የቅጣት ፍርሃት።
በጥምር ምልክት ጥምር የቅጣት ፍርኃት። የእዮር አደባባይ ደወልን እንዴት ተረዳነው? ከሥርጉተ - ሥላሴ ( Sergute © Sselassie ) 09.05.2018 (ከገዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ።) „እንዳይቈጣባችሁ አንድ ጊዜም እንዳያጠፋችሁ፣ ቀድሞ ከኖራችሁበት ተቈጥቶም በመከራው እንዳይገርፋችሁ፤ ቀድሞ ከነበራችሁበት ተቈጥቶም በመከራ እንዳይገርፋችሁ፣ ቀድሞ ከነበራችሁበት ካባቶቻችሁ ሥራት እንዳትወጡ፣ ማደሪያችሁም እስከ ዘለላሙ ድረስ መውጫ በሌለበት በገሃነም እንዳይሆን ከትእዛዙ ከህጉ አትውጡ “ ( መጸሐፈ መቃብያ ሣልስ ፱፲፱ “) · መነሻ። ሰሞኒትን በድንጋጤ እና በትፍስህቱ አዋድጄ ለማቅረብ አሰብኩኝ። የልዕልት ኬኒያ „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ግርማ ሞገስ አቀባበል ይምጣልኝ ስትል ልዑካኗን አዲስ አባባ ድረስ ቀድማ የፍቅራዊነት ሐዋርያዊ መልዕክተኛ መላኳ ብቻ ሳይሆን፤ መሬት ላይ ለጣና ዘገሊላው የግዮን ትምህርት ታምር የሰጠችው ወደር የለሽ አክብሮት እና ልዕልና ከእዬመጣ ያለውን ደመመናዊ ሰማያዊ ቁጣ እጀባ ውስጥ እኛዊነትን አክዬ ለማተያዬት አስቤያለሁኝ። አዋድጄ ለማቅረብ። ማሳብ መልካም ነው፤ ሃሳብን ከብራና ጋር በቀለም ማዋደድም ደምሞ ማቅረቡ ደግሞ የበለጠ ነው። ግን የኔዎቹ ቅኖች እንደ እኔ „ሞኝነት“ የፈቀዳችሁ የዋህ፣ ቸር እና የእኛዊነት የፊት ግንባሮች እንዴት ሰነበታችሁልኝ። ኢትዮጵያን መውደድ ቋንቋ ሳይሆን በመሆን ውስጥ ፈተናውን መሸከም ማለት ነው - ለእኔ። እሱን በሚያድን መንገድ የፈጣሪ ተመስገን በመቁንን ሳይሆን፤ በደርበብ ሳይሆን፤ ...