7.2 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ወይስ እናፈርሳለን ? መቼም << አብዛሀኛዎቹ የመንግሥት ሰዎች ቁርጥ ላይ እንጂ ቁጥር ላይ እስከዚህም ናቸው! >> የሚባለውኮ በምክንያት ነው! የከተማ እና የመሠረተ ልማት ሚንስቴር ከአመት በፊት ይፋ ባደረገው "ዕቅዱ" 7,200,000 (ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ቤቶችን በ 10 ዓመታት እገነባለሁ ብሎን ነበር ። ይህም ማለት፦ << በዓመት 720,000 ቤቶች ፤ በወር 60,000 ቤቶች ፤ በቀን ደግሞ 2,000 ቤቶችን እገነባለሁ! >> ማለት ነው! እንግዲህ ቁጥር የሚዳፈረው ተግባረ ዜሮው መንግስታችን ፤ በእስካሁኑ ልምዱ 400,000 ቤቶችን ለመገንባት 18 ዓመታት ፈጅቶበታል። አይደለም በቀን 2 ሺህ ቤት ሊሰሩ (ሊያመርቱ) ይቅርና ለፕሮፓጋንዳ ''ሰራናቸው '' ያሏቸው ዳቦ ቤቶች እንኳ ፥ በቀን 2 ሺህ ዳቦ ማምረት አልቻሉምኮ! ለመሆኑ ግን ሌላ ሌላውን ቁጥር ማግተልተሉን ተውትና ፥ ከታቀዱት 7 ሚሊዮን 2መቶ ሺህ ቤቶቹ ስንቶቹ ተመረቱ? ወይስ ደግሞ እቅዱ '' የ7.2 ሚሊየን ዜጎችን ቤቶች እናፈርሳለን!'' ነበር ወይ ?