ልጥፎች

ከኦክቶበር 22, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ተፈተነ።

  " #ሲለቁሽ ሜዳ ሙሉ፥ ሲይዙሽ #ጭብጥ ሙሉ።" የአበው እና የእመው ቅኔ።   "እንደ ኃጢያታችን አላደረገብንም፤ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።" (መዝሙር ፻፪ ቁጥር ፲።)   #ምዕራፍ ፳።   ከዛ ሁሉ የግፍ እና የጭካኔ ዘመን በኋላም እንዲህ #ማወክ አለመታደል ነው። ከዛ ሁሉ የስቃይ ዘመን በኋላም ከስህተት ለመማር አለመፍቀድ #ርግማን ነው። ከዛ ሁሉ የትውልድ እልቂት፤ የታሪክ ስደት እና የአብሮነት ሰቆቃም በኋላ የሚነገረውን መስማት አለመቻል #ህመምተኝነት ነው።   በሰው ልጅ ላይ ቅንጣት የበደለ ሰብዕና ቁሞ መሄዱን ሊያከብረው ይገባ ነበር። መልካም ዕድል ለእነሱ ተንበርክኮ፤ ሰግዶም ለምኖ አልተሳካም። #ፈሰሰ ።   የስንት ትዳር ጎጆ ፈረሰ? ዘመን - #ይቁጠረው ። የስንት ወጣት ተስፋ አረረ? ጊዜ - #ይስፈረው ። ስንት ስደተኛ እንደወጣ ቀረ? ወቅት - #ይመትረው ። ስንት ህዝብ ሰማዕት ሆነ? ዓመታት - #ይለኩት ። ስንቱስ አካሉን አጣ? ሰዓታት - #ይዳኙት ። ስንቱስ የአልጋ ቁራኛ ሆነ? ደቂቃት - #ይመስክሩት ።   ህወሃት ከተጠነሰሰበት ዕለት ጀምሮ የሰብ፤ የተፈጥሮ፤ የአደራ፤ የትውፊት፤ የታሪክ፤ የዕውቀት፤ የአንድነት የተፈጥሮ ክስለት። የቂም የበቀል የጥላቻ ህንፃ ተገነባ። ኢትዮጵያ ምን አተረፈች? ሰው መሆናችን በእጅጉ #ተፈተነ ።    የሚገርመኝ ሥርዓተ አልበኝነትን #አና ብለው፤ ከህግ በላይ ሆነው፤ የተደራጀውን በማን አለብኝነት ንደው።እራሳቸውን ሹመውም እንዳሻቸው ሲሆኑ ባጁ።    #ቁንጣኑ አላስችል አለ። ለዛ ለተቆርቋሪያቸው፤ ለሚደክምላቸው እንደ በኽረ ልጅም ለሚያቸው ለአሜሪካ መንግሥት በንቀት በራቸውን ዘግተው ተመላሽ አደረጉ። እንግዳ እንዲህ...

የኢትዮጵያ ሊቃናት ይሁኑ ሊሂቃናት የማሰብ፤ የመናገር ነፃነታቸው ከተገደበ #አመክንዮ #ፎርምለስ ይሆናል።

  የኢትዮጵያ ሊቃናት ይሁኑ ሊሂቃናት የማሰብ፤ የመናገር ነፃነታቸው ከተገደበ #አመክንዮ #ፎርምለስ ይሆናል።   ሁሉም የሚፈልገው ማስገበር ብቻ ነው። "አንተ ምድር ነህና፤ እሷም ምድር ናትና፤ አንተ ትቢያ ነህና እሷም ትቢያ ናትና፤ አንተም መሬት ነህና፤ እሷም መሬት ናትና፤ ከእሷ የተገኜውን እህል ትመገባለህና ወደ እሷም ትመለሳለህና፤ ያነሳህ ዘንድ እስኪወድ ድረስ መሬት ትሆናለህና፤ የሠራኽውን ኃጢያት እና በደሉንም ሁሉ ይመረምርሃልና።" (መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፫)   #ምዕራፍ ፳።   እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ - ቅንነት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።   #የኔታዊወሊሂቃን ።   ቢያንስ እኔ ላንሳው ብዬ እንጂ የኢትዮጵያ ሊሂቃን እንኳንስ ሃሳብ ሊያዋጡ፤ ይቅር እና በየዘመኑ መኖር በተፈቀደላቸው። ይህ ለረጅም ጊዜ በሰንሰለት የታሠረ ጉዳይ ነው። ዊዝደም ከታሠረ ድፍን ፷ ዓመታቱ ነው።    የኢትዮጵያ ሊሂቃን እራስ እግራቸው ዊዝደም ናቸው። ጸጋቸው፤ በረከታቸው ከባችለር፤ ከማስተር፤ ከዶክትሬት ዲግሪ አይቀዳም። ከእዮር እንጂ። አልፎ አልፎ አስኳላየን አክለው ሲገኙ ደግሞ እራሳቸው #ፕላኔት ሊሆኑ ይችላሉ።    የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዳጡ ይሁን ረግረጉ ይኽው ይመስለኛል። አንዱን ይዞ ሌላውን አንጠልጥሎ ስለሚሆን። የኢትዮጵያ ሊሂቃን አገር - ያበጁ፤ ፊደል - ቀርጸው ዕውቀትን መልክ ያሳያዙ፤ ቀለም ሠርተው ጥበብን አቆላምጠው ለኢትዮጵያ ስልታዊ ትንፋሽ መርኽ የሆኑ፤ ሥልጣኔን አበክረው መኖርን ያዘመኑ ናቸው።   ሳይንሱ፤ ፍልስፍናው፤ ምርምሩ ምጡቅ ዕይታው ጸጋውን ከባረከላቸው፤ ከሰጣቸው ይቀዳል። ግን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ የተገለሉ ብቻ ሳይሆን ...