ቅብጥ እና ቅልጥ ያለች ወግ ቢጤ ...

ያሰረብኝ
„ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ
 በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ
በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
16.09.2018
ከሰላማዊቷ ሲዊዘርላንድ።

  • ·        እፍታ።

ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁን? እኔ አለሁላችሁ። ይህ እንደግዲህ ካልተተመው 8ኛው መጸሐፌ ውስጥ ያለ ወግ ቢጤ ነው። ያው ግንቦት 7 ኢትያጵያ ላይ ዴሞክራሲን ሊሳዬን ከሄደ እንደ ሶሞናቱ ገለጣ ማለት ነው ትንፋሽ ይገኛል ማለት ይሆናል። ይህ ማለት እንገናኝ ይሆናል በመጣጥፉ፤ በትርካው በሥነ - ግጥሞ በፍቅራዊነት ፕሮጀክቱ፤ በ አጫጫር ፊልም ... ወዘተ እንደ ፈቃዱ ቤተ የቅኖች ማዕዶት ቢኖረን ተብሎ ተስልቷል። አሁን ሲዊዝሻ ነጣነቷ እያታወጀላት ነው።
 በማዕቀብ - በክትር - በገደብ በወያኔነት ፍረጃው አክትሟል „የዛሬ 6 ወር ያለሰብነው እዬተባል ነው“ „መነገድ እና ትንሳኤ እኛ ነን“ ተብለን ነበር። ዛሬ ደግሞ ሌላ ጨዋታ መጥቷል። ለካንስ እንሱም በድርጅታቸው ተስፋ አጥ ኑረዋል። ሆድ ያባውን ሆነ እና የምናውቀውን እያሰሙን ነው …
የሆነ ሆኖ ዕድሜ ለአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ እና ለቄሮ ንቅናቄ። እንዴት ነው ብአዴን ተዚህ ላለውም ወገኖቹስ የጃኖ ገብያ ቢከፍት ምንአለበት? እይመስላችሁንም?  የንጉሡ የጃኖ ሌጋሲ ቤት ተብሎ፤ ለእኛ ደግሞ ሙለወርዷን … ወጉ እንዲህ ቀርቧል …
  • ·        የወግ ገበታ።

           ውይ ውይ ውይ … እ! እ! እ! አቃሰትኩ። አምላኬ ምስክሬ ነው በጢንብራዬ ሊዳፋኝ … ፈተለኝ። ሲፈትለኝ ዘኃም ግራም … ጥጡም … ጥጥፍሬውም የለም …. በልሙጡ ... ሊደጠኝኝኝ እም ... 

ብቻ ብቻ ብቻ የዛሬው የጉድ ነው። መጥቶበታል አልኳችሁ መጥቶበታል። አቤት! ምኑን ነው ያሰረብኝ? ዝም ብሎ ድንቡልቡል ግን አንቦልቡሎ የሚልክለት ያሰኛው …

እህ! አሰኘው … ጥድፊያ በጥድፊያ … ችኮላ በችኮላ …. ፍጥነት በፍጥነት … እሰይ!እንዲህ አድርጎም የለም ... 
እእ! እሰይስ  አይባልለትም ፋታ ነው ሊጠዬቅ የሚገባው። ድምጼን ጮህ አድርጌ „ ይቀረጽልኝ!“ ስል ቆዬት ብዬ ደግሞ „ፖሊሲ!“ አልኩ እሱ እቴ ፓሊስ ያልኩት ይመስል „የመጣ ይምጣ!“ ሲል በልበ ሙሉነት በተደላደለ ምላስ ገለጠልኝ።

ጎሽ! ይገባል! እውነት ነው! ይደርደሩ ወኔ ሲገኝ … አነጣጥሮ ብልቱን የሚል … አነጣጥሮ በሃሳብ ጥራት አናቱን የሚል የጉብራን ጩኸት የሚያስታግስ ወኔያም ከተገኘ እኔ ልሙት ለምኜ - ተንበርክኬ -ጾሜ= ወድቄ ተነስቼ - ሰግጄ በልቡ ውስጥ ክትም። 

„ታድለሽ“ በሉኛ አንበሳውን ባለጋማ ደም መላሹን። ተዚህ ላይ ግን ...--- የድል አርበኛ በአቋራጭ ሳገኝ ማን እንደ እኔ ጌታ … እሰቡት የድል አጥቢያ አርበኛ አላልኩኝም… በምለሱ ውልፍት የማይል የወጀብ ቤተኛ ያለሆነ እንደ ማለተ …
ውይ ጩኽቱ … አንከባለለው፤ ዱብ ዱብ አደረገው' ሰጊድ ለኪም አልቀረለትም። … እንደ ነሃሴ ዝናብ በዶልዶሌ አንዶለደለው - ዕንባውን። „ጫረኝ - ፈጀኝ - ጨረሰኝ - „ እያለ ለቀቀውውው --- ኡኡታውን፤ በለው... ህም።

ተንደፋድፌ አራቱንም ኖ! ሶስት ነው ያለን ሶስቱን ምድጃ፤ ሶስት ብረት ድስት ጣድኩና … ሽንኩርት ፍለጋ ፍሪጁን ክፍት ሳደርገው … ምደረ በዳ … ይህን ሲያይ አያጅሬው አምላካችሁ አለ ዘልዝሎ ሊበላኝ ምንም አልቀረውም …
ወይኔ ጉዴ እንደ ነገሩ አዛንፌ ለብሼ ያቺው የላስቲክ ኮረጆዬን ይዤ ብጥል ብዬ ስውጣ … ስልክ ጮኽ … ወይ ደግሞ ያው የልቤ ይሆናል ብዬ ስልኩን ላነሳ ስል ከእጄ ሞልቅቆ ልሞት ነው „ ሞት ፈረደችብኝ ብሎ“ ለምን አያባርቅም መሰላችሁ?ዖዬ ... 
 … "እናት ዓለም መልሰህ ትደውል?" ስል … ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁ „እሳት አደጋ ስለተነሳ በአስቸኳይ ልቀቁ!“ የራሱ ጉዳይ! ብዬ ዕንባውን እረግጬ ስሄድ ገደል ጠበቀኝ … እንዴት ልሻገረው …. ተግባር ብሰጠው በታገሰልኝ ነበር፤ ግን ከምጡ ወደ ረመጡ …. 
             አለዬሁህም ብልህ
                    የትውልድ መንፈስ ቅንና ብልህ
             ድርሻን ከትሜ እንደመጣልህ
             ራህብን ላክልኝ ልትፈትነኝ
             በድርጊት ፈትሎ ሻማ እንዲሆነኝ
             ሸማ አቅልሜ - ውስጤን እንደ አበጀው
ገላውን አሳዬኝ የወገኔን የሁነኛው
ከናፈቀኝ ጋር ሊገናኘኝ
ማልዶ ቀረበ ለህሊና
በቃኝን እንዳቀርበው እንድለው ናና …
… ያ … የቀን ቀና!
·       መውጫ።
ጡሁፈ በ2013 የተጣፈ ነው። ሊታተም የተዘጋጀ ነው። ቀን ከወጣለት ይታተማሉ ከቤተኞቹ ጋራ። ክብሮቼ ውዶቼ ዛሬን በዚህ እንከውነው። 

ያው ትናንት ለቅኖች እንደነገርኳችሁ በግድፈት ቻፕተር ሦስት ነው ያልኳችሁ አራት ነው። እሱን አጠቃልዬ መስራት አለበኝ እና ዛሬ ወደዛ ዞር ልበል። ትናንት ተሰርቶ የተለጠፈው የቻፕተር 4 ኮንፓክት ከታች ተለጥፏል … ስሰራውም „ሦስት“ ያልኩት ግድፈት ነው አራት ተብሎ ይታረምልኝ። ትናንት ደክሞኝ አላረምኩትም።

የፍቅራዊነት ተፈጥሯዊ መርህ የቃላት ፓስተር ነው።ሃሳብ የቃላት ዲዛይን ነው። የፍቅራዊነት ተፈጥሮ ሌጋሲ ሊባል ይችላል። ሰርቶ ማስቀመጥ ምን አልባት አንድ ቀን የተበረከ ሰው ያስቀጥለዋል። ሰው እና እንጨት ተሰባሪ ነውና። እኔ ሳልናገረው ከማልፍ ተናግሬው፤ ለመነሻ የሚሆኑ አቅጣጫዎችንም ብተልም ይጠቅማል በሚል ነው። ሃሳብን ማውጣት … ማዋጣትም ይጠቅማል። 

ፍቅር ስለተባለ ፍቅር አይገኝም፤ የፍቅር ተፈጥሮ በትምህርት፤ በሙያ ተቋማዊ በሆነ ሁኔታ እንጂ በወጀብ እና በአውሎ ወይንም በጎርፍ ሙላት እና በዝናብ አይገኝም። እርግጥ ዝንባሌ ያላቸው ታታሪዎች፤ የጥበብ ሰዎች ቅኖችም ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን በሁኔታዎች ህግጋት ሳይሆን የፍቅር ተፈጥሮ የመዋለ ዕድሜ አንድ የዕውቀት ዘርፍ ነው። የነፍስ ፕሮጀክትነቱ ውቅያኖስ ነው ሊማሩት ሊመረቁበት፤ ማህያም ሊያገኙበት የሚገባ። ኤክስፐርቶች፤ ፈላስፋዎች፤ ሙሁራን፤ ሊቀ ሊቃውንታት ሊጠበቡት የሚገባ 13ኛው ፕላኔት ነው።

ፍቅር ታታሪ ቋሚ ተቋማት፤ ቋሚ ኮሌጆች፤ ቋሚ ዩንቨርስቲዎች ያስፈልጉታል። በስተቀር ፍቅር ቅዳሜ ገብያ ማለት ይሆናል። ገብያተኛ እና ገብያው አንድ ላይ ያወካካሉ ለአፍታ፤ ገብያው ሲፈታ ወና ይሆናል። በዚህ መልክ የፍቅር ተፈጥሮ አይደፈረም። እንደ ሰሞናቱ የስታዲዬም ውሎ እና አዳር … የህሊና አጠባ ተቋም ያስፈለገዋል። ካሪክለም ያስፈልገዋል። መደበኛ ተግባር ነው። 

የፍቅር ተፈጥሮ ፍልስፍናም ሳይንስም ነው። ይህን እራሱ ፕላኔታችን አልተቀበለችውም። በ2015 ላቀርብኩት ማመለክቻ የተባባሩት መንግሥታትም አውሮፓ ህብረት የሰጡት መልስ እጄ ላይ ይገኛል።

የሆነ ሆኖ የፍቅር ተፈጥሮ ሊጣነ፤ ምርምር ሊደረገብት፤ ስክንት ባለው ሁኔታ ጥልቀቱ ላይ ሰፊ ውይይት፤ ዲያሎግ ሊካሄድበት የሚገባ ነው። አንድን የፖለቲካ ድርጅት አፍቅረህ ወደህ ፍቅርን ማምጣት አይቻልም። 

ፍቅር ደንበር የለውም ሲባል ከዚህ ይነሳል። የፍቅር ተፈጥሮ ከፈጣሪ በታች ከነገሮች ሁሉ በላይ ነው። አንድ ምሳሌ ባነሳ እሳተ ጎመራ የሚወድ ሰው ለተፈጥሮ ፍቅር ስላለው ነው። ደን የሚወድ ሰውም እንዲሁ።

የሆነ ሆኖ ቻፕተር አራት የፍቅርን ተፈጥሮ ከእውቀት ጋር ያወዳደረ ነበር። ኮንፓክቱ ተሰርቷል፤ ተካታዩም ኮንፓክትም እንዲሁም ሳመሪውም ይቀጥላል የወደዳችሁ ጎብኙት -  በአክብሮት።
Compact 24, Chapter Three 09.15.2018 (Comparison)

መፈጠረን ያከበረ ተፈጥሯል!

የኔዎቹ ክብረቶቼ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።