የኢትዮጵያ መንግሥት ለስትራቴጂ ብቻ የሚፈለግ ከሆነ ...
ዓይን። „የፈረደብህ በግፍ እንዳይደለ ትገልጥ ዘንድ ስለ ሰው ሁሉ የሚያስብ ካንተ በቀር ሌላ ፈጣሪ የለምና፤ ስለ በደለኞች፤ ሰዎች ለመከራከር ወደ አንተ የሚደርስ ዳኛ ማነው።“ መጽሐፈ ጥብብ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነ ሻ። „በአሰላ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የአማራ እና የሌላ ብሔር አባላት የሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዬች የመስቀል በዓል የደመራን ዝግጅት ተከትሎ ውጥረት እና ውክቢያ ውስጥ እንደሆኑ ኑዋሪዎቹ ለልሣነ _ ዐማራ ገልፀዋል።“ መስከረም 04/2011 ዓ . ም https://www.facebook.com/AmharaPress/?__xts__[0]=68. መነሻዬ የለጠፍኩት ጉዳይ ነው። ተያያዥ ጉዳዮችንም አክላለሁኝ። ኦቦ በቀለ ገርባ ስትራቲጂካዊ የ150 ዓመት ትግል ነፃነትን አሳዬን፤ የሞቱት ተነስተው ባዩልን ባይ ናቸው። ነገም ለስትራቲጂ ከሆነች ኢትዮጵያ የምትፈለገው ምን አስኪሆን ይሆን የሚጠበቃው የ ኢትዮጵያ መንግሥት የአብይስ ካቤኔ? ... ወደ ቀደመው ስገባ ዛሬ ጥዋት አንድ መሰረታዊ ነገር ከልሳነ አማራ ሚዲያ አዳመጥኩኝ። አሰላ ላይ መስቀልን ለማክበር ስጋት እንዳለ። አሰላ ላይ ብቻ ሳይሆን ቄሮ በተዳረጀባቸው አካባቢዎች፤ ጄኒራል አቶ ጃዋር መሃመድ በሚመራቸው ኔቶች ሁሉ መሰል ስጋቶች ይኖራሉ። ስጋቶች ካሉ ልዑል እግዚአብሄር የማያውቀው ስሌላ ቤት መቀመጥ ነው። በነገራችን ላይ አሰላን አየኋዋት ምንም ለውጥ የላትም። በዚህ አይነት ጢቾ፤ አምኛ፤ ዲክስስ፤ ሴሩ ምን ላይ ይሆኑ እል ለነበረው ግብረ ምላሽ ...