ልጥፎች

ከጃንዋሪ 5, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የህይዋን መፈጠር ይሁን #የኖኽ መርከብ እናትነትን የማስቀጠል ሰማያዊ #ሚስጢር ነው ለእኔ ለሥርጉተ©ሥላሴ። እናት #አልቦሹ ነገ በእጅጉ ያስፈራኛል። አናት አልቦው ማግሥትን ሳስበው የውስጥ ሰላሜን ያውከዋል።

ምስል
  #የህይዋን መፈጠር ይሁን #የኖኽ መርከብ እናትነትን የማስቀጠል ሰማያዊ #ሚስጢር ነው ለእኔ ለሥርጉተ©ሥላሴ። እናት #አልቦሹ ነገ በእጅጉ ያስፈራኛል። አናት አልቦው ማግሥትን ሳስበው የውስጥ ሰላሜን ያውከዋል።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #የዕይታዬ ምንጭ የBBC ዘገባ ነው።   ጠበቃ አስረስ ዳምጤ የፋኖ መሪ ከመሆኑ በፊት የሚያደርጋቸውን ቃለ ምልልሶች በአትኩሮት አዳምጥ ነበር። የህግ ባለሙያወች ሰብዕናቸው ቁጥብ እና መምህር ስለሆነ ተስፋዬ የዘለቀ እንዲሆን አድርጎታል። ጠበቃ አስረስ ማረ ታስሮም ነበር። ይፈታ ዘንድ በትጋት ከሰሩት አንዷ ነበርኩ። የእስር ቤት ቆይታውም አጭር ነበር።   ይህን ዜና በአንድም በሌላም አዳመጥኩት። ውስጤ በእጅጉ አዘነ። ውስጤ ተረባበሼ። ስሜታዊ እንዳልሆን በመስጋት ዕይታዬን አዘገየሁት።    እናት ስለምን #ትገደል ? እናት ስለምን #ትሙት ? እናት ስለምን የባሩድ #ስንቅ ትሁን? እናት እንደምን #ቀባሪ ትጣ? እናት እንደምን #ይጨከንባት ? #እናት የሆነ፤ #እናት ያለው ሁሉ ማንንም ሳይወግን፤ ማንንም ሳያገል ብቻውን ሆኖ ከራሱ ጋር ይምከር።    ሴት የተፈጠረችው ለእናትነት ጸጋ ነው። እግዚአብሄር ፈቅዶላት እናት ትሁን፤ መሃን ያ የእዮር የእናትነት ተፈጥሮዋ ምንጊዜም፤ በየትኛውም ሁኔታ ይኖራል። ይህ ጸጋ በባሩድ ሲቀማ እጅግ ያሳዝናል። ትውልዱ ለዛውም በንጉሦች ንጉሥ በአጤ ቴወድሮሥ ሥም የተደራጄ አካል፤ ለሥሙ ክብር ሲል እንኳን እርምጃው ሥሙን በሚያስነቅስ ማንኛውም ተግባር ላይ ቁጥብ፤ የተረጋጋ እና ከስሜት የጸዳ ሊሆን ይገባል። ሁሉም እናት አለው። ፍጥረት እናት አልቦሽ አይፈጠርም። የነገ እናትነት፤ የማግሥት እማዊነት በዚህ...