የቅጣት ፍርሃት።

በጥምር ምልክት ጥምር የቅጣት ፍርኃት።
የእዮር አደባባይ ደወልን እንዴት ተረዳነው?
 ከሥርጉተ - ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
  09.05.2018 (ከገዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ።)
 „እንዳይቈጣባችሁ አንድ ጊዜም እንዳያጠፋችሁ፣ ቀድሞ ከኖራችሁበት ተቈጥቶም
 በመከራው እንዳይገርፋችሁ፤ ቀድሞ ከነበራችሁበት ተቈጥቶም በመከራ እንዳይገርፋችሁ፣
 ቀድሞ ከነበራችሁበት ካባቶቻችሁ ሥራት እንዳትወጡ፣ ማደሪያችሁም እስከ  ዘለላሙ
ድረስ መውጫ በሌለበት በገሃነም እንዳይሆን ከትእዛዙ ከህጉ አትውጡ
(መጸሐፈ መቃብያ ሣልስ ፱፲፱“)


  • ·         መነሻ።

ሰሞኒትን በድንጋጤ እና በትፍስህቱ አዋድጄ ለማቅረብ አሰብኩኝ። የልዕልት ኬኒያ „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ግርማ ሞገስ አቀባበል ይምጣልኝ ስትል ልዑካኗን አዲስ አባባ ድረስ ቀድማ የፍቅራዊነት ሐዋርያዊ መልዕክተኛ መላኳ ብቻ ሳይሆን፤ መሬት ላይ ለጣና ዘገሊላው የግዮን ትምህርት ታምር የሰጠችው ወደር የለሽ አክብሮት እና ልዕልና ከእዬመጣ ያለውን ደመመናዊ ሰማያዊ ቁጣ እጀባ ውስጥ እኛዊነትን አክዬ ለማተያዬት አስቤያለሁኝ። አዋድጄ ለማቅረብ። ማሳብ መልካም ነው፤ ሃሳብን ከብራና ጋር በቀለም ማዋደድም ደምሞ ማቅረቡ ደግሞ የበለጠ ነው። ግን የኔዎቹ ቅኖች እንደ እኔ „ሞኝነት“ የፈቀዳችሁ የዋህ፣ ቸር እና የእኛዊነት የፊት ግንባሮች እንዴት ሰነበታችሁልኝ። ኢትዮጵያን መውደድ ቋንቋ ሳይሆን በመሆን ውስጥ ፈተናውን መሸከም ማለት ነው - ለእኔ። እሱን በሚያድን መንገድ የፈጣሪ ተመስገን በመቁንን ሳይሆን፤ በደርበብ ሳይሆን፤ በቁንጥር፣ በጭብጦ ገለመሌ ሳይሆን ራስን በመስጠት፤ የተለጠጠ ፍላጎትን በማማዛዘን ሊሆን ይገባል ይላል የሥርጉተ ሥላሴ ፈንገጥ ያለው ህሊና። ብላክቦርዱና ቾኩ ብቻ ሳይሆን ሰነዱም ሁሉ ፈተና ላይ የተቀመጠበት ዘመን ነው። ዘመን ጥሩ ነው እንዲህ መስታውቱን ገዝቶ ይሸልማል። ምሪታችን „የዳማዋን፤ የቀዮዋን፤ የጠይሟን፤ የቡኒዋን“ ልሳነ ነባቢት ህያዊተ - ህላዊነት በሚመለከት የትና እንዴት ነን --- ለመሆኑ?
  • ·         በብሄራዊ ስሜት ስለመጨነቅ ግን እንዴት?

„አስደንጋጭ ዜና በጉራጌ አካባቢ በተፈጥሮ መሬት እንደ ዳቦ ለሁለት ተቆረጠ“
ውድ የዘሃበሻ አዘጋጆች አጅግ አድርጌ አመሰግናችሁ አለሁኝ እኔ የዘወትር ታዳሚያችሁ። ጉዳያችን ውስጣችን ባትሉት አትለጥፉትም ነበር። ከዚህ ቀጥሎ ያለው በጸሎት እንደ ዕምነቱ መትጋት ነው አቅም ያለው። ጸሎት ሃይማኖታዊ ህይወት ነው የነፍስ መድህን። ጸሎት ህይወትን ተናባቢቱን ይታደጋል። ነፍስን ይመልሳል። ምድርን ያድናል። ጽናተ ትእግስትን ያጸደያል። የእርቅ ድልድይን በካስማ ሃዲድነት ከምድር የደካ እስከ እዮር በአድዮሽ ይዘረጋል። ሌላው ቢቀር ቢያንስ - ያጸናል። ውስጥን በፈርኃ እግዚአብሄር ያንጻል። ፖለቲካ ካለ ፈርኃ እግዚአብሄር የዱብሽት ቤት ነው። ጸሎት ተስፋውን በፈጣሪ ደግነት፤ ምኞቱን በአምላክ ቸርነት ርህርና፤ በአደኖይ ኪናዊነት ያደርጋል። መከራችን ገና አላለቀም። እንዳያልቅም ራሳችን ሊጋባዎች ነን። ይህ ዕውነት ነው። ዕውነት እና ዘመን ገጥለገጥ ሲገናኙ አስተዋዩ ምልዕት በዝግታ ለመራመድ መወሰን ይኖርበታል። ምድሪቱ በተለያዩ መርገምቶች ልዑል እግዚአብሄር በእነ ወደ ኋላ አንመለስም እንዳይመታ፤ ከዘመነ ፈርዖን መማር በእጅጉ ያስፈልገናል። አካል የሌለው የልዑል እግዚአብሄር ቋሚ አገልጋይ ቅዱሱ መጸሐፍ ለአማንያኑ የገሃዳዊ መርህ የእጅ ሥራ አይደለም። የቃል መጠበቂያ የገነት ተክል እንጂ።
  • ·         ሳይንስና ሰሞኒት እንደምን እዬተኳኳኑ ይሆን?

የሰውኛ ሟርት በገፍ ስንለቃቅም ሰነባበትን። ፈጣሪን አቤት ብለን፤ በቀሪው ላይ የሆነውን ሁሉ በጥበብ ክህሎቱ ለፍጻሜ ያደርሰው ዘንድ መትጋት ሲገባ ሰው ሆነን ተፈጥረን ግን የተፈጠርንበትን የምስጋና ሽራፊ ነሳነው። እሱ በክህሎቱ ምክንያት ፈጥሮ ለላከው የምህረት ምልክት አክብሮቱ ቀርቶበት አስከፋነው አንድዬን፤ ከክብራችን ዝቅ ብለን በራሱ ውሳኔና ሥራ ገብተን የሰውኛ ሟርት ቤተኞች ስንሆን፤ እነሆ እዮር ቁጥር ሁለትንም ሦስትንም አከታትሎ በጣምራ ቅጣት፤ በጣምራ ሰማያዊ ቁጣ በሙላት፤ መሬትን ከሁለት ሰነጠቃት። ያ መሬት ኢትዮጵያዊ መሬት ነው። የእኔም የእርስዎም። ያ ተፈጥሮ ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮ ነው። ቀድሞም ምልክት ሰጥቶ እንደነበረም ከቃለ ምልልሱ ተረድቻለሁኝ። ምልክቱ የመቀሌው ቁጥር አንድ ተከታይ ቁጥር ሁለት ነበር። የዝናቡ ሁኔታ ባልተለመደ ዱብ እዳ እንደ ነበር፤ በርካታ ወገኖቻችን ከኑሯቸው እንደተፈናቀሉ አሁን በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ፤ በዚህ ውስጥ ህፃናት፤ ነፍሰጡሮች፤ አዛውንታት፤ አቅመ ደካሞች፤ ጤናቸው የተጓደለ ይገኙበታል። ቁጥር ሦስቱ ደግሞ መሬት መሰንጠቁ ያልተለመደ ድምጽንም ምራኝ ብሎ መሆኑ ጆሯችን ለቀረቀርነው ወንበርተኞች ሁሉ አስደንጋጭ መልእክት ልኳል። ወንበራችን ጆራችን ነውና። አሁንም ከዛው ከገህዱ ዓለም ያልተወጣው ፍልስፍና „ከአፍሪካ የተነሳ አፋር ሊደርስ እንደሚችል በዝግምተኛ የተከሰት ነው ይላል የሳይንሱ እፍታና አፍ። የመቀሌው ይሄ ከፍተኛው ነው ከእንግዲህ የሚከሰቱት አናሳዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ እንገምታለን“ የሚል ማህል ላይ የገተረን ተሜንት ነበር። አሁን ከዛ አልፎ ጉራጌ ዞን ላይ ደርሷል። ነገስ የትኛው ቀዬ ላይ? ሳይንስና ሰሞኒት እንደምን እዬተኳኳኑ ይሆን?
  • ·         ዘመኑ አንድ ወራቱ የተጠጋጋ ስለመሆኑ፤ ግን ስለምን?

የወራቱ ተቀራራቢነትስ በምን ምድራዊ ሳይንስ ሊቀመር ይሆን? ኢትዮጵያ ያለችበት የፖለቲካ እሰጣ ገባስ ፊዝክሱ ባሊህ ብሎ ሹክ የሚለን ሚስጢር ይኖር ይሆን? አፋርን ዘሎ ሌላ ቦታስ ቢከሰትስ ምን ልንባል ይሆን? ትግራይ ላይ ቀደም ብዬ እንዳወሳሁት „ይህን ትልቁ ነው ብለን አስበነዋል ቀሪው ትናንሽ ነው“ ሲባል አሁን ያን ቀዬ ተወት አድርጎ በጦፈው የጉግስ ቀዝቃዛው የአራት እንጨት እግር ጦርነት መሃል ሌላ  የእዮር ጣምራ ቁጣ በጣምራ ቅጣታዊ ቀለም ተክስቷል። ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ከፈጣሪ ጥበብ ጋር እንዴት እና እንዴት ሆነው፤ መቼ እና መቼ ሊገናኙ ይችሉ ይሆን? „የፈርዖኖች አስተዳደር መሪ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ችግራችን የልማት ነው፤ ያለብን ችግር የመልካም አስተዳደር ነው፤ የድህንት ነው“ እንደሚለው ፌዝ ነው - ለእኔ። ሰው እኮ በቢላዋ እዬታረደ ነው። የዘር ማፍሪያው ከነተፈጥሮው እዬጠፋ ነው። የተፈቱትም መቆምም፤ መቀመጥም አልቻሉም፤ ባሊህ ባይ አላገኙም። ባለቤት አልቦሽ ናቸው። አንዲት አንስት በመዳህኒት ስትፈዝ ዛሬ አይታወቃትም። ለዛውም ለቀናት የዘለቀ ነፍስን የመሳት ሰቆቃ። የአማራ ተጋድሎ ታታሪት ጀግኒት ወጣት ንግሥት ይርጋ ለቀናት ሰውነቷን አደንዝዘው ነበር ሁሉን የቀራንዮ፤ የጎለጎታ ሰቆቃ የፈጸሙት። ገድለው ነበር በቀላቸውን የተወጡበት። ምን እንዳደረጓት አይታወቅም። የተሰጣት መዳህኒት ዕድሜዋ እዬገፋ ስሄድ መዳህኒት የማይፈውሰው መከራ ልትሸከም ትችል ይሆናል። ይሄ ብቻ አይደለም በሼህ አላሙዲን የወርቅ ማዕድን የዕደሳት ዘመን ቀጣይነት በምልሰት ሲቃኝ ዘርን ሽባ የማደረግ ዓላማ ከጣና እንቦጭ ጋር ታቅዶ የተከናወነ ነው - ለእኔ። የጣና ሩቅ ቪዥን ቀመር ፈላስፋ የ31 ዓመቱ ጥበባኛ በታቀደ የመኪና አደጋ፤ እያለ የሌለ በቁሙ ፍዳን እንዲቀበል የተፈረደበት አሳረኛ ሊቀ ሊቃውነቱ ወጣት ጸሐፊ ራዕዬኛው ወጣት ምስባከ ወርቁ ዛሬ መናገርም ማሰብም አይችልም። በሰላይ እና በስልት ከእጃቸው አስገቡት፤ ሁለመናውን በትእዛዝ ሥር አሰሩት በሳጅን በረከት ጋንታ የደህንነት ኔት በድኑን አስረክበውናል። „አማረነት ዕዳ ነው“ የእነ ሳጅን በረከት ስምዖን ግፍ ገናም ብዙ አለበት። ዛሬ የማናዬው ነገ የምንሸከመው የመከራ ቁልል። ማግስት ከዚህም የባሰ ዓይን ከሚቸለው በላይ ጉድ ይኖረዋል። አጀንዳ ሆኖ አስቸኳይ መፍትሄ ካልተሰጠው። እርግጥ ችግራችን ሰው ከሚችለው በላይ ነው  … ከብረት የተፈጠረም አይችለውም። ይህን መተርጎም ተስኖን ነው ፍላጎታችን አንጠራርተን መንፈስ ስንበትን ውለን እምናድረው። ቅንጦች¡ ዘመናዮች¡ ትርምስ ጠማኞች¡
  • ·         መርማሪ።

ከትናንት በስትያ ቀን ላይ ነበር ይህን የመሬት መራድ ዜና እያንቀጠቀጠኝ ያዳመጥኩት። አሁንም እንደ ቁጥር አንዱ የመሬት መራድ ኢትዮጵያዊው ሰው ውጪ ሐገርም ሆነ ሀገር ቤትም በተገባው ልክ ያሰተዋለው አይመስልም። ድንገቴው ባለተራረቁ ወሮች የተከወነ ነው። ስለምን እንዲህ እና እንዲህ ሆኖ ተጣመረ። እራሱ የዜናው አሰራር ውስጤን እየመረመረኝ ነበር ያዳመጥኩት። መጀመሪያ የሰማሁት ከወያኔ ጭንብል ከቅቤ ጠባሹ ኢቲቪ ነበር። ትናንት ጥዋት ዘሃበሻን እንዴት አደርክ ስል በድጋሚ አገኘሁት። ወደ 400 የሚጠጉ ወገኖቼ ቅኖች ሸር አድርገውታል። ተባረኩ! በዚህ ውስጥ አንድ ቀንጣ/ አንዲት ቀንጣ ሊሆን / ልትሆን ትችላለች ንጽህና ያለው/ ያለት መንፈስ ማረን፤ ማህክነ፤ ተሳህለን ካለ / ካለች ይበጀናል። እግዚኦታ ያስፈልገናል። ልዑል እግዚአብሄር ለአንድ ቅዱስ ፍጥረቱ ሲል ብዙ ነገር ይታደጋልና። ህብራዊ ካደረግነው ደግሞ ጉልበቱ ይጨምራል።
ታስታውሱ እንደሆነ የመጀመሪያውን ቁጥር አንድ የእዮርን ደወል መልዕክት ስጽፍ ደወሉ ለትግራይ ብቻ ሳይሆን ብሄራዊ፤ አህጉራዊ እና ግሎባለዊም ነው ብዬ ነበር። በመሬት መራድ ላይ የሚመጡ ቀውሶች፤ ከሰዎች አቅም በላይ ስለሚሆኑ ዓለምም እህ ብላ የምታዳምጠው ጉዳይ ነው። የዓለም ሥልጣኔ አድማስ ይህን የፈጣሪ ሞገድ ማስቆም፤ መከልከል፤ ማገድ አይችልም በብዙ ምክንያት። አቅሙ የተሰጠው በልኩ ነውና።
እኔ ችግር እያዬሁ ያለሁት በእኛ በራሳችን ነው። የእዬር አደባባይ ቁጥር አንድ መቀሌ አቅራቢያ፤ ቁጥር ሁለት አርምጃ ጉራጌ ዞን፤ ቁጥር ሦስት የተቆጣ ወላፈን እዛው። ይህ አስደንጋጭ መልዕከቱ እራሱ በኽረ ጉዳያችም አጀንዳችንም ሊሆን አልቻለም። አሁንም የእኛ ነገር ከዛው ላይ ነን። ጉዳያችን ቢሆን የምንራኮትብትን ጉዳይ ስለምን ብለን እንጠይቅ ነበር? የፈጣሪ ምህረት ያለው በንጽህና ብቻ ነው። በደቦ የሴራ ግርግር ከፈጣሪ እርቅ ጋር መደራደር አይቻልም። ምህረት የሚገኘው በቅንነት ማህጸን/ አብራክ ብቻ ነው፤ መከራ የሚታገሰው ርህርህና ሲኖረን ብቻ ነው። ስለመፈጠራችን ሚስጢር ስናውቅ ብቻ ነው። ማውቅም ብቻ አይደለም የደንበራችን ልክም ስንረዳም። አሁን እኮ ደም ለማፍሰስ የቋመጠ የሻብያ መንፈስ አለ ለዛ መከረኛ ህዝብ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያጣውን የጎመጀመውን ያህል ለማረድ ሌት ተቀን ወገንን እያፈናቀለ ነው። እኛ ደግሞ ትንሽም ትንፋሽ ሲገኝ መጠራቅቅ እዬፈጠርን መሬት እዬደበደብን ጦር አውርድ እንላለን … ማሳዘናችን። አቅሙ ከኖረ በአቅም ልክ መንፈስን አደራጅቶ ትግልን ሞጥሮ መቀጠል ነው። ድሮም ኦህዴድ ነፃ ያወጣናል ብሎ አልነበረም የፖለቲካ ድርጅቱ ሁሉ ማንፌስቶ አርቅቆ ቀን ቆርጦ ሲታጋል የነበረው። ዛሬም የልቡ ካልደረስ ሚደያ ላይ ሳይሆን መሬት ላይ መሥራት። አብሶ ውጪ ያለው። ማን ከልካይ አለና። ለድል ቢበቃም እኮ እጁን አጣምሮ አይቀመጠም ቀረብኝ የሚለው ባለ ማንፌስቶ፤ ጠንክሮ ለመውጣት ቀጥሎ መታገሉ አይቀሬ ነው። ሂደት ፈተናውን ባዘጋጀ ቁጥር ድንኳን ጥሎ ምሾኛ ጋር ከመደራደር ከበቃ ተግባር ጋር ውል ማሰር ነው አዋጪው መንገድ። ስለመሻሉ የሚያውቀው ተጠቃሚው ብቻ እና ብቻ ነው። እጠቅምሃለሁ ስላለ ጥቅም የለም፤ አልጠቅምህም ካለም ጥቅም የለም። ሁሉም ሚፈተሸው በእውነት ዓውደ ምህረት ጉባኤ ነው። ለዛ ራስን ማብቃት፤ የሚያባክኑትን ጊዜ ቆጥቦ ህሊናን መንፈስን ራስንም ካሾለኩት የስልት ጥበብ ጋር ማወደድ ነው ቀደሚው ጠቃሚው መንገድ። በ2016 ስለ ብልህነት እና ብልጠት በፖለቲካ ዕሳቤ ተንትን አድርጌ ጽፌያለሁኝ። ብልህነት ነው ዘላቂ ቋሚ የአምክንዮ የድል ዲታነት። ብልጥነት ለጊዜያዊ ኢኮኖሚያዊ ቅርጣፊ ትርፍ ነው። ለዛውም ትርፍ ሚዛናዊ ካለሆነ የህሊና ዕዳ ነው። ሥም አንድ ጊዜ ነው የሚገናበው፤ የሚባክነውም። ያን ጊዜ አቤት ስትል የእኔ ብዕር አድማጭ አልነበራትም። „ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ቆሞ የሚጠብቅ የሆነ Stagnate አምክንዮ የለም“ እነኝህ ሁሉ ለዛሬ የጥሪት ጠጋኝ ነበሩ። ልባሞች በክህሎት ተካኑበት። አተረፉበት።   
  • ·         መዳን በፈጣሪ ልቦና ውስጥ ነው ያለው። 

መዳን በፈጣሪ ልቦና ውስጥ ነው ያለው። አንድ አባት ሲናገሩ ሳዳምጥ እንቅልፍ ላይ ብንሆን ጥፋቱ የከፋ ይሆን ነበር ነው ያሉት። በስም አብ! ፈጣሪ በውነቱ ታድጎናል። ግን ነገስ ምን ሊሆን ይችል ይሆን? ምንስ ጋራንቲ አለን? እንደ ፊዝክስ ተማራማሪው አፋር አቅጣጫ ሳይሆን በፈጣሪ ውሳኔ ደግሞ የትኛው ማዕት፤ የትኛው ስፍራ ላይ ይከሰት ይሆን? ምን አይነቱ የተለዬ የቁጣ አይነት በምን ሁኔታ ይታዘዝ ይሆን? ግን ይሄ የእኛ ስጋታችን አይደለም። አይጨንቀንም አይጠበንም፤ በእጅጉ የፈጠጠውን ሃቅ አርቀነዋል። ይህ ከህሊና አስከአልገባ ድረስ አደጋው መጠነ ሰፊ ነው። ከእኛ ይልቅ ሀገረ ኬኒያ የሰማይ ሚስጢር አስቀድሞ ገብቷት፤ ቀድም ብላ በእጮዎች ውድድር ላይ ሰፊ ሽፋን በሚዲያ NTV & CGTN Africa ሰጥታ በሳል ፖለቲካ ሃያስያዎቿን ስታሰትፍ ነበር። ከምርጫው ማግስትም እንዲሁ፤ ይህም ብቻ አይደለም እማማ ኬኒያ ከብርሃን ፍጥንት ባልተናነሰ ሁኔታ በከፍተኛ ልዑክ ቡድኗን በባዕታችን ልካ ውሳጧን በእኛዊነት ስሜት አበልጽጋለች ናልኝ የእኔ ምኞት የኢትዮጵያ ነገር በጭንቅ ውስጥ አሰቃይቶኝ ነበር በላለት ነበር። ግብዣ ሥራዬ ብሎ ልዑክ በመላክ። ይህም ያልተለመደ ልዩ ክስተት ነው። ትባረክልን!
Flag of Kenya.svgእቴጌ ኬኒያ! አሁን ደግሞ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ኢትዮጵያ ከሰጠችው ክብር በላይ፤ በላይ ድንቅ ነገር ፈጽማለች - እቴጌ ኬኒያ። 21 ጊዜ መድፍ እስከ መተኮስ ደርሳለች። ሥርዓቱ ማራኪም ሳቢም ደማቅም ነበር። ይህ ግን ሰውኛ ነውን? ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ዝቅ ብላ ሥሟን ለመጥራት በተጸዬፈው ደራጎን ዘመን እያለ፤ ከነቁመናው እዬተነፈስ ሳይሟሟ የኢትዮጵያ አምላክ በጸጸት ቀጣው፤ አርመጠመጠው እፉኝቱን ሁሉ። ኢትዮጵያን በጥርሳቸው የያዟት ስውሮችም መንፈሳቸው ገሃነም ተለከ። አፍሪካን በጥበቡ በነፃነት ቀንዲሉ የሠራው ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው ታስሮ፤ ተገንዞ፤ ድንቄ ያሉት ለሞት - ለእስራት - ለስደት - ተዳርገው ግን ኬንያ የኢትዮጵያን የቀደምቱን የማደረግ ትወፊታዊ አቅሟን ክፍ ብሎ ማዬት ህልሟ ስለነበር ያዬነውን ታምር አሳዬችን። ከቶ ኦህዴድ እንደ ድርጅት ምን ያህል ክብር እንዳገኘ አስተውሎት ይሆን? ምን ያህል አደራ ለፓን አፍሪካኒዝም እንዳለበትስ? በዚህ ውስጥ የገዱን መንፈስ እንዴት ያዬው ይሆን? ኬኒያ እኮ የራሷ ድል አድርጋ ነው ያነገሠችው። ያጭጌችው። ድንቅ ቃሉ አይገልጸውም ገድል የሰማይ። …  የዶር አብይ አህመድ ወደ እጩነት መምጣት „ተለጠጠ“ ያሉን በእኛ ሥም ያሉ ሚደያዎች ሁሉ ከቶ ይህን መርዶ ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን? ገናም ገና አለ ገና … ፈቃዱ ሰውኛ ስላልሆነ። ብቻ የፈጣሪ ጥበቃ ይህን ሠርቶ የማይደክም፤ ከትናንሽ የብረት ቁርጥራጭ የተሠራ ባላቅኔ ጠ/ ሚር መንፈሱን ይጠብቀው። ኢትዮጵያ ወደ ቀደመው ክብሯ ተመልሳ አፍሪካን ትመራለች እያልኩም ስጽፍ የባጀሁት በዚኸው ነው። የናሙናዊነቷ እድሜ ዘለቁ ንጥር መክሊቷ የልዕልት ኢትዮጵያ እንደ ገና አዎን እንደ ጋና ይፈካል! ያብባል! ይጎመራል!
  • ·         ልዕልት ኬኒያ „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የልባዊነት ዘውድ በክብር ደፋችለት!

  „እግዚአብሄር እዮብን ልቡ ከሃጥያት እንደጸዳች ባዬ ጊዜ በብዙ ክብር ተቀበለው (መጽሐፈ መቃብያን ሣልሳ ምዕራፍ ፰ቁጥር ፪“)
108ቱ በልባቸው መዳንን ያባቀሉት የጻድቃን „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ትንታግ ወታደሮችን ጨምሮ፤ የምልዕቱ በዬቤቱ ጸሎት የውሳኔያቸው ትክክለኝነት በዓለም እንዲህ ደምቆ ሲታይ ከዚህ በላይ ምስክር የለውም። ይህን ያዩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እዬዩትም ነው። በፍቅራዊነቱ የኬኒያ ጉባኤ አቦ ለማ መግርሳን ሳይ ራሱ ሐሤቴ ወደር አልነበረውም። መከረኛዋ ሞያሌም የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ማዕከል ለመሆን የማሾዊ ተስፋ ባለቤትም ሆናለች። ብስጩ ወያኔ ደግሞ ይህን በማክሰል ሰለሟ የታወከ ሞያሌን አልሞ እዬተነሰተ ነው። ሰላም የላትም እንድትባል። የሆነ ሆኖ ካሳው የፈጣሪ ነውና እንዲህ በስልት እና በጥበብ ያሹትን ለማግኘት ዕዮባዊነትን ማጫት ይጠይቃል። ርቁቅነት እና ሩቅነት።
  • ስሌት፤ 

ለዚህ ነው በባዕለ ሽመቱ ማግስት የሂሳብ ስሌት ሲንደረደር ያሸነፈው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፤ በኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው አሸነፊም ተሸናፊም የለም“ ብዬ የጻፍኩት፤ ቀደም ብዬም ለኦህዴድ „መልካም ዕድል“ ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር። መዳን በፈጣሪ ልቦና በተቀበሉት ብቻ ስለሚገኝ።
የሆነ ሆኖ የኬኒያውን ያን ግሎባል የእንኳን ደህና መጣህልን ክብር እና ዝና የትናትናው የፓን አፍሪካኒዝም ጣዕምና ለዛ የሊቀ ሊቃውነቱ የፕ/ ማሞ ሙጬ ድካምና የውጤት አዝምራ፤ እጅግ የተከበሩ የ ዓለሙ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ፤ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን፤ የድንቁ ይድነቃቸው ተሰማ ጥበባዊ ፍላጎት ምኞት እንዲህ በሙሉ አቅም ጎልብቶ ሲወጣ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የምርኩዝ ግራጫዎች የዘመቻ የጥፋት ደቦም በዚኽው መርዶውን አወራርዷል ብዬ አስባለሁኝ። አብሶ ሳጅን በረከት ስምዖን፤ አቦይ ስብሃት ነጋ ምድር ብትውጣቸውስ? በቁም በደመመን እንዲህ መዋጣቸው ነው ክፋቱ? መንፈሳቸው ቋንጣ ሆኗል። ከትንግርት በላይ ነበር አቀባበሉ፤ ክብሩ - ሞገሱ - ግርማው - ማህባው ዕጹብ ጽላት። እንዲህ እናት ኢትዮጵያ ይመርባት እንጂ …
ኢትዮጵያ በሀገሯ ተረግጣ ግን አፍሪካ ላይ፤ ኬኒያ ላይ እንደ ድሯዋ በቀደመው ክብሯ ልክ እንሆ ቦግ ብላ በራች። ተመስገን! የኬኒያ መንግሥት እና ህዝብ ለዚህ ታላቅ ክብር ለዛውም ውስጣችን በሃዘን ተኮማትሮ ለኖረው ቅኖች ሁሉ፤ የወንበር ጠረን ትውር እንዲልብን ለማንፈቅደው እንደ ዓለም ዐቀፉ ጋዜጠኛ እንደ ዓለምነህ ዋሴ አገላለጥ ለእኛ „በሞኝነት“ ማህበር በህሊና ለተጋባነው ሁሉ ልዩ የምሥራች ቀን ነበር። ስለሆነም ከመቀመጫዬ ብድግ ብዬ ፈጣሪዬን አመሰገንኩት። አቧራ ላይ ለወደቀው የቀደምት አርበኞቻችን ደም እና አጥንት ለተከፈለበት የነፃነት ተጋድሎ በልኩ፤ በመጠኑ የተሰጠው አክብሮት እና ልዕልና ለሰጠው የኬኒያ መንግሥት እና ህዝብ ምስጋናዬ ይድረስልኝ ስል በልዩ አክብሮት ሻማዬን ለኩሼ ነው። ሰሞኒት በመሬት መራድ ድንጋጤ ብቻ ሳይሆን ይህን ሁለት ቀን ብሩህ ሐሤትም ነበረበት። የማለውቃት ኬኒያ ሳትቀር እስክትናፍቀኝ ድረስ ውስጤ ቧም ፏም አለ። ተመስገን!
  • ቡኒት።

ኢትዮጵያ ማለትም ሆነ ኢትዮጵያዊነት መሆንም በድርጎ፤ በደርበብ፤ በሲሶ እና በእርቦ ተሸራርፎ አይደለምና። ያ የናፈቀን ታላቅነታችን መንገድ ላይ ነው ዕዮባዊነትን ከሰነቅን። „ዕዮባዊነት በእጅጉ ያስፈልገናል“ ብዬም ጽፌም ነበር፤ „እጬጌው ሂደትም“ ማጣፈጫው ኮረሪማ ነበር። መጻፍ አይታከተኝም እና፤ ሌላም ምን አቅም አለ … በግርዶሽ ትቢያ ውስጥ ብቅ እንዳይል አቅማችን ለተቀበረች ነፍስ፤ ግን ብራና ሳተናው አለ እንደ አባት አዳሩ ትውፊተኛ። ተመስገን!
ኬንያ  የኢትዮጵያዊነት ብቁ አንባሳደር ነው የሆነችው ዘመንን በፍቅራዊነት በንዑድና ጠለፋ ነው። ለነገሩ ኢትዮጵያን ለመውረር አስባ የማታውቅ የሰላም ልዕልት ናት። አደብ የገዛች የፍቅር ትንግርት! ከዚህ በላይ ልቅና ከዚህም በላይም ትልቅነት ከዚህም በላይ ልዩ ስጦታም የለም። ይህን ትልቅነት ዳግሚያ ትንሳኤውን ደግሞ መስጥራው በኖረችው ጭምትንቷ ልክ እንሆ ዘመን ሲፈቅድ ገድል አሳዬችን። ይህን ነበር ትፈልግ የነበረው ልባዊቷ ኬንያ። እንግዲህ የፌስ ቡክ የአሉታዊ  ቢሮዎች ኬኒያ ላይም አንድ ዘመቻ ምንትሶ በሚል ሥያሜ አዬር ላይ መክፈት ሊኖርባቸው ነው። ተጨማሪ የቤት ሥራ የመቻቻል አንባዋ ኬኒያ በልባምነት ልካላቸዋለች ለፌስ ቡክ አሉታውያን ባለሟሎች። ለእኛ ለሞኞቹ ማህበር ደግሞ የቤት ሥራችን አቃለለችልን እቴጌ ኬኒያ። ትባረከልኝ! የውጩ መንግሥታት ቀልብ ያረፈበት ታላቅ የሎቢ ተገባርም እግረ መንገዷን ልባዊቷ ፍቅር ሆናበታለች ስለእኛ። ድካማችን ቀነሰች። የተዚህ ቀደሙንም ጥረትንም ፈረመችበት። ተመስገን!
ሌላው የእቴጌ ኬኒያ ድንቁ ብቃታዊ መለኪያ ጉዳይ የአሜሪካ ልዑክ ኬንያ ከመድረሱ በፊት ገዢው ፓርቲ እና ተፎካካሪው ጉልበታም ፓርቲ ገመናቸውን የከደኑበት ጥበብ ለፓን አፍሪካኒዝም ታላቅ ናሙናዊ ተቋም ነበር። አፋቸውን ነበር ያስያስያዙት። ኮፒ ራይት አልባ አደረጓቸው። እኛ አስማማን ማለት አልስቻሉም፤ ለአፍሪካ የዴሞክራሲ ጥበቡ ባዕድ ነው በሚበልበት ስላቅ ውስጥ መሆንን በተግባር አሳዩበት የኬኒያ ሊቀ - ሊቃውንታት። እህህህ … እኛስ? የእኛውማ በሆነው ተግባር ስንጥር ስብጥር፤ ድክመትን ነቅሶ መተቸት ይሁን ይባል፤ ጊዜው ገና ልጅ እግር ሳይሆን ቢሆንም፤ ደሙ ያልረጋ ጽንስ ቢሆንም፤ ስለቱ ክፉ ዜና ዱብ አደርግልን ነው እዬተደመጠ ያለው። የውጭ ሚደያዎች እስኪታዘቡ ድረስ።
ሞጋች ሃሳቦች እኮ ሁላችንም አለን፤ ጠብቀን ቆጥበን ዬያዝነው፤ አሁን ግን አይደለም። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሚሊዮን ጥያቄዎችን ከህዝብ ዕይታ ጋር ዝቅ ብለው ወርደው ባልተለመደ ሁኔታ ሰበሰቡ፤ በአስተያዬት ሳጥናቸው አጠራቀሙ፤ የተሰጣቸው ስለሆኑ እሱን በፋይል በማቀፊያ መደራጀት አለባቸው በቅድሚያ፤ ለዬባለቤቱ የቤት ሥራውን ለመከወን መርሃ ግብር ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከዛ መደልደል ነው። ይህ አንዱ ምዕራፍ ነው። ተከታዩ ምዕራፍ ደግሞ ከዚህም በላይ መሬት ላይ ከራሳቸው ህይወት ጀመሮ ሰውኛ ስለሆኑ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የሰበሰቧቸው አምክንዮዎች አሏቸው፤ ከዚህ በላይ ማህበረ ደራጎን በሴራው በጋንታ፤ በጋንታ ተደራጅቶ አሰፍስፎ እዬጠበቀ ነው ሲችል ነኮር በጥበጥ እያደረገም ነው፤ በዛ ላይ ካቢኒያቸው ብዙም ለሳቸው የንጽህና መንፈስ ቅቡልነቱ ጥያቄ ውስጥ ነው፤ የሳቸውን ሰዋዊነት ተፈጥሮ የመሸከም አቅሙ አይችለውም - እንደ እኔ። ሙሉ ለውጥ ቢሆን ነበር አሁን ግን አቀበት እና ቁልቁለት ብራ እና በረዶ በቅልቅል ነው።
  • ቅንነት።

ያለው ቅን መንፈስ በጎን የአቦ ለማ መግርሳ፤ እና ነፍሱ በግራ በቀኝ በሳጅን በረከት ስምዖን ሳንጃና የስለላ መረብ ተጠርንፋ የተያዘችው የአቶ ገዱ አንደርጋቸው የኤሉሄ ንጹህ መንፈስ ብቻ ነው። ሌሎችም ጥቂት ጎልተው ያልወጡ ቅኖች ሊኖሩ እንደሚችሉ በታሰቢነት ተይዞ። ስለዚህ እኔም የብዕር ቦንብ ስልክ፤ እርሱዎም የተከበሩት ፈንጅ በተንቀሳቀሱበት ቀጠና ሁሉ ሲያጠምዱ፤ ከፍ ሲልም ቦንብ አዝናቢ አዬር ሃይል በመላክ ማወክ አይገባም። ተመክሮ አብሶ የፖለቲካ ተመክሮ አደብ ይሻል፤ አደብ የነሳው ፖለቲከኛ ዕድሉን ቢያገኝ አንድ ስንዝር መርቶ እግቡ ሊደረስም ሊያደርሰም አይችልም። አቅለ ቢስ መቅኖ ቢስ ነው። ተመክሮ ሌላ ፍልስፍና የለውም ስክነት ነው። ከዚህ የተጣለ የኔታዎችን ደጀ ሰላም ደጅ መጥናንት ይኖርበታል፤ ከሁሉ የሚከፋው የሰማዩን ቁጣ ይፋፋም እና ዕንባ … እንደ ወረደ ማወራረድ ነው፤ ለዛውም ዕንባማ ወንድ ከሚሊዮን አንድ ከተገኘ እሱም የሰማይ በረከት ነው። ያው የውጩ ፖለቲካ የወንዶች ዓለም ስለሆነ አራጊ ፈጣሪዎች እናንተው ስለሆናችሁ።
ይልቅ ከእንግዲህ የሴቶች ጉዳይን ሴቶች አይውሰዱት የእኛ ጉዳይ ነው መነሳት ከፈለግን ይዘን መጓዝ መውደቅንም ከተሳልን ትተን መጪ ማለት ብለዋል ጠ/ ሚሩ አዋሳ ላይ፤ ሌላው ብልህ አገላለጽ ደግሞ መዳንን በፆታ፤ በሃይማኖት በብሄረስብ ኮታ አናድርገው የሚል ልሁቅ ዕሳቤም አዳምጫለሁኝ ይሄ ደግሞ አሶሳ ላይ የምስለኛል። ወሸኔ ነው። አቅም ነው መመረጥ ያለበት ይህንም አሳምሬ እጋራዋለሁኝ። ሌላም „እኔ እንደ እናንተው የሆንኩኝ የአንድ ገበሬ ልጅ ነኝም“ ብለዋል። ይህም በተመክሮ ለዘለቀ ፖለቲከኛ ሌላ የማረሚያ ተቋም ነው። ተንታኝም ከተሆነ በዛ ዘልቆ በቅሎ መሬት ላይ ህይወቱን ከኖረ ነው። በሲዲ ስምሪት ለነበረ ይህ ፍልስፍና ከባድ ነው። ህዝብ ማደራጀት የውሎ ደርሶ መልስ አይደለም። በወረትም አይደለም ቁጭታን ይጠይቃል። የተደራጀን መንፈስ የልብ፤ የራስ ሃብት ለማድረግ መነሻ ተመክሮ ይሻል። ቢያንስ የአንድ ቀበሌ፤ ሆነ ገበሬ ማህበር መሪ መሆን። የተግባር የኔታው ያለው እዛ ነው። ማደረጃት እጅ በማውጣት ወይንም በማጨብጨብ ፍሬው አይገኝም። በአድካሚ በአታካች ተከታታይ ትጉኽ ሥራ ብቻ። ማደራጀት ሸቀጥ አይደለም። በኪወስክ የሚሸመት ወይንም የሚቀና። መንፈስን ከመንፈስ ማጣጣት ይጠይቀል። በመቅርብ እና በማቅረብ።
  • መፈታትን።  

እንኳንስ ለተቃዋሚዎች ለኢህአዴግ ማህበርተኞችም ፈተናው ከባድ ነው። በሥራ ፈትነት ተኮፍሶ የኖረው የብረት የቀለሃ ጉልበተኛ አሁን ጉዱ ነው። ጠ/ ሚሩማ የለመዱት ነው። ሌት ተቀን መበታል የተሰጣቸው ነው። ከኦህዴድ በስተቀር የዚህን ጉልበታም መንፈስ ራዕይ ምቹም የለም፤ ተፎካክሮ ማሸነፍም የሚችለው እሱ ብቻ ነው። አብሶ የሳጅን በረከት ጋንታ እንደ አሻው የሚጨፍርበት ብአዴን ፈርሶ መሠራት ካልቻለ „ከእርምጃ ወደ ሩጫ ለመሸጋገር በእድገት“ ይከብደዋል። ጣሪያ ነው። ተቃዋሚዎችም ቢሆኑ ራሳቸውን ማሰናዳት ያለባቸው ከዚህ መንፈስ ጋር ነው። በዛ ላይ ማንፌስቷቸው የህዝብን ጊዜ በቀል አጀንዳ ያልዘገበ ነው። ሾልከዋል። መሬት ላይ አማራነትን የማን ነበር አጀንዳው? ሌላው አዲሱ እና ነበሩ ካቢኔውም እንዲሁ ፈተናው በቀጥታ ይፈትሸዋል። ለዚህም ቀይ መስመር ተሰምሮበታል። አብሮ ከረባት አስሮ በገበርዲን ከቦታ ቦታ መንቀስቃስ ሳይሆን እዛውም ላይ የቤት ሥራውን እዬሰጡ ነው። የመቆጣጠሪያ ስልቱም አላቸው። ሁሉን ነገር ይመዘግባሉ። ቀላል ሰው አይደሉም። የሚደፈር፤ እንደአሻን ልንረማመድበት የማንችል ምክሊተ - አቅም ነው ያላቸው። ስብሰባ እኮ ከሥራ ሰዓት ውጪ እና ሰንበት ላይ ብቻ መሆን እንዳለበት አበከረው ገልጸዋል፤ በባለ ሃብቶች ስብሳባ „እኔ 7 ቀን እሰራለሁኝ፤ ትንሽ ምህረት ላድርግ እና ግዴለም እናንተ እሁድን ከሰዓት እረፉ“ ነበር ያሉት። በዘመነ ኢሠፓ እንደዛ ነበር አብሶ የፓርቲ አካላት እንሰራ የነበረው። ዕምነት የሚባለው ራሱ ይህን ንጽህና መመርመር ተስኖታል።   
  • ·         ክፉ ዜናም እንደ ንጹህ አዬር ተወዳጅ ሆነ …. ህም!

የሚያሰገምተው የፈጠራው ክፉ ዜና ነበር። አንዱ ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ጠ/ ሚኒስቴር ሊሆኑ ተወሰነ ሲለን፤ ሌላው የግንባሩ ስብሰባ የአዲስ ጠ/ ሚ/ር ስዬማ ሹመት ብሎ ነገር የለም ሲለን፤ ሌላው ከምርጫው ማግስት ደግሞ ከትግራይ በኋዋላ ደክሟቸዋል እረፍት ላይ ናቸው ጠ/ ሚሩ  የአማራ ወጣቶችን በሚሊኒዬም አዳራሽ እንደ ጠሩ ሰምተናል ስንባል፤ ሌላው ጭራሽ በነሳጅን በረከት ስምዖን የሚመራ የኮሚቴዎች ብርጌድ ድርድር እስከ ምንትሶ ጊዜ ተግባሩን በሃላፊነት ሊመራ ተሰናድቷል፤ የጠ/ ሚሩ ቢሮ መና ቀርቷል ሲለን፤ አንዱ ኢትዮጵዬ አዬር መንገድ ትኬት አሳላፊ ጠ/ ሚሩ መሆን ነበረበት ሲለን፤ የባሰበት ደግሞ አሜሪካ ኢንባሲ ቪዛውን ቁሞ ሊያስመታ ይገባል ይለናል። ወደ አማራ ክልል መሄዱ ቀርቷል ሲባል ጎንደር ሲሄዱ ደግሞ የተሰበሰበው ካድሬው ነው፤ ለዛውም የጠ/ ሚ/ሩ ያን ንግግር ረግጦ ሄዷል ጎንደር፤ ያ በዬዘመኑ በጥርስ ተይዞ ሲከተከት የኖረ ህዝብ መቼም መከራው ማለቂያ የለውም፤ ሌላ ቦታ እንደዛ በጦር ካንፕ ውስጥ የ አደባባይ ጉባኤ አልተካሄደም ፍደኛው ህዝብ ግን በዛ በወታደር ተጠርንፎ ሁሉንም ችሎ የታደመበትን የአደባባይ ጉባኤ፤ በማቃለል የጎንደር ህዝብ የመሪውን ንግግር ጥሎ ሲሄድ ሹልክ አድርገው መሪውን ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ጎሃ መሸጉት፤ ስንባል በጎንደር ህዝብ ታሪክ ላይ የጥቁር ሰሌዳ እያሰናደን መሆኑን ልብ አላልነውም። ለዚህ ሥልጣን ያበቃቸው አብይ አመክንዮ እኮ የጎንደር የ አማራ ማንንት ብሄራዊ ግሎባል አብዬት ነው። „አቦ በቀለ ገርባን መሬዬ የኦሮሞ የጋንቤላውም ደም ደሜ ነው ብሎ“ ሞትን ለተጋፈጠ ጀግና የግንባር ሥጋ ህዝብ ውለታ የትግል ውጤቱን ለማዬት አልፈቀደም ተባለ።  የተባለ ቢባል ያለንንም፤ የምንችለውንም የሆነውንም የምናውቀው እኛው ራሳችን ብቻ ነን። ወዳጅም ጠላትም አሳምሮ ስለሚያወቅን ነው ከራሳችን ወርዶ የማያውቀው። የአለን አለን ያጠነው በአለን የበታችነት በሚያምስው ህሊና ሰላማችን መታወኩ ነው በዬዘመኑ።
  • ተመስገን!

ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ቂመኛ ቢሆኑ ኖሮ ይህ ጉድ አስቆሞ አያስኬድም ነበር፤ ግን ውስጣቸው ውስጧችን ስለሆነ ቅጭጭ አላለንም። እንዲያውም ከትከት ብለን ሳቅንባችሁ ስታራግቡት። ወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ የተፈጠረው ጎንደርን ለማክስለ ነው። ያን ተሸክሞ፤ ሁሉንም መከራ ችሎ ከ20 ሺህ እስከ 30 ሺህ የሚገመቱ የጌቶችን ሥጋ እና ደም በችሎት፤ በፍቅር እንደ ተለመደው እዬተጋባ፤ እዬተጎራበት ተሸክሞ የኖረ ህዝብ ነው እንኳንስ ያን ቅን ባተሌ፤ ብቻ የበሬ ወለደ ታሪክ ሲተረተር አንደ ዳንቴል ተከረመ። መሬት ጦር አውርድ ብሎ መደብደብ። ሥርጉተ ሥላሴ እኮ ጎንደሬ የጎንደር ከተማ ልጅ ናት የመይሳው ትንፋሽ። የትኛውም ሰው ባሊህ ባላለበት ሰዓት „አብይ ኬኛ! አብይ ብቸኛው የጎንደር ጌጥ!“ ብላ እስከ ክፍል ስድት አንቱዎችን የሞገተች፤ የተፋለመች፤ በተያያዥ ጹሑፎችም በበርካታ የብዕር ቦንቦች የተፋለመች ናት። ሽንጧን ገትራ ከውጥኑ ጀምሮ የተጋች ባተሌ ናት። ዛሬ ጎንደር ታሪኳን በትውስት ጸሐፊ አይደለም የሚሠራለት። ልጆቿ የት ሄደን?! ሥርጉተ ግንዷን ሳትንተራስ? እንዴት ተቀለደ!  ለእሷ ያልሆን ከቶ ለማን ልንሆን? ከአብይ የተሻለ እኔ ለጎንደር ነበርኩኝ፤ አለሁኝ የሚል ሊሂቅ በሉት፤ ተንታኝ በሉት፤ ጸሐፊ በሉት፤ ጋዜጠኛ በሉት፤ አክቲቢሰት በሉት፤ ፖለቲከኛ በሉት ይምጣ እና በሳተናው ብራና ይሞግተኝ። አቅሙ ከኖረ። እንደ ድርጅት ከኦህዴድ የተሻላ መሬት ላይ የፖለቲካ ድርጅት ከኖረም አለሁለት ሳተናው ብራና ላይ። በ43 ዓመት የሾሻሊዝም እንቅርት ዘመን ውስጥ አማራን ከውስጡ በንጽህና ያበቀለ ድርጅት ቢኖር ኦህዴድ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ሰው ሰራሽ አይደለም የፈጣሪ ሥራ ነው። ዕንባችን የሰጠን ታላቅ የጸጋ ካሳ። የተከበሩ የሃይማኖት አባት ኡስታዝ ራያ ጎንደር ማን አለው ሲሉ አላዳመጣችሁንም? የጣና ኬኛ ዕንቆዎች እኮ ጎንደር ድረስ ሄደዋል። ውስጣቸውን ማግኘት ነበረባቸው። ኦህዴድ ሽልማትም ነው። ቤንሻጉል ላይ ይህም በዛበት ብሎ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያሰናደው ወጣት የተናገረው አዳምጡት፤ ፉክክሩ በሞት ውስጥ ከከተመው አማራ ጋር እንጂ ከዘመናዊቷ ትግራይ ጋር አልነበረም። አንብርክኮ ከገዛው 27 ዓመት ሙሉ ከናዚያዊ ፍልስፍና ጋር አልነበረም።
  • ልክ።  

ስለሆነም ቅኖች በቅርንጫፉ ላይ ሳይሆን በግንዱ ተስፋ ላይ ድልድልን በእዮባዊነት ያመንኩሱት እንላለን። መናጆነት በቃ! መናጆነት በቃ! አንጋችነትም በቃን! አንጋችነት በቃ! በቃን ያላሉት በተሰጣቸው ልዩ የክብር አደባባይ ይቀጠሉ፤ ሲሞቅ እንደሚወረውሩ እንደ 2016ቱ ሲቀዘቅዝ ደግሞ ከፍ ብለው እንዲታዩ ሲከበከቡ ታች ላይ ወደቅን ስንጠቀጠቅ የኖረነው እንታዘባለን፤ ታች መሆኑ ጥሩ ነው አሻቅቦ ለማዬት ይበጃል።አቧራ የለበስነውም ትቢያዋን ተጎናጽፈን ያለነው ለትንሳዔያችን ድርና ማግ መሆናችን ደግሙ በጥንድ ጥንካሬ ያልጥርጥር ይቀጥላል። አይደክመንም! ግድፈቶችን ሲነሩም የጠ/ ሚሩ ቢሮ ይሞገታል። አሁን ባለው ሁኔታ ገበሬውን ትጥቅ ማስፈታቱ ይቁም! በቀጣይነት ጎንደር ጥያቄዋ ይመለስ ተከዜ ነው ደንበሯ፤ ከዚያ በኋዋላ የትኛወም የከፋኝ አንጋች መረማመጃ በዙር ጎንደር አትሆንም። በፍጹም! የፈለገ በዬጫካው ይሸፍት እና መስዋዕትነቱንም፤ ጀግንነቱንም እንደ ቀደምቱ ጀግኖች አያቶቻችን በቀዬው ሆኖ ያመጣጥነው። አሁንም ጫካው ስላለት እዛ ሄዶ ይፎክር ይሸለል። „የአጋሩን በሬ በአገሩ ገበሬ።“ ዛሬ አዋሳ ከዚህ የደረሰችው ጎንደር ጎብጣ ባፈራቸው የድል ርካብ ነው። ሞኝነት በቃን!  እንደ ትውፊታችን „ልብ ያለው ሽብ፤ ሙያ በልብ“ እንላለን፤ አጃቢነት ሱስ የሆነው የቀረበት ይነሳ ይውደቅ - ተጠማኝ። እኛ የተመኘነውን ሰጥቶናል ፈጣሪያችን የ44ቱ አምላክ። ቀሪው እዮባዊነት ይመልሰዋል። ስለሆነም „ላም ባልዋለበት“ ክፉ ዜና እዬሰራችሁ የጎንደርን ታሪክ ጥላሸት ከመቀባት ታቀቡ። ሰይፉን ሰውኛ ሳይሆን ፈጣሪ እራሱ ይስለዋል። ለምድራዊው ደግሞ ሥርጉተ ሥላሴ አለች። አሁን ብሎግም አላት። ሳታናውሻ አደከምኩት ብዬ ሳስብ እረፍት እምሰጥበት። ከእኔ ጋር መሥራት ችግሩ ሰው ይደክማዋል ስለማልል፤ ስለዚህ ለወንድሜ እረፍት ስሰጠው እናንተ ደግሞ „Kenebete (ቀንበጥ)“ ብሎግን እንዴት ነህ? አለህን? ማለት ትችላላችሁ ኑልኝኝኝኝኝ … ወቀሳውንም አስነኩት ድርጁ ትክሻ ስላለ አሳምሬ ቼ ፈረሴ አስብልላችሁ አለሁኝ፤ በፍቅር በሰናይ አስብዬ፤ ማስበል ደግ ነው ከሰብሎች ባዕት። ልካችን እናውቃለን። ደንበራችንም አንስትም። 
  • የተሳሰተ መረጃ የተሳለ ለትወልድ የሃቅ ውርርስ ምላጭ ነው። 

ክፉ ነገርን አጭቶ ምንም መረጃ ሳይኖር በተፈበረከ አንዲትም ቅንጣት የእውነት ቅርጥምጣሚ በሌለበት ሁኔታ ሁሉም የጠ/ ሚር ቢሮ ባልደረባ፤ አማካሪ፤ መርሃ ግብር ነዳፊ፤ የውስጥ አዋቂ ሆኖ ገመናችን ለዓለም አደባባይ ሲዘከዝክ ሰነባበተ። ጮርቃነት። በዚህ ስንት መንፈስ መበተን ብቻ ሳይሆን ዓለም ዐቀፉን ማህበረሰብ በተሳሳተ መረጃ እንዴት እንዳመሰነው ብቻ ሳይሆን፤ የመረጃችን ምንጭ ክፉ ምኞትን ሲያዘክር፤ ለዛውም ቪዛ ተከለከለ፣ ፓሱ ተነጠቀ ያልነው አባወራ በጠሐይ ሆላንድ፤ ኬኒያ አሁን አሜሪካ ነው ያለው። ሃፍረት። ስንብቿችን ማነሳችን ዓወጆልናል። ሊሂቃኑም ተው የለም። ይበቃል የለም። የኬኒያ ሊሂቃን ግን ሊህቅንትን በጥበብ አሳዩን - በዘመናችን። አዲስ ብስራታዊ ምዕራፍን ከፈቱልን። ሚዲያውን ሁሉ አመዱን ቡን አድርገው ክውን ያለ፤ ክሽን ያለ፤ ምራቁን የዋጠ የስክነት ተግባር ከወኑበት። ሁሉንም የተመቸውንም ያልተመቸውንም ፍላጎት አዋደው ለይስማሙ ተስማምተው ግን ተዋውጠው ጥቁር አፍሪካዊነትን አዳኑት ከሽንፈት። እንዲህ አፍሪካዊነት ጥቃት ሲያወጣ ልብ ብቻ ሳይሆን ነባቢትም ይሸለማል። ተመስገን!
  • ·         እኛስ።

እኛ ተነስተንም ወድቀንም ያችው የአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ላይ ነው ያለነው። አቃቂር ስናወጣ፤ ስናብጠለጥል፤ አውሬውም የቻለውን ያህል ሲያፍን፤ ሲንድ፤ ሲያተራምስ፤ ቁርሾ እያሞሻ ሲያጋጭ ብሄረሰቦችን ንጹኃንን ሲያፈነቅል ተግቶ ይገኛል። በሚዲያው አውሬው የሚሠራው ሳቦታጅማ ተዝርዝሮም አያልቅም። እሺ አዎሬውስ አውሬ ነው፤ የለመደበትን የተፈጠረበትን ይከውን፤ ግን እኛስ መቼ ነው ወደ ልቦናችን የምንመለሰው? አሁን ከሰውኛው የእርስ በርስ የስጋት ደመናስ የሰማዩ ማዬሉን የሚያስተውል ልቦና ፈጣሪ ቢሰጠን ምን በነበረበት? የነሰሃ ጊዜ።ሟርት ዜና ማጨት፤ ክፉ መረጃ መዳር መኳል አሰኘን ይሔው አሁን ጫን ተደል መከራ ተጀመረ … ነገስ? አናውቀውም ምን ያህል የገዘፈ ቅጣት እዬር እንደ በዬነብን? ቅጣቱ ኢትዮጵያ ብቻ ላይሆን ይችላል፤ አይደርሰብንም ባልነው ቦታ ሁሉ ከች ማለቱ በአለአቀድነው እና ባላሰብነው ሁኔት መከሰቱ የእኛ የእጅ ሥራ ዳንቴል አይደለም። የሚበጀው አፈር ትቢያ ነስንሰን አቤት ማለት ብቻ ነው። ባህር ውቅያኖስ ብናቋርጥ መጪው ከመመጣቱ፤ ቅጣቱም ከመበዬኑ አይቀርም። ውስጣችን በቁስ አምላኪነት ቆሽሿል። ፈጣሪ ይርዳን፤ አሜን!
አዋሳ ላይ አንድ ተናጋሪ ሲናገሩ „ባልተለመደ ሁኔታ እንለወጥ“ ነበር ያሉት። አዎን እኔም እላለሁኝ „ባልተለመደ ሁኔታ ለመለወጥ እንወስን!“ ፈጣሪም እያዘነብን ነው። መታመሳችን አልወደደውም። ቀጥተኛ መልዕክቱን ከዋዜማው ጀምሮ እዬላከልን ነው። የአቦ ለማ መግርሳ ልብ ምን ነበር አንድ መቶ ሚሊዮን ሁኖ ለሁላችን ፈጣሪ ቢያድለን ምንኛ በታደልን በነበረ? ሰሞኑን በተሰራው የOBN ልዩ ዝግጅት „ውስጣችን መርዝ አለ፤ ለማውጣት አልፈቀድንም፤ እዬቆሰልን እያለን እንኳን እኛ አውጥተነዋል። የእኛን ያህል በራስ ውስጥ እርምጃ ለመወስድ ዝግጅቱ ግን ያጠራጠርኛል ነበር ያሉት“ ዕድምታው ይሄው ነበር። አቦ ለማ መግርሳ ዘመንን ራሱን እዬሠሩት ነው። ዘመን የተረጎመ መጸሐፍ በእያንደንዱ እርምጃቸው ውስጥ አለ። ቤተ መክሊት። ቤተ መፍትሄ። ምን አይነት ማህጸን እና አብራክ እንደ ፈጠራቸው እራሱ የሚደንቅ ነው። የሶሻሊዝምን የአቅም አድኖ አጥማድ ማቅ ማልበስን አንዴት እንደ ተፈላሰፉበት ግሩም ነው። ይኑሩልን አቦ!
„ኦ..ኤን ዛሬ የለቀቀው ምርጥ ዶክመንታሪ ~ ለማ መገርሳ ስራቸውን እየሰሩ ነው“ ችግራችን።
አሁንም ቢሆን እኛ ያላዬነው ችግር አለ ብዬ አምናለሁኝ። ይህ ባልተለመደ ሁኔታ የተከሰተው ችግር በጉራጌ ዞን የሚኖሩ ወገኖቻችን በሥነ - ልቦናቸው ላይ የሚፈጥረው ጫናን። ወጥተው እስኪመለሱ፤ ምሽተ እስኪነጋ፤ ልጅ ት/ ቤት ልከው እስኪመለሱላቸው ከእንግዲህ አቅላቸው አያርፍም። በዕለት ህይወታቸው ላይ የሚያሳድረው ስጋት መጠነ ሰፊ ነው። እሰከ አሁን በምድር በጨካኞች የሚደርሰውን ግፍ ችለው መኖራቸው እያለ አሁን ደግሞ የእዮር ቁጣ የላከው ደወል ከሰውኛው ስጋት በላይ ረቂቅ ነው። አንድ ሰው ከወደደው ወይንም ካቀረበው ሰው ጋር በመስማማትም ይሁን ባለመስማማት ሲለያይ በሰውኛ ሊተረጉመው ይችል ይሆናል፤ ለእኔ ግን እንደዛ አይደለም። በዛ ውስጥ እግዚአብሄር የተከፋበት ነገር አለ ብዬ አስባለሁኝ። ስለዚህም ጉዳዩን የማስተናግድበት አያያዝ ይከብደኛል። ለዚህም ነው ገዳማዊ ህይወት ምርጫዬ የሆነው።
  • ሦስትዮሽ ፍርሃታት።

አሁን ሦስቱን የእዬር ደወሎች ቁጥር አንድ መቀሌ አካባቢ፤ ቁጥር ሁለት እና ሦስትን ጉራጌ ዞን እኔ ሳዳምጥ በመሃል ፈጣሪ የተከፋበት ነገር እንዳለ ይሰማኛል። አስኳሉን እኔ በሰውኛ ፈትቸዋለሁኝ እንደ አቅሚቲ። ከደማና ደም የተላከ ምጥ ነው። ይህን ለእኔ የህሊና ጭንቀት ማሳመኛ ወይንም ማስታገሻ ትቼ እንደ ሐገር ምን አጉድለን ነው? ምንስ ካሳ ይኖረዋል ፈጣሪን ላስከፋንበት ለበደላችን ክርፋት? እንዴትስ ይህን የፈጣሪ እሳተ ነበልባል ቁጣ ወደ ምህረት መመለስ ይቻላል? በምህላ? በድዋ? በሱባዬ? ወይንስ በምህላ? ሃይማኖት - ጎሳ ድንብር ሳይገድብ ብሄራዊ የወልይሾ የፈቃድ ጾም እና ስግደት በውስጣችን በማወጅ፤ እንዴት አንቀረራብ፤ ከዚህ የምህረት ጥያቄ ጋር፤ ግንስ ወስጣችን ንጸህናው ደረጃው ምን ያህል ነው? ዕውን ምድራችን ሰላማዊ እንድትሆን እንሻለን?  ዕውን የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባዊ ዘመን እንዲያከትም እንፈቅዳለን?  ውስጣችን ለፈጣሪ የምንፈቅድበት ሁኔታ ብንፈጥር ከቶ ነገን ይታደገው ይሆን? ከቶ ለንስሃ ዘግይተን ይሆን? እንዴት እና በምን ሁኔታ ከፈጣሪ አምላካችን ጋር የእርቅ ድልድዩ ይሰራ? ማህበራዊ ሚደያውስ ይህን በተደራጀ መንፈስ ለተወሰነች ቀን ከሁሉም ነገር ተግ ብሎ ለፈጣሪ ዕንባውን ለማፈስስ የመሰናዳት ባህሉ እንዴት ማምጣት ይቻል ይሆን? እኔ ጨንቆኛል። ፈርቸዋለሁኝ። የቁጥር ሁለት እና ሦስት ተጣምሮ መምጣት፤ የቅጣቱ ሁለት ዓይነት በጣምራ መሆን በራሱ ከአቅማችን ጋር ሳስበው ገዘፈብኝ። በመንፈስ ስንዱዎች አይደለንም። በመንፈስ ድርጁዎች አይደለነም። የተፈጠርንበት ሰዋዊነት እፍታ የት ላይ እንደሆን ግራ እስኪያገባ ድረስ ነው ምድራዊ የሆነ ዝም ብሎ ኩፍስ ነገር የመጨረሻ ደወል፤ ማስጠንቀቂያ ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚደመጠው … ታዲያ የእዮሩ ድወልስ ማን ያድምጠው?
  • ·         ኪናዊ - ሊሂቅ።

ሊሂቅነት ለእኔ የሰውነት ሊሂቂነት ነው። የሰው ጠረን ያለው ሊሂቅነት ብቻ ነው ኢትዮጵያን የሚታደጋት። ስለሆነም ለዚህ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው ሊሂቃን? ለመሆኑ በይመለከተናል አስበውት ይሆን ይህን የጣምራ የቅጣት እዮራዊ ደወል እንዴትስ አዳመጡት? ወይንስ ለፖለቲካ ትርፍ እና ኪሳራ ምንዛሬ ዝርዝር ቤት አሰኝቷቸው ይሆን? ከዚህ ከዓለሙ ውቂ ደብልቂው፤ ከኳኳቴ እና ድብልቅልቅ ወጥተን በስክነት የፈጣሪን መልዕክት ቢያንስ አዳምጠን ዕውቅና መስጠት የምንችለው በምን መልኩ ይሁን? ግን አቅም አለን? ለመሆኑ ደወሉ የስንቶቻችን በር አንኳኩቷል? አቅማችን የት ላይ ነው? በምን አጀንዳ ነው አቅምን እዬበተነው ያለው? ጦርነቱ ማን እና ምን፤ ምን እና ማን ነው? ጉዳያችን ምንድን ነው ሰው ወይንስ ቁስ? ግን መሬት መራድ እና ጦሱ ከስፊው መከራ ጋር ቢጨመር ቀውሱን ለመመከት ምን አቅም አለ? ቢያንስ ሊመጣ ይችላል ብለን እንኳን የተሰበሰበ ሃሳብ አለን? የተደራጀ መንፈስ አለን? እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ ስንል በዛ ውስጥ ያሉ ሥጦታዎችን አክብረን የልብ ነበርን? ወይንስ ተጋፍተነው ይሆን እንደ ገና ፈጣሪ የቁጣ በሩን የከፈተብን? እንሰበው፤ ፉከራ ግን አይደለም በማስተዋል ሁነን እንመርምረው ለማለት ነው። ዜናውን ደግመን ደጋግመን አዳምጠን የልባችን አጀንዳ አድርገን እነዛ የተረፉ ምንዱባን ዛሬም ፈተና ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን እንኳን አተረፍክልን ብለን አምላካችን ማመስገን ያለብን ይመስለኛል። የቀሩትንም የአስር ቤት ምንዱባኖችንም ከነ መደገፊያ ምርኩዛቸው ሆነውም ቢሆን ለዓይነ ሥጋ አብቃን፤ አሳዬን ብለን መጸለይ ይገባል። የሰይጣን ጆሮ ይደፈነው እና አጥተናቸው ቢሆንስ ኖሮ?
  • ·         ሰውን መቆጠብ ይቻላልን?

ሰውን በሰው ሰራሽ ዘዴ መቆጠብ ይቻላል። ሰውን መቆጠብ የማይቻለው በእዮር ቁጣ ዙሪያ ከሆነ ብቻ ነው። በሰውኛ ከሆነ ግን ዞር አድርገህ፤ አሸሽተህ፤ ግርዶሽ ሰርተህ፤ ስልት ነድፍህ፤ ሌላው የአንተ ያላልከውን ፊት ለፊት ማግደህ፤ የአንተውን ግን መስጥረህ ልታተርፈው፤ ልትታደገው ትችላለህ ልክ ይሄ አስቸኳይ ጊዜ ይሁን የ27 ዓመቱ የእና ቤቢሻ መቀማጠል እነሱን እንዳይነካ በብልጠት እንደ ተከወነው፤ ግን በእዬር ቁጣ የሰው ቁጠባ ባለክህሎቱ ባይገኝም ግን የታለመው ተቆጣቢ አይድንም። የሰው ልጆች የሰውኛ ጥበብ፤ ስልት፤ ብልጠት፤ ብልሃት ሰውህን ለይተህ፤ ነጥለህ አታተርፈውም። የሰው ልጅ የሥልጣኔ ደረጃ ሰው መፍጠር አልቻለም። ሰው መሰል በሰው ሠራሽ ሽቦ የተጠመጠመ አሻንጉሊት ብቻ ነው ፕላስቲክ መሥራት የሚችለው አቅሙ የሰው። የሰማዩንም ቁጥ በኤሌትሪክ ገመድ ቅጥልጥል ማገድ አይቻልም። ስለዚህ የሰው ቁጠባ በሠው ሰራሽ ክህሎት ለተወሰነች ወቅት ቢቻልም፤ ከእዬር አደባባይ ቅጣት፤ ቁጣ፤ ነዲድ ማትረፍ አይቻልም። በፍጹም! ስለዚህ ወደ ሰውኛ አቅም ተመልሶ ፈጣሪን መለመን ግድ ይለናል እከሌ ተከሌ ሳይባል። በሰው ልጅ አፈጣጠር ላይ የበዛ መቀናጣት፤ መራጠጥ አለ … በፈጣሪ ቅብዕ ላይ መረጋገጥ፤ መረማመድም አለ። ይቅር ይበለን።
ፈጣሪ ከሁሉ አልቆና ዕጹብ ድንቅ አድርጎ በፈጠረው ሰው ላይ ተፈጥሮውን በመቀዬር፤ በመበዬድ ያለው የቀዶ ጥገና ሂደት፤ ያን ዘመን መጥ መጥኔ የፎቶ ሾፕ አስቃቂ ትውና ሲታይ፤ ሰው „ሰው“ መሆኑ ታላቁን ስጦታውን ትቶ ከወገብ በላይ ይሁን በታች እንደ ዱር እንሰሳ ቀንድ እና ጅራት ተክሎ ሲታይ ልኩን ያጣ መቀናጣት ነው። ሰው ፈጣሪ አምላክን ሊሆን አይችልም። ፈጣሪ አምላክ የፈጠረው ሰው የፈጣሪን ኪነ ጥበብ ጸጋ አልተሰጠውም። ልክ አለው። መጠን አለው። ግፍም ስንሰራ፤ በፖለቲካ ስነወሰልትም ቤተ ሙከራው በሰው ልጅ ላይ ስለሆነ በቀጥታ ህግ በመተላለፍ ከፈጣሪ ሥልጣነ ክህሎት ጋር እንላተማለን። እንድንኖር ከተፈቀደልን ልክ አለፍ ብለን ስንዳፈረው ይህን መሰል ከቶውንም ማስቆም የማይቻል መልዕክቱን ይልካል። ይህን ለማድመጥም ልብ ይጠይቃል። ልክ እንደ እንደ ብልሁ ቀደምት ራስ መንገሻ የሖንስ የሰው የሆነ ልብ። ሰው መቆጠብ የሚቻለው የሰው የሆነ ልብ ሲኖር ብቻ ነው ከእግሩ ሥር ወድቀን ስለሰራነው ሥውር የሸር ወረርሽኝ ይቅርታ ስንጠይቅ። በሰው ቁስል ከሆነ ግን ተያይዞ ይሆናል መከራው። ዳኛው አለና ከአደባባዩ። መቼስ እንደ እኛ በኔት ሸር መጠለያ አልቦሽ ጎዳና ታዳዳሪ አይሆን ነገር የፈጣሪ ቁጣ።
  • ·         ቁስ እና ቁስ በጦርነት አታካቱን። 

ጉግሱን ዝም ብሎ ለሚያደምጠው ለቁስ ብቻ ነው። ቁሱ ደግሞ ሦስትም አይደለም፤ አራትም አይደለም ወይንም እንደ ሲዎዞች ሰባት አይደለም አንድ አንጨት አራት እግር ያለው፤ አንድ ያልተደላደለ መደገፊያ ያለው፤ ወለል እንኳን የለውም ሰው ለሰራው አራት እግር በቃ ለዛ ነው ሲያነሳን ሲጠልን አባጅቶ ያከረመን። ለዛውም ተሸከምነው ለማንሄደው። ቢሆንማ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በሆኑበት። የጦርነቱ ዓውድ ይሄው ብቻ ነው። ለእንጨት። ሴት ልጅ ወንድ ልጅን ዘር አልባ ለማድረግ ግፍ በምትፈጽምበት ሀገር የአዳም መፈጠር እና የህይዋን መፈጠር ኢትዮጵያ መሬት ላይ ህግጋቱ ሲጣስ ስለምን ይሄ ዓይመጣም ብለን ማሳብ አንችልም። ያቺ ጨካኝ ሴት እናት ናት፤ እህት ናት፤ ሚሰት ናት፤ አክስት ናት የተፈጠረችው ለዚህ እዮራዊ አምክንዮ ነው። እራሱ በምን ትውፊት ደፍራ ያን የተመሰጠረ አካል ለማዬት ዓይኗ እንደፈቀደ እራሱ ይህቺ ከቤርሙዳ ትርያንግል የመጣች የጉዶች ገድጓድ ናት። ሰው ለማለት ይቸግረኛል። ሴትነት እኮ በራሱ የፍጥረት ንጥር፤ ህብር ቀለም ውስጥ ሥነ - ምግባር አለው። የማይፈቀዱልን ብዙ ነገሮች አሉ። አብሶ ኢትዮጵያዊ ሴት መሆን ብዙ የትውፊት ያልተጻፉ ህግጋታ አሉ። ልንተላለፋቸው የማይገቡ። በትውፊት ለመኖር መፍቀድ አለመሰልጠን አይደለም። መጋፋቱ ነው ራስን መጣሱ።
ሴት እናት ስትሆን ሥልጣን እና ክብረቷ ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጣት የርህርህና፤ የሙሉ ሥነ - ምግባር ሰማያዊ መክሊት በውስጡ አለበት። ያን ጥሳ የተገኘች፤ ያን ረግጣ የተፈጠረች ክፉ ሴት ራሷንም ሰርዛላች፤ ሰማያዊ ህግጋትምን ጥሳለች። እራሷ ሰው ሆና መፈጠሯ የለም። ስርዙ ነው። ስለዚህ ፈጣሪ በፈጠረው ፍጡሩ ላይ ይህን መሰል ከሞትም አሟሟት የቁም ሲሆን አዘቅዝቆ ተመለከተ፤ አዳመጠ፤ ቻለ አሁን በተቀራረበ ጊዜ ውስጥ ጠንከር ያለውን መልዕክት በድርብ ላከ። የአዳምን መፈጠር በቅድስት ኢትዮጵያ ስለታረደ።
  • መሰቃዬት።

አዎን ብዞዎቻችሁ ተኝታችሁ አድራችሁ ሊሆን ይችላል፤ እኔ ግን አልቻልኩም። ነገ ደግሞ ተረኛው ማን ይሆን? የትስ ይሆን የፈጣሪ የምልክት ቀጠሮ? የትኛው መከረኛ ባዕት ደግሞ ይሆን ቤተኛ የሚሆነው? ከብደቱስ መጠኑስ ምን ያህል ይሆን? የአሁን የውሃ ሙላትም፤ የዶፍ መጠን መክብድ ነው፤ ቀጥሎ ጦሮ ንፋስ ይሆን? የሃይቆች መናወጥ ይሆን? የተዘራው ሳይበቅል ይቀርን? የበቀለው ላይ ተባይ ይሰፍርበት ይሆን? ፋታ ባጣ ሁኔታ የለመድኩት በሃኪም ትዛዝ የተገዛው ፍራሼ ላይ እንኳን መተኛት አልቻልኩኝም - ጎረበጠኝ። ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህምድ „ ታውቃላችሁ የአቤል ደም ይጮሃል፤ እኔ ያሰብኩት ወንዞች ደም ይሆናሉ ብዬ ነበር“ የሚለውን ዕድምታቸውም እኔ እጋራወለሁኝ። በሴራ መረብ የተሠሩ ማናቸውም ሸሮች የጊዜ ጉዳይ ነው …
የሆነ ሆኖ ከዜናው በኋዋላ ሃዘኔን ለማስታገስ ብሎጌ ላይ ትንሽ ነገር ለጣጠፍኩኝ - ከትናንት በስትያ። አዬሠራሁ በማስቀምጠው የፍቅራዊነት ዩቱብም ላይ አንድ የቪዲዮ ክሊፕ ለጠፍኩኝ። ለወዳጆቼ በኢሜል ለመጣልኝ መልዕክት መልስ ላኩ፤ ግን ሰውነቴን አዝሎ እንቅልፍ ሊሆነኝ፤ ሃሳቡን አስረስቶ መንፈሴን ሊያሰባስብልኝ አልቻለም። በቅርቤ አንድ የኦርቶዶክስ የጸሎት ቤት አለና ዘወትር ክፍት ነበር፤ ትናንት ስሄድ አምላካችሁ አለ ክርችም ብሎ ተዘግቷል። ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ ብትከፈት ለዛሬ ምን አለበት ብዬ ወደ ቤተ መቀደሴ ተመልሼ ሻማዬን አብርቼ የሚሆነውን አደረኩኝ።
ይህ ነገር እንዲህ እዬቀጠለ ብሄድስ የሚለው የመንፈሴ መባተል እረፈት ነሳኝ እና ይህን ጫርኩኝ። እኔ የምጸፈው በገሃዱ ዓለም ስለሚኖሩ ነፍሶች ሳይሆን ቅኖች በመንፈስ ህይወት እንዲኖሩ የፈቀዱ፤ የወሰኑ ንጹሃን አሉኝ ብዬ ስለማስብ ለእነሱ ነው። ስለሆነም እስኪ በመንፈስ ሃዲድ ወደ አምላካችን በምንችላት አቅም ሁሉ ይህ ድንገቴ ቁር ይታገስ ዘንድ፤ የግል ሱባኤ የሦስትም // የሰባትም የአንድም ቀን የአንድ ሰዓትም ይሁን እንደ አቅም እንደሚቻለው የሁለቱ ሃይማኖቶች አማንያን እባክህን ፈጣሪ ሆይ በዚህ አትቅጣን፤ የባጀብን የሰው ቅጣት ይበቃናል በማለት ትጋት ቢኖር ቸር አምላክ ለአንድ ንዑድ ነፍስ ሲል ምህረቱን ይልካል። ከባድ ነገር ነው። ትናንት በቅርብ ርቀት ከመቀሌ፤ ዛሬ ደግሞ በጉራጌ ዞን በጣምራ ቁጣ፤ በጣምራ የቅጣት ዓይነት። ነገስ የት እና መቼ? ያሰፈራል … አጅግ ያስፈራል … ሆድም ያባባል።
  • ·         የቀደመው ጭንቀቴ የገለጽኩበት በዚህ መልኩ ነበር። 

„ምልክት። ምስክር። ምድር ቁስ አይደለችም። የመንፈስ ቅዱስ ማረፊአ እንጂ! አምናረክሳትም እምናስቀጣትም እኛው ራስችን ነን።“
  • ·         የኬኒያ አትኩረተ ምልከታ የቀደመ ነው።

PM Abiy Ahmed faces an uphill task in uniting and reforming Ethiopia
Abiy Ahmed to be sworn as Ethiopia's new PM
President Uhuru Kenyatta welcomes the Ethiopian PM Abiy Ahmed
Abiye Ahmed to be sworn in as Ethiopia's new prime minister
Ethiopian PM resigns

ቅኖቹ የልዑል እግዚአብሄር ወዳጆች፤ የእምዬ ኢትዮጵያ የልቦች፤ እስኪ „አቤቱ እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በደላችን አይሁንብን“ ብለን መንፈሳችን ሰብስበን ወደ ሁሉ ጌታ ማረንን እንላክልት። ቢማለደን፤ ይቅር ቢለን።
ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ዓራት ዓይናማው መንገዳችን ነው!
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚሰጢር!

„በሰማይም ያለም ቢሆን በምድርም ያለ ቢሆን ረቂቅም ግዙፍም ቢሆን ሁሉም የሱ ገንዘብ ሁሉም በሥራቱ ጸንቶ ይኖራል።“
 (መቃብያን ሣልሳ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩)


እግዚአብሄር ይስጥልኝ - ኑሩልኝ። መሸብያ ጊዜ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።