው የተሰጠው መንግሥታዊ አደራም ከእንግዲህ ውል የለሽ ነው። እሳቸው የሚታገሉት ለታላቋ ኦሮምያ ጋር ነውና።
ያን ጊዜ ደጋግሜም እንዳነሳሁን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ታውጆ ያን ረግጠው ነቀምት ላይ ስብሰባ እንዲዛጋጅ ያደረጉትም ይህን መሰል የሰሞኑን መሰል ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት ስለመሆኑ የሰሞኑ
ይፋዊ እንቅስቃሴ ይታያል። ለዚህም ነው ሲፈቱ አጀንዳ ያልነበሩ ሲታገቱ ለሚዲያ መጫኛነት የተጠቀሙባቸው። ጥምልምሉ ፖለቲካችን እንዲህ ነው። ለእውነት ሳይሆን ግርግሩ ለ እኔ ከጠቀመኝ ነው።
ለ እኔ በግልጽ ቋንቋ ማሽሞንሞን ስለማልሻ መፍንቀል መንግሥት ነው አዬሆነ ያለው። የሆነ ሆኖ ለንፅጽር እንዲረዳን
አንዳንድ ጭብጦችን ማቅረብ ፈልገሁኝ። ይህን ሳቀርብ ግን ወስጤ እዬቆስለ ነው። እሳቸውን ኢትዮጵያ እንድታጣ አልሻም ነበር። አሳቸውን
ብቻ አይደለም ተስፋ የጣልኩባቸው የለማ ቲምንም እንዲሁ አሁን የሚታዬው ታጥቦ ጭቃ ነው። እንቦጭ!
- · እኛ የምናውቃቸው አምላክ መርቆ የሰጠን ብለን ግዛን ንዳን ያልንቸው ኦቦ በቀለ ገርባ እኒህ ነበሩ ለታሪክ … ውጪያቸው …
https://www.ethiotube.net/play/%E1%8A%90%E1%8D%83-
ነፃ ሃሳብ – የከትማ
ልማት
እና ቤቶች ሚኒስቴር ለአቶ
በቀለ
ገርባ
እኔም የኢትዮጵያ ንጹህ መንፈስ ያረፈባቸው፤ የነፃነት
አርበኛ ናቸው ብዬ ብዙ ጽፌያለሁኝ። ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከተለካውም አጭር ፊልሜ ውስጥም አሉ ደብዳቤዎችም ውስጥ እንዲሁ።
እሳቸውን ይጭነቃቸው እንጂ እንጂ እኛን ሞኞቹን፤ ጅሎቹን
እና ቅኖችን ቅንጣት እኛን አይጨንቀንም አይጠበንም። አይቆረቁረንም። መልካምነት ትርፍነቱ ለህሊና ነው። በአገር ልጅነት የተገባውን ክብር ልዕልና ፍቅር እና የመንፈስ ክብካቤ አድርገናል።
ጸጸቱን የሚሸከሙት አሳቸው ብቻ ናቸው። መቼውንም ቢሆንም በዬትኛውም ሁኔታ ቢሆን የጎንደር
ህዝብ የሰጣቸውን ፍቅር አያገኟትም።
እሳቸው አሜሪካ ሲሄዱም የጎንደር የትምህርት ጓደኞቻቸው ምን ያህል ፍቅር አንደሚለግሷቸው ገልጠዋል።
አሁን ግን ሁሉም የለም ተፍቋል። እሳቸው ደሜ ባሏቸው ክብካቤ እና ተጋድሎ ነው ለቅዳሜዋ ዕለት የደረሱት። የእነ ገዱ መንፈስም፤
የ108 የፓርላማ ድምጽም ላሳቸው ብጣቂ ያደረገው ነገር የለም።
- · አጭሩ ፊልም ይህ ነበር። ብዙ ቦታ ተልኳል። ትርፍም ተገኝቶባትል ጸህፍት አንስትን አስፈትቷል።
Ungerecht (injustice) neue
ጎንደር ላይ የነበረውን ነገርም መሪዬ ነው ብሎ ወጥቶ
የተቀበለውን ፍዳ የሰማዩ ዳኛ ብቻ ነው የሚያውቀው። የሰሞኑ ኦቦ በቀለ ገርባ ደግሞ እኒህ ናቸው። ውስጣቸው እንዲህ ሻከራማ ነው ...
Ethiopia: የኦፌኮ ምክትል ልቀመንበር
አቶ በቀለ ገርባ ከOMN ጋር ያደረጉት ቆይታ
ይህ ሲገርመኝ ቅዳሜ ላይ በነበረው
ሰላማዊ ሰልፍ ደግሞ እኒህ ናቸው።
Obbo
Baqqalaa garbaa fi obbo jawar Mohammed Haasaha taasisan OBN tamsaasa kallattii
መሬቱን ሊረግጡት ተጸዬፉት። በአዬር ላይ ተንሳፈፉ።
በቃ መሬት ለሳቸው ባትፈጠር እና ለሳቸው ሲባል የሰው ልጅ አፈርን ሳይነካ አዬር ላይ ቢራመድ በወደዱ። በቃ የግራቢት ህግጋት
ቢሰረዝ በወደዱ ነበር። የሰኔ 16ን የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ትህትና ያዬ ይህን ሲይ ህሊናን ይፈትናል።
ውዶቼ ክብረቶቼ የለጠፍኩትን ቪዲዮውን አስተውላችሁ እዩት -
ትእዛዝ አይደለም በትህትና። በሠራዊት ማህል በዙፋን የሚጓዙ ከሰማዬ ሰማያት የወረደ ምድራዊ ንጉሰ ንጉስ አጤ ነው የሚመስሉት።
እኒህ ነበሩን እኒያ የሞራል መምህር እያልን፤
የፍቅራዊነት ሐዋርያ እያልን ፊት ለፊት ወጥተን የማህብራዊ ሚዲያውን ግርፊያ ችለን የመሰከርንላቸው አቦ በቀለ ገርባ? የት ነበሩ ጃዋርውያን ያን ጊዜ? ስለሳቸው የሚጻፉ ነገሮች እኮ 60 ሰዎች ነው ሼር የሚያደርጉት የነበረው። አሁን ማካሄጃ ስለመሆኑ የቆዬ ሰው ያዬዋል።
እርግጥ ነው እሥር ቤት ውስጥ ያልተለመዱ ነገሮችን ማድረጋቸው ብወድላቸውም የፈለገ ነገር ቢሆን ዳኞች ሲመጡ አልነሳም ማለታቸው ግን ከፍቶኝ ነበር። እንዲያውም ለማከብረው ወዳጄ ጽፌለት ነበር፤ ሲፈቱም የማላውቃቸው ሆኑብኝ መታበይ አዬሁባቸው ብዬም ለዛው ለማከብረው ሰው ጽፌ ነበር ኢሜል ቢጤ። ብቻ የፍርድ ቤቱ ከሁሉም በላይ የከፋኝ ነበር።
ስለምን እንደሆነ ብረዳም ቢያንስ ልጆች ያያሉ ማለት ያስፈልጋል። እራሷ ኢትዮጵያም ህግ ናት። ኢትዮጵያም አገሬ ስለማትባል ቀርቶባት ዛሬ እያሳዩን ያለው ሰለጠነ የሚሉን የገዳ ሥርዓትን ቢያንስ ፍርድ ቤት ላይ ሊያሳኙን ይገባ ነበር። ገዳ ማለት ማክበር ከሆነ። ገዳ ማለት ትህትና ከሆነ። የገዳ ሥርዓት የፈጠራቸው እና
ያሰተማራው ኦቦ በቀለ ገርባ ለህግ የበላይነት ታጋይነት እና ድርጊት የተፋጠጡበት ዜና ነበር … ለፍርድ ቤቱ ሳይነሱ ቀርተው 6 ወር ተራዘመ ሲባል እስሩ ...
እንደገናም አንተ ፍትህ ተዛባ፤ የህግ የበላይነት ጠፋ ብለህ ለዛ እዬታገልክ፤ ፍዳ እዬከፈልክ አንተ የህግ ጠቅጣቂ ከሆንክ ለሞራል መምህርነት እርግጠኛ የሚያድርግ ብጣቂ የዕውነት አመክንዮ አልነበረም።
በሌላ በኩልም ያን ጊዜ እነሱ እንዲፈቱ የለውጥ
አራማጆች ከወያኔ ሃርነት ጋር ጉሮቦ ለጉሮቦ እዬተናነቁ እሳቸው ደግሞ የእስር ጊዜ እንዲራዝም ያልተገባ ጀብዱ ነበር የፈጸሙት። ጥምልምል ያለ እርምጃ።
እንደ ወትሯቸው በባዶ እግር መሄድ፤ በህብረት መዝሙር
መዘመር እነሱ ባይቀበሉትም የወል ታሪካችን ነበር። የ ኦሮሞ ግድል ተብሎ ይመዝገብልን ቢሉ ይሁን። የሆነ ሆኖ ህግ ለማስከብርክ እዬታገልክ ህግ ጣሽ መሆኑን በሳቸው ዕድሜ አዝኜ ነበር፤
ህሊናን ይፈትናል እንዲህ አይነት ነገር፤ በሌላ በኩል በተራዘመ ቁጥር ዓይነ በሽታቸው እና ግብዐቱም ነበር።
ብቻ እሳቸው የደፈረስ ስዕል ናፍቆተኛ መሆናቸው በነቀምቱም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥሰት አሳይተውናል። በዚህ ዘርፍ ዶር መራራ ጉዲናም ቢሆኑ የመጀመሪያውንም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ ሁለተኛውንም በጥሰት መሰሉን ነበር የፈጸሙት።
ህግ እዬጣስክ ለህግ የባላይነት እታገላለሁ አይገጥምም። የትኛው ህግ አሁን እነ አቶ ጃዋር ህግወጥ ሰንደቅዓለማ እያሉን አያደለምን? ዶር ነጋሶ ጊዳዳስ ህገ መንግሥቱ ተጣሳ እያሉን አይደለንም? ያው እነሱው ናቸው ይህን ህገ መንግሥት ያረቀቁት ያጸደቁት ይህም ማለት የራሳቸው ነው ማለት ነው፤ ለዚህ ታግለን ወያኔ ነጠቀን ነበር የቅዳሜው ዕወጃ ... ስለዚህ ራሳቸው ያወጡትን ህግ ስለምን ይጥሱታል? ፕሮግራሙን የመራው ሰው ይህን ነው የሚለው።
SIRNA SIMANNAA ABO 05 01 2011
ያን ጊዜ ያ የለውጥ ትረት ተደናቅፎ ጫና ለማምጥት የተሳበ ነበር። ነገር ግን አለስፈላጊ መስዋዕትነት መፍቀድ ኪሳራ
እንጂ ትርፍ አልነበረውም። ነቀምት ላይ አንድ አጋዚ በቂ ነበር። ድምጥማጣቸውን ሊያጠፋቸው ይችል ነበር። አካላቸውን ቢያጎድለውስ። ብቻ ፈጣሪ ጠበቃቸው እና ዛሬ ውስጣቸው ምን ያህል ጥምልም ያለ እንደነበር እያዬናቸው ነው … ዘመን ጥሩ ነው ..እንደ ሌላው ግን ደስ ብሎን አንቀበለውም። እናዝናለን። እሳቸውን በዚህ ደረጃ አልጠብቅንም እና ሁን ደግሞ አረጋጊ ነኝ ባይ ናቸው። እነሱ በተገላበጡ ቁጥር መንፈስ አክሮባቲስት አለመሆኑን ይወቁ።
እነዚህ መሰል ግድፈቶች፤ ህግ መተላለፎችን በተለያዬ ሁኔታም በጥቅሉ
ጽፌበታለሁኝ፤፡ የሆነ ሆኖ የዛሬው ግን እጅግ ከፋ -ከረፋም።
Obbo
Baqqalaa garbaa fi obbo jawar Mohammed Haasaha taasisan OBN tamsaasa kallattii
ሊንኩን መድገም ግድ ያለኝም በዚህ ቪዲዮ ላይ ትክክለኛውን አቶ ጃዋር መሃመድ አክተርነቱን ሳይሆን የውነቱን
ታገኙታላችሁ፤ የሜጫ ጨዋታ ጋር የተዋህደች ምስል ናት፤ ትክክለኛውን ፕ/ ህዝቃኤል ገቢሳን ገፃቸውን ከነውስጣቸው በማዬት ብቻ ግብረ ምላሹን
ታገኙታለችሁ።
በሳቸው
ጉዳይ መጻፉንም አልወደውም፤ አሁንም ተያያዥ ስለሆነብኝ እንጂ፤ ህብር ራዲዮ አለላቸው እጬጌ የሚያድርጋቸው የህዝቃኤል ድምጽ
እስኪያሰኝ ድረስ። ምን እንደገኘበት ባለውቀም አውራው ነበሩ።
ሌላው
የኦቦ በቀለ ገርባ የኦሮሞ ህዝብ 150 ዓመት ታግሎ ከዚህ ነፃነት ደረሰ ነው የሚሉት። ሥማችን እስከ ጹሑፋችን ድረስ እኮ
በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አለ አስከ የተባባሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ድረስ። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሚዲያም እንዲሁ። የእኔ ጥረትን በሚመለከት የተላከበትም ሰነድ
እጄ ውስጥ ይገኛል። በኧርጀንትም በአደራም ሲላክ ስለነበር።
የእነሱ
ዲሞ ምን የረባ ጊዜ አካሄደው ነው? በ27 ዓመት ውስጥ አትላንታ እና ለንደን ነው ስብሰባ የሚባለው በዘመን ውስጥ አንዲት ጊዜ ብቻ፤ ደግሞስ ለማንስ ታግለው? የቱ ለይስ ጎልተው ተገኝተው? ሁልጊዜ ተነጥለው እና ነጥለው ነው ሲታገሉ የኖሩት። የእነሱ የፖለቲካ ትልቅነት ዕወጃው ፕሮፖጋንዳው ነው። ዕድሜ ለኢሳት ዕድሜ
ለግንቦት 7 ይበሉ።
ኢትዮጵያዊው ባካሄዳቸው ዲሞዎች ግን እገሌ ተገሌ ሳይባል ለነፃነት ሁሉም
በእኩልነት ታግሏል፤ እነሱ ተገኝተው አያውቁም። ሥጦታችን ግን ይሄው ነው።
https://www.youtube.com/watch?v=SWzcsoc2twQ
„በስትራቴጂ
ተምርቶ እዚህ እንዲደርስ ከአንድ 150 ዓመት በፊት የዛሬዋ ቀን እንድትታይ አንዴ ተነስተው ይህን ባንዴራ እና ነፃነት ቢዩ
ምን ይሉ ነበር።“ አማርኛ ዜና OBN 05 01 2011
የእኛ
ቅንነት፤ የእኛ የዋህነት ለትውልድ አብነት ስለሆነ ከንጹህ መንፈሳችን እረፍት እንዳርጋለን፤ የእነሱ ቁልፍልፉ ጥምልምል እና ጥምንም ሰብዕና ልብ ደግሞ
የኦሮሞን ልጅ ብክነት ያውጃል። የ ኦሮሞ ልጅ ብክነት አስከመቼ የሚለውን ጊዜ ይፈታዋል።
አሁን ያስማማቸው የአብይ ተቀባይነት ነው። የአብይ አቅም አለን ከሚሉት ሁሉ በላይ ስለመሆኑ ነው። አንድም ያደረጋቸው የአብይ
ልቅና ሰብሮ ለመጣል ነው።
ተገንጥለው
ቢታዩ መንፈቅ አይሞሉም ሲበታተኑ። እስካሁንም አንድ አልነበሩም። አንድ ያደረጋቸው በማን ሃይል እና በማን ፈቃድ እንደሆነ
እነሱም ያውቁታል እኛም እናውቀዋለን። ለዚህ ኦቦ ለማ መገርሳ ቀን ከሌት በግልጽ እና በሰውር ደክመዋል። ምክንያቱም የወል ፍላጎታቸውን ኦነግ እንዲያስፈጽም እነሱ ደግሞ የግንባሩን አብሶ ብአዴን የጣላባቸውን መንፈስ አደራ ጠባቂ ሆነው መቅረብ ግድ ይላቸው ስለነበር ነው።
የቄሮ
ትግልም ቢሆን የሽዋ ኦሮሞ ትግል ነው። ዕውነቱ ይህ ነው። አንድ ወጥ አድርገው ለመምራት አልቻሉም። የነገረ ጃዋር ሚስጢር
እስልምና ነው። ደጋፊዎቹ እንሱው ናቸው። እንዲያውም ወጥ መንፈስ የመጣው በ አብይ እና በለማ መንፈስ ውስጥ ነው። አንድ ቃለ ምልልስ ሲጠዬቅ ሌሎቹ ይቆዩ ብለን ስለነበረ ነው አለ። አቅም ስላልነበረን ማለት አልተቻለውምና።
የሆነ ሆኖ ነገ
ሌላ ቦታ ሳይኬድ የሃይማኖት ኢሹ በቂ ነው። ሌላው ከእንግዲህ ይህ የኦቦ በቀለ ገርባ መታበይ ለማን ሊገዛ? ለማንስ
ሊተዳደር። ጠ/ ሚር ልሁን ነው ትግሉ … አቶ ጃዋር መሃመድስ? ኦቦ ዳውድ ኢብሳም በክራንችም ቢሆን? ኦቦ አዲሱ ረጋሳ? ዶር መራራ ጉዲናስ? ጎልተው ያልወጡ በ ኦህዴድ ውስጥ ሁሉን ነገር ሎጅስቲኩን ከጀርባ ሁነው እያሟሉ ያሉትስ የት ይሂዱ?
አቶ
ንጉሡ ጥላሁንም ቢሆን በዚህ ውስጥ ናቸው፤ አብይ መንፈሱ ባለበት ቦታ ሁሉ ትውር አይሉም፤ ወደ ሥልጣን እንደ መጡ የ ሳቸው እና
የዶር ነገሬ ቃለ ምልልስ አዳምጡት፤ ዶሩ ነገሬ በ10 ዲቂቃ 16 ጊዜ ኢትዮጵያን ሲያነሱ አቶ ንጉሱ ደግሞ በአገሪቱ ተጀምሮ
በአገሪቱ ነው የተጠናቀቀው።
አሁን
ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን አቀንቃኝ ሆነው ተስለፈዋል። የአማራነትን ማነቆነት በማደረጃት፤ በምምራት ደረጃ ደግሞ አሳቸው ናቸው። ድርብ
ሃላፊነት ወስደው እዬከወኑ ያሉት። እሳቸው ወደ ፌድራል ካልሄዱ በመጨው ዘመን ለአብይ አከቢኔም ለአማራ የህልውና ታጋድሎም
ቁልፍልፍ ጥምልምል ጥምንም ችግር ይገጥማዋል። እሳቸውን ያወቀ የለምና።
ለማወቅም
የፈቀደ የለም። ኮስታርነታቸውን አባ ኮስትርን ቢያሰመስላቸውም ሌጋሳቸውን አልወድላቸውም። ገፃቸው እራሱ አስፈሪ ነው ውስጡን
ለማግኘት የሚቸግር። ትክክለኛ ቃሉን ዛሬ ባልጠቀምበት ይሻላል። „ብቻ ልብ ያለው ሸብ“ በሚለው ይከወን። ራሳቸውን ይሸልማሉ፤
የራሳቸውን ትውፊትም እንደሁአማራ መሬት ላይ ሆነው ዘውድ ደፍተው ለማን እዬተጉ እንደሆነ አሳምሬ አውቀዋለሁኝ።
- · ማነው በገንዘብ የተገዛው? ከፊታችሁ ተቀምጠው።?
- የመንግሥት ሚደያዎች ሥራ ፈቶች፤ የፖሊስ ኮሚሸንሩ መግለጫዎች ሁሉ በገንዘብ የተገዙ፤ በስተጀርባቸው ተልዕኮ ያላቸው። በ አደባባይ እኮ ነጻነት ታውጇል። በ አደባባይ የተደራጁ ሃይሎች እርምጃ ውስድ ተብሎ መመሪያ ተስጥቷል። ማን ነው የሚሞኘው።
- · ሰሞናቱ የተነሱት ጦርነቶች እነዚህን ቃለ ምልልሶች ከልብ ሆኖ ማደመጥ ይገባል።
SIRNA SIMANNAA ABO 05 01 2011
Ethiopia: የኦፌኮ ምክትል ልቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ከOMN ጋር ያደረጉት ቆይታ
·
ንፅህና ለህሊና ቢሆንስ?
ገራሚው ነገር አሁን ደግሞ ከደሙ ንጹህ ነን ጩኸቱ ነው። ኦህዴድ ያደረገውን አድርጎ ከደሙ ንጹህ
ነው። ኦፌኮን ያደረገውን አድርጎ ከደሙ ንጹህ ነው። እህሳ? በገንዘብ የተገዙ? ሰውር ዓላማ ያላቸው? እነማን ናቸው እነሱ? እነሱን
መልክ ለማስያዝ የማይችል መንግሥት ከተሆነ አቅም የለም ማለት ነው። አገር ያስገባውን ሆቴል እዬከፈለ ያሰቀመጠውን በቪአይፒ ደረጃ ደህንነት ቀጥሮ እያስጠበቀ ያለውን መንፈስ ሁሉ አደራውንስ እንዴት ሊወጣው ይሆን?
በማን ነው የሚመካኘው ግንቦት 7 አገር ቤት ነው። ኤርትራ አገር ቤት ፍቅር በፍቅር ጫጉላ ላይ
ናት፤ ኦነግ ቅርንጫፎቹ ሁሉ አገር ቤት ናቸው። ወያኔ ከንግሥና ቦታው ነው አገር ቤት ነው ያለው። ኢሳት አገር ቤት ነው። ኦኤምኤን
አገር ቤት ነው። አብነግም ከዚህ አይዶለውም የተወሰኑትም አገር ገብተዋል።
እጃችሁ መዳፋችሁ ሁሉም መሬት ላይ አለ። የኦሮሞ ድርጅቶች ደናግል ቅዱሳን መላዕክታን፤ ወያኔ ሳጥናኤል ሲኦል ኖ! ክፉዎች የትም አሉ። ሴረኞች የትም አሉ። ይህን ቀደም ብዬ ሁሉ ጽፌዋለሁኝ። በወያኔ ሃርነት ትግራይ ምንም የሚመካኝ ነገር የለም። መሪው አደራጁ መዳቢዊ ሾሚ ሸላሚው ኦህዴድ ነው። በቃ። ህግ ማስከብር የ አገርን ሉዑላዊነት ማሰጠብቅ ያለበት ኦህዴድ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ ሁሉን ትቶላችሁ መቀሌ ነው ያለው። ሳቦታጁን፤ ሴራውን መቋመቋም የእናንተ ነው።
መፈንቅለ መንፈስ እኮ ተካሂዷል። ስለመገንጠልህ እድገፍሃለሁ ነው። ሆኖ እኮ አያውቅም እንዲህ። ከጥንዝሉ የ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃን የአስተሳሰብ ድህነት በስተቀር። ልክ ኤርትራ ትገንጠልልኝ ተብሎ ነፃነት ወይንም ባርነት ድራማ ነው እኮ እዬታዬ ያለው።
ስለዚህ ይህ እንሳሳዊ እርምጃ ከጀግናው ቄሮ መንፈስ የተፈጠረ ነው። መሪዎቹ ደግሞ እነ ጄኒራል
ጃዋር መሃመድ እና ኦቦ በቀለ ገርባ እራሳቸው ናቸው፤ ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ የተሰቀለው እኮ ሻሸመኔ ላይ ህዝብ ዙሪያ ከቦ እያጨበጨበ፤ እዬሳቀ፤ ፌስታ ላይ ሆኖ ነው የተፈጸመው እንጂ ማርስ ላይ አልነበረም። ይህን ወጥቶ ያወገዘ ሚዲያ፤ ሊሂቅ ይምጣ እስኪ እኔን ይሞግት።
ይህን መቼም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፈጸመው አይባልም። በወያኔ ሃርነት ትግራይ አይላከክ። የቆመስ ስመኘውን ገዳይ አምጡልን ብሏችሁል እኮ የትግራይ ህዝብ። ቡራዩም፤ ሰበታም፤ አስኮም የወያኔ እጅ
አለበት ማለት አይችልም። ስምምነቱ „ትግሬን አትንኩ“ መሆኑን ግን አሳምረን እናውቃለን። ይህም ስልጣኑ እስኪደላደል ድረስ ነው። ሁሉም ተራውን ይጠብቃታል።
ሰሞኑን የተሰጠውን የአቶ ጃውር መሃመድ እና የኦቦ በቀለ ገርባ መግለጫ ማድመጥ ነው። ጠብቁ
ታገኟታላችሁ ነው። ያ ግርዶሽ እንዲሠራበት ነው አቶ አዲሱ ረጋሳ እና የማከብራቸው አቶ ታዬ ደንዓ ሲያስተባብሉ የነበሩት። አቶ
ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ የአማራን መንፈስ የመግደል እና የማስገደል ትውናቸውን ተያይዘውታል ሲደመር አብይን መፈንቀል ነው። አህዴግንም መፈንቀል ነው። ሌላ ጨዋታ የለውም።
የአብይን የሚሊዮን
ፈርታይል የሆነ መንፈስ ነቅንቆ ማስወገድ እና የራስን እኩይ ተግባር መፈጸም ነው። ለሁሉም ማገር ሊንክ ሊሆን የሚችለው አማራው ነበር። አማራውም ቅንነቱ ተፈርቷል። ለራሱ ለትግሬው ከአማራ የቀረበ ነፍሱ የሆነ የለም። ግን አላወቀበትም።
- እውነት ሆይ!
ዕውነት አንተንም ስትፈትነህ ማለፍ የምትችለው መድፈር ስትችል ብቻ ነው። የሚያሳዝነኝ ብቻ ሳይሆን
የማፍርበት የኢትዮጵያን ሚዲያ ነው። አሁን እንኳን ህዝብ ሞቱን ፈቅዶ እውነቱን እዬተናገረ ይህን ለመድፈር አለመቻሉ እና ከጠ/ሚር
ቢሮ የሚወጣውን መግለጫ ወይንም ኤዲቲንግ ብቻ ለማስተናገድ መፍቀዱ ነው። የኢትዮ ሚዲያ ሙት ነው። ያሻው እንዳሻው የሚቀዝፈው ሬሳ።
በዚህ ውስጥ ከእንግዲህ በሰውር ብዙ ነፍሶች ይጠፋሉ፤ በዚህ ውስጥ ብዙ የሃቅ አርበኛ ነፍሶች
ይታፈናሉ። ሌላው ፈታኝ መከራ እንደ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አይነት ዕውነትን ሲደፍሩ ማዬት ይናፍቀኛል።
ጋዜጠኛ መሳይ የተወሰነ ነገር ደፍሯል። እርእሱን ወድጄዋለሁኝ፤ ነገር ግን እሱ የፖለቲካ ድርጅት
ካድሬነቱን ዝንባሌ ላይ ነው መቋጫው። የትኛዋ ኢትዮጵያ?ግንቦት 7 ኢትዮጵያኒዝም የመሸከም አቅም የለውም። ይህ እውነት ነው። ሌላውም እንዲደሁ።
የሆነ ሆኖ መሳዩ ይህን ያህል መሄዱ ግን ያስመሰግነዋል፤ ልክ እንደ ወሎ እልቂት
ከጎን እንደ ቆመው ማለት ነው። እንደ እኔ ጓድ ገ/ መድህንን በርጋ ወይንም ኮ/ ጎሹ ወልዴን መሰል ብልሆች ቢያገኙት ኖሮ ብርት መዝጊያ ይሆን ነበር። እውነት አምላኪ ብቻ ይሆን ነበር።
ሌላው ቲያትር ደግሞ በ27 ዓመት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተብዬዎች ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን ልክ እንደ ኢሠፓ ያከሰሙበት ዘመን ቢኖር
አሁን ነው። ይህን
ፅፌው ነበር እኮ፤ የሚጠበቀው ግንቦት 7 እስኪገባ ድረስ ነው ብዬ ሁሉ ነበር። ለዚህ ነው ቀንበጥን የጀርኩት ሃሳቤ ሳይቋረጥ ተከታታይ
እንዲሆንም። አሁን እኮ ልክ 66 ላይ ነው ያለነው። የዛን ጊዜ ግርግር ላይ። ወይንም የእነ ግርማሜ ዘመን … ቁልፍልፍ - ጥልፍልፍ - ጥምልልምል ...
አሁን ሁሉም ጠቅለል ብሎ የኢህአዴግ ፍላጎት አስፈጻሚ ሆኖ አረፈው። የ ኢሄኢአዴግ ካድሬ ወይንም ልሳን ወይንም አቦካቶ። የተሰጠውን ብቻ የሚጎርስ የሚውጥ። ወኔ ተሰደደ ... እንደ ተለመደው፤ እንደ
ድሮው፤ እንደ ተኖረበትም። አንድ የረባ ሰው፤ አንድ የረባ ፍሬ ያለው ሞጋች ድርጅት እንዴት ይጠፋል? እንዴት ይታጣል?
በቃ የውቂ ደብልቂ ፖለቲካ ይህው ነው ትርፉ። ለዚህ ነው እኔ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚመራው ንፋስ
ነው የምለው። ዓላማ ግብ የለም። ሃሳብም የለም። ሌሎች ባቀዱት በሚከውኑት ላይ መለጠፍ። ቁሮ እንጨት። ተቃዋሚ የሚባላቱን ኑ ከእኛ ከኢህአዴግ ጋር ተዋህዱ ቢባሉ ዓይናቸውን አያሹትም።
ይህን ዕወጃ ነው የሚጠብቁት። እንዲያውም እኔ እቀድም እኔ እቀድም ሩጫ ሽሚያ ነው …
ለወረፋ ለሰልፉ …
ለነገሩ ልናረጋጋ ነው አገር ቤት የገባነውም ተደምጧል እኮ? ሊፎካካሩ አይደለም ማለት ነው። እባካችሁ የ እኔ ክብረቶች አቅማችን ባልተገባ ማፈሰሱ ብቻ ሳይሆን እነሱን አምነን ማህበራዊ ሰላማችን
አናጠውልግ? በተለይ ሲዎዞች እንደ ወትሯን መሆን አለብን። መነኩሲያዋ ሲዊዝም የምታራምደው ይህንኑ ነው። ገለልተኛ ግን ለእውነት ዘብ መቆም።
ሊሂቃኑን፤ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን የ66ቶችን ሁሉም የሚያስማማቸው አንድ ነጥብ አለ አማራን አግላይነት እስከ ወዲኛው። ይህን ደግሞ ከጅምሩ በድርድር ሹመቱ
የተከወነ በሚመስል ሁኔታ የጠ/ ሚር ቢሮም ሆነ የመንግሥት ሚዲያ አማራን ያገለለ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ጽፌዋለሁኝ። መድፈር አልተቻለም።
አሁን አፍዝ አድንዝዙ ግንቦት 7 እያካሄደ ነው ድግምት ቢጤ ይዞ ወክ እንዲህ እያለልን ነው፤ ሌላው ቀርቶ የአብይ የድጋፍ ስለፍ ጊዜ ጎንደር የደገፈው ሳይሆን እነሱ ያሰናዱት የወህኒ ቤት
ደጋፊዎች ድምጽን ነበር ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያቀረበው። በዬትኛውም ሁኔታ ጎንደር የምትካሄድ አንዳችም ህዝባዊ ተሳትፎ አትዘገብም።
ለማን ሲባል ለኦነግ ተልዕኮ ሲባል። የኦነግ ተልኮ እስኪሳካ ድረስ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብጣቂ መንፈስ አትነካም። መደራደሪያ ... ጅሉ አማራ።
ገራሚው ነገር የድጋፍ ሰልፉን የሁሉንም በሚዲያ መቅረብ ብቻ ሳይሆን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ
ወጥተው ሲያመስግኑ የባህርዳሩን እንኳን ለማንሳት አልፈቀዱም የጉራጌ ህብሮቼ ጌጦቼ ሲሉ … እንኳን ማትብ የት ነህ አስኝቶኛል። እኔ ሁሉንም ነገር ነው እምከታታለው።
በ አዲሱ የ አብይ ካቢኔ ነፍሴ እዬተባለ ድፍን የሆኑ ነገሮች ሁኔታዎች ቢኖሩም አማራ አምላኩ አይተወውም፤ ሁሉንም ከእጁ ይጥለዋል። በዚህ
እንጽናናለን። ኦነግን ፈቅደህ ይህን ያህል እያስፏለልክ፤ አገር መውሰድ ትችላላችሁ መዲናዋም ይህችትልህ ተብሎ አማራ መሬት ላይ
አማራ ነኝ ማለት በሥውር ህግ መደንገጉ ጠፍቶን አይደለም።
ይገባናል። ልብ አለን።
ለዚህ ደግሞ መሪው አደራጁ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ዳብል ገጽን ተከናንበው እዬፈጸሙት ነው። የአብይ
ካቢኔ ቢወድቅም ቢነሳም አሳቸው እጥፍ መጠለያቸውን ያሰናዱ ልባም ሰው ናቸው። ኦነግም ቢመጣ ግንቦት 7 በሁሉም ዘርፍ በጣምራ ስንዱ ናቸው። በሦስት አራት እጥፍ መሰናዶ እያስኬዱት ነው።
አገር ጠቅሎ የገባውም በግማሽ ፊት ዕድል የምትጠብቀው
ገጽ አለ፤ … ሙሉ ሆኖ አላዬሁትም … ወንበሩም ሰው ተቀምጦበት አላዬሁትም
ባዶ ነው፤ ግን ይጠበቃል …
አማራ ልብ ይኑርህ! እንደ አባቶችህ ቅኔ ሁን! አንድስም እንኳን ስለ አንተ የሚጮኽ የሚተጋ
የለም። አትዘነጋ። አዲስ አበቤም አጀንዳ አይደለህም በአንድም ተፎካካሪ በለው ተቃዋሚ ቀረምት ላይ ነህ። ስለዚህም ተደራጅ በመረጥከው
መንገድ። „አንድ አገር አንዲት ኢትዮጵያ“ ካስኬደህም ሞከረው ብሄር አልቦሽ ነህ እና።
- · የመከራው ነጋሪት።
የዚህ ሁሉ መከራ ምንጩ ግን ያ የሰኔ 16 የድጋፍ ሰልፍ ነው። የዲያስፖራ ፖለቲካ መቀዬጡ ደግሞ
አደጋ ነበረው። ቅንጅትንም፤ አላያንሱንም፤ አንድነትንም፤ ቀድም ሲል ህብረትንም፤ አማራጭ ሃይሎችንም መቅኖ አሳጥቶት የቀረው ይኸው
ነበር።
ለማውያን የሆንኩትም ከዲያስፖራ የጸዳ ጥገኛ ያልሆነ ሰውኛ ተፈጥሮኛ መንፈስ ስለነበረው በኢትዮጵያዊነት ውስጥም ነው ብዬ አምኜበት ነው።
ነገር ግን ለዲያስፖራ ውጥንቅጥ ፖለቲካ የተጋለጠው ለውጥ ቅይጥ መንፈስ የመጣው በአሜሪካ ጉዞ ምክንያት ነው።
ከዛ በኋዋላ ነው ቅይጡ መፍንቀለ መንፈስ አና ያለው። ሁለቱም ወቅታዊም አስፈላጊም
ተፈላጊም አልነበሩም። ለብዙ አደጋ አዲሱን ተስፋ አጋለጡ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሩ ለሊሂቃኑ አማካሪ የላቸውም። ቢኖሩም ጥሩ መንገድ አይመሩም ... ዳብል ሚና ስላላቸው።
አማካሪ ስል ሙያዊ የሆኑ ማለቴ ነው። አሁን በአብዩ
መንፈስ ውስጥ አማራ ህዝቡ፤ የ አማራ ሊሂቃኑ፤ የ አማራ ታታሪዎች፤ የአማራ ጋዜጠኞች፤ የአማራ የጥበብ ሰዎች፤ የአማራ ጸሐፍትና በአማራ ሥም የተደራጁ ተገላይ እንዲሆኑ መደረጉ አብይ ካቢኔ አንካሳ እንዲሆን ተፈልጎ ነው፤ ይህ
ደግሞ ታቅዶ በስልት እዬተከወነ ነው። ደፍሬ እምናገረው ውጤቱ ውደቅት ነው … የመንፈስ።
ስለምን? ቅኑ አማራ አምላኩ ሁሉንም ከ እጁ ስለሚጥለው፤ የተከፈሰው ግነቦት 7 ኮሮጆ ልመና አማራ መሬት ነው ያለው፤ ወታደሮቹን በጭነት መኪና ልኮ እሱ በቻርትር ገብቶ ያው ልመና የሄደው አማራ መሬት ላይ ነው "አማራነት መንፈስ ነው" ጅልነት ግን ከእንግዲህ አይኖርም። ይሠራበታል።
መቼም አብዩ ኦህዴድ ከእኔ ጋር ነው የሚል ተረብ እንደማያመጣ ነው … የአብይ መንፈስ የራሱ
አልበቃ ብሎ አማራንም ለግንቦት 7 ህልም ማስረከቡን ልብ ሊለው ይገባል … ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንዲሉ ...
ለነገሩ ከኤርትራ ጋር
የለው ምክክርም በዚህ ዕድማታ ውስጥ የሚታይ ነው። የባከነ ታሪክ እንዳይኖር በሞኝ ክንድ ዘንዶ ነው ነገሩ … የአዲስ አበቤው
ዕጣ ፈንታ ከአማራ ጋር የማንን ታሪክም፤ ውለታ ግንባት የሚለውን ልብ ያለን ይገባናል።
በዚህ ሂደት አቅም እያጠራቀም ያለው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። እዛች ድርሽ የሚል መንፈስ
የለም። ውንዳታ! መረማመጃው አማራ ነው - ኩስምን። አማራ ህዝቡ ደግሞ ልቡን ይሰጣል ተብሎ አይታሰብም። ሥነ - ልቦናውን መንጠቅ፤ ታሪኩን መንጠቅ፤ ፍልስፍናውን
መንጠቅ ትውፊቱን መንጠቅ የተለመደ ቢሆንም የአሁኑ ትለውድ ግን ዳይናሚክ
ስለሆነ ንቅንቅ አይልም።
ከበዛ ከበዛ በዚህ አያያዝ መራራውን ነገር ሊያመጣ ይችላል … አማራ። የማይደፈረውን ሊደፈር
ይገደዳል - አማራ። ወደ ዛ እዬተገፈተረ ስለሆነ … አማራ በተራ ተጋዛ ነው ፈሊጡ ትናንት ለትግሬ ዛሬ ለኦሮሞ እኛ ወደ ለምለሚቷ
አገራችን ብናመራ ደግሞ ለጉራጌ ቀሪዋን ተስፋህን ይዘህ ተክዝ ነው ጨዋታው። ቁልፍልፍ - ጥልፍልፍ - ጥምንም ... ለዛውም ደግሞ ከ ኤርትራ ጋርም የተጀመረ ነገር አለ ...
ሌላው ባለቤት አልቦሹ ኢትዮጵያኒዝም ነው እሱ እዳሪ አዳሪ ነው። እሱም ሚዲያም፤ አክቲቢስትም፤
ጋዜጠኛም ያገኜ አይመስልም። ሁሉም ለወገን ለገኑ ነው። ከመረብ መለስ አይነት … ቁልፍልፍ - ጥልፍልፍል - ጥምልምል ---
ዕውነት ሳትደፈር ጣረሞት ላይ … ስንት ዘመን ትባዝን?
መኖር ከተፈለገ እውነት ይደፈር!
የኔዎቹ ኑሩልን።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ