ያላለቀ መከራ ሰርካዊነት።
ማንዘርዘሪያ። „ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላሁ።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ 16.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ትናንት እና ከትናንት በስትያ ሌሎች ተግባሮችን እዬተከታተልኩኝ የተሰጡ መግለጫዎችን አዳምጥ ነበር። በመጀመሪያ የአቶ ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ መግለጫ ከውጭ ለሚመጡ እንግዶቻችን አዲስ አበባ አቀባባል ታደረግለች የሚል ዕድምታ ነበረው። ኦነግ እና ግንቦት 7 ብቻ ነው ወይ በስታዲዬም ደረጃ አቀባበል የሚደረግላቸውን ያሰኛል? የኦጋዴም፤ የአፋርም፤ የትግራይም፤ የአማራም፤ ኢትዮ መንፈስ ያለቸው የሲቢክስ ድርጅቶች መሪዎች እኮ ከዚህ ቀደም ገብተዋል። ምነው የዜግነት እሮብ እና ሲሶ ነበረውን ወይንስ አለውን? ሌሎቹ እኮ ከነመፈጠራቸውም አይታወቁም። በአክቲቢስት ደረጃ የኢትዮ ሱማሊያ፤ የአፋር፤ የአማራ፤ የጋንቤላ /ኢትዮ/ ገብተዋል እነሱስ ዜግነታቸው የእንጀራ ልጅነት ያህል ነውን? ለነገሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሚሊዬነም አዳራሽ ንግግር ሲያደርጉ ሁለት የኦነግን ክንፍ ሲጠሩ፤ ሌሎችንም ሲዘረዝሩ አንድም የአማራ ድርጀት ሊሂቅ ሲጠሩ አልሳማሁኝም። አንድም የአማራ አክቲቢስት ሲያወሱ አልሰማሁም፤ ዶር አብይ አህመድ አብነት በሆኑበት በጎ አደራጎት ደግሞ አዲስ አባባ የከንቲባ ጽ/ቤት መልካም ተግባር ሲከውን ሰነባብቷል። ለነገሩ የብአዴን የካባ እና የጃኖ ልዩ ዝግጅትን እወክላለሁ ለሚለው አማራ አብራክ እና መህጸን ለተገኙ ሊሂቃኑን ሲቀበልም ሲያሰተናገድም ክብር ሲሰጥም አልታዬም። ይህ የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሌጋሲ መሆኑ ባይጠፋኝም ፊት የተነሱ ዜጎች መኖራቸውን ግን ግልጥ ሊሆን ይገባል። አማራም ይህን ከታሪክ እዬተጋፋ ስለመሆኑ ማወቅ ይኖርበታል። ባይታወርነቱ ቀጥሏል ለዛውም በተደ...