ልጥፎች

ከዲሴምበር 23, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ፅናት ማሸነፍ ነው።

ምስል
 ያጣኽውን በማጣትህ ከፀፀተህ በገደልከው በደል ውስ ለመኖር አትፍቀድለት።   አገርን ፈጣሪ ከመረቃት አይዞሽ ባይ እረኛ ይሰጣታል። ይህ ካልሆነ አገር የህዳር ዝናብ እርግማን እንደታዘዘባት ትረዳለህ። ሰብል አልባ ትውልድም አደራም እራፊ መጠጊያ ዬልብ ዓይን የላቸውም እና።    የክፋት ሽርሽር በደግነት ላይ ማፈናቀልን ለመተግበር ነው።    ገዳዮች እርቃናቸውን ተወልደው፣ እርቃናቸውን ኖረው፣ እርቃናቸውን ከመሬት ጋር እርክክብ ይፈፅማሉ። ክትመት።    ትዝታ ሲሄዱ ማደር ነው።    ፅናት ማሸነፍ ነው።    የህሊና ድንግልና የትውፊት ማህደር ነው።     ማድመጥ ሥጦታ ነው። እራሱን የማድመጥ አቅም ያለው ሌላውን ለማድመጥ ዳጥ አይሆንበትም። አቅል ያለው ትውልድ የሚገነባውም ይህ መሰል ሰብዕና ያላቸው መሪዎች ሲኖሩት ብቻ ነው። መታደል ከበለፀገ፣ ምርቃትም ከተበራከተ የተስፋ አዝመራ ይኖራል።    ትውልዱን የምናባክነው እኛ ነን። ከትናንት የተሻለ ሥርዓት መፍጠር ስላልተቻለን። ለምን? በውዳሴ ሥካር አቅም ስለሚባክን።  ትውልዱ ይረገማል። ረጋሚዎቹ ዘመኑን አባካኞች ናቸው። የእነሱን ዘመን አክስለው፣ የዛሬውን ቀምተው፣ የነገን ማሳረር የተፈጠሩበት ነው።  ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019        

ደግነት የሚያኖረው የራስን ኑሮ በማኗኗር ነው

ምስል
 ደግነት የሚያኖረው የራስን ኑሮ በማኗኗር ነው። ይህ ደግሞ ለትውልድ ያለአስተማሪ የመኖር የኔታ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ክፋዎች ሳይኖሩ የኖሩ ይመስላቸዋል። መኖራቸውን ቀምተው የሚኖሩት ኑሮ ሙጃ መሆኑን አያስተውሉትም እና።

ምስል
 ክፋዎች ሳይኖሩ የኖሩ ይመስላቸዋል። መኖራቸውን ቀምተው የሚኖሩት ኑሮ ሙጃ መሆኑን አያስተውሉትም እና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

የዕድሜ ዕርጅና አይጭነቅህ፣ በጭንቅህ ውስጥ እራስህን የሸጥክበት ዘመን ከሌለ።

ምስል
 የዕድሜ ዕርጅና አይጭነቅህ፣ በጭንቅህ ውስጥ እራስህን የሸጥክበት ዘመን ከሌለ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ልብ ከሰጠህ።

ምስል
 የፍቅርን ሙሉ ዋጋ ለሰጠኽ ቀን ካላከበርከው ያጣኽው ዕለት ተቋም ይከፍትልኃል። ትማርበት ዘንድ አዲስ ህሊና ይሸልመኃል፣ ልብ ከሰጠህ።  ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ምን ብላ?

ምስል
 በእሾህ ውስጥ የበቀለች ፅጌረዳ ለእሾኽ ምክር ትለግሰዋለች። ምን ብላ? አትዋጋ እያለች። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ቅን ልብ ቧ ፏ ያለ የተከፈተ የገነት በር ነው

ምስል
 ቅን ልብ ቧ ፏ ያለ የተከፈተ የገነት በር ነው። የቅኖች ዘመን ቅንነት ብቻ ነው። ቅኖች ምንም አይኑራቸው በህሊና ድንግልናቸው ብቻ የመንፈስ ዲታዎች ናቸው። ቅኖች የአደራ ዕዳ የለባቸውም። የሰው ልጅ የተፈጥሮ መርህ ነው። የተፈጠረበትን ሲጥስ ማን ይባል፣ ምንሥ ይባል ይሆን? Sergute©Selassie ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019      

የሳንባን ሥራ ለማቃለል ዕውነትን ይፈልጉ።

ምስል
 የሳንባን ሥራ ለማቃለል ዕውነትን ይፈልጉ። ዕውነት ያለበት ቦታ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ድርሽ ላይል እርግማን አለበት እና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ገላጣ ላይ የተጋለጠ ዕብለት ብዙም ፕሮፖጋንዲስት አያምረውም።

 ገላጣ ላይ የተጋለጠ ዕብለት ብዙም ፕሮፖጋንዲስት አያምረውም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019

አማራነት ሰውነት ነው።

ምስል
 አማራነት ሰውነት ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019    

ድፈሩት! አማራ ነኝ በሉ!

ምስል
 አማራነት ከፀጋው የሚነሳችሁ፣ ከበረከቱ የሚነፍጋችሁ፣ ከምርቃቱ የሚያሳጣችሁ የለም። ድፈሩት! አማራ ነኝ በሉ! ቸሩ አማራነት ሁሉም አለውና ያሰብላችኋል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019  

አማራ ነኝ የምትሉ ዝም ብላችሁ አዳምጡት፣ አጥኑት። ወደ መልካም ነገር ይመራችኋል።

ምስል
 አማራ ነኝ የምትሉ ዝም ብላችሁ አዳምጡት፣ አጥኑት። ወደ መልካም ነገር ይመራችኋል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019  

አማራ ስትሆን ፈርኃ እግዚአብሄር ፈርኃ አላህ ይገዛኃል። ይልኙታም ይዳኝኃል።

ምስል
 አማራ ስትሆን ፈርኃ እግዚአብሄር ፈርኃ አላህ ይገዛኃል። ይልኙታም ይዳኝኃል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ጥበብን በሴቶች ተፈጥሮ ውስጥ ተመስጥሮ ታገኜዋለህ።

ምስል
 ጥበብን በሴቶች ተፈጥሮ ውስጥ ተመስጥሮ ታገኜዋለህ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019 

ቅኖችንም፣ ቅንነትንም የፈጠረልን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን

ምስል
 ቅኖችንም፣ ቅንነትንም የፈጠረልን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን። የእነሱ መኖር ከጨለማዊ ቀስት እንድንበት ዘንድ ልዩ ምርቃት ነውና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019 

ክፋነት የህሊና እድገት ዘገምተኝነት ነው።

ምስል
 ክፋነት የህሊና እድገት ዘገምተኝነት ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019 

#ጤናችን።

  #ጤናችን ። ከአቶ ኃይሌ አሳምነው ገፅ የተወሰደ ለጤናችን። "የሳምባ ምች/Pneumonia የሳምባ ምች በአንዱ ወይም በሁለቱም ሳምባ ላይ የአየር ከረጢቶች ላይ ኢንፌክሽን በሚፈጠርበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ የሳምባ ምች ከመጠነኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊያደርስ የሚችል ሲሆን በህፃናት፣ እድሜያቸዉ ከ65 ዓመታት በላይ ለሆኑ አዛዉንቶችና የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ በተዳከመባቸዉ ሰዎች ላይ እስከ ህልፈተ ህይወት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት ሊያመጣ ይችላል፡፡ የህመሙ ምልክቶች የህመሙ ምልክቶች:- የህመሙ ምልክቶች ህመሙን እንዳመጣዉ የጀርም አይነት፣ የታማሚዉ እድሜና አጠቃላይ የጤንነት ሁኔታ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡ መጠነኛ የሳምባ ምች ያላቸዉ ሰዎች የህመም ምልክቶቻቸዉ ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸዉም ህመሙ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ የህመም ምልክቶቹ የሚከተሉትንም ሊያጠቃልል ይችላል፡- • ትኩሳት፣ማላብና ብርድ ብርድ ማለት • ሳል • በሚያስሉበትና በሚተነፍሱበት ወቅት የደረት ላይ ህመም • የትንፋሽ ማጠር • ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣ተቅማጥ ናቸዉ፡፡ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ? የአተነፋፈስ ችግር፣ የደረት ላይ ህመም፣ የማይቀንስና ከ39 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ ትኩሳት፣ የማያቋርጥ ሳል በተለይ መግል የመሰለ አክታ ከገጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች የሳምባ ምች ማንኛዉንም ሰዉ ሊያጠቃ ይችላል፡፡ነገር ግን በጣም ተጋላጭነትን ከሚጨምሩት ዉስጥ • ከ2 አመትና ከዚያ በታች የሆኑ ህፃናት • ከ65 አመትና በላይ የሆኑ አዛዉንቶች ሌሎች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ • የበሽታ መከላከል አቅምዎ የተዳከመ ከሆነ፡- የኤች አይቪ ኤድስ፣ የአካል ንቅለ-ተከላ የተደረገላቸዉና የካን

እኔ የሚገርመኝ ጦርነቱ ሲጀመር ምን ሲሉ የነበሩ፣ ዛሬ ምን እያሉን እንደ ሆን ሳዳምጥ ይገርመኛል። ዝም ቢሉ ምን አለ?

ምስል
 እኔ የሚገርመኝ ጦርነቱ ሲጀመር ምን ሲሉ የነበሩ፣ ዛሬ ምን እያሉን እንደ ሆን ሳዳምጥ ይገርመኛል። ዝም ቢሉ ምን አለ? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20/12/2021    

ዕውነት ዕጣ ነፍሱን መለመላውን ቢቆምም እኔ አልለዬውም።

ምስል
 ዕውነት ዕጣ ነፍሱን መለመላውን ቢቆምም እኔ አልለዬውም። ዘመኔን ሁሉ የተገበርኩበት እናቴን የበሞቴ ልዕልቴን እሽ ብዬ ፈቃዷን ሳልፈፅም ፀፀትን የታቀፍኩበት ነውና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.12.2020  

#ያልተደፈረው መከራ። ምፃዕተ አማራ የሴቶች በፋሽቱ ህወኃት መደፈር እና ባሊህ ባይ ማጣት።

ምስል
አቋም የለሽ ሰብዕና ፖለቲከኛ ሊሆን አይችልም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20/12/2021   #ያልተደፈረው መከራ። ምፃዕተ አማራ የሴቶች በፋሽቱ ህወኃት መደፈር እና ባሊህ ባይ ማጣት። 1)በታቀደ የትግራይ ህዝባዊ ሠራዊት የጭካኔ የመደፈር አደጋ የደረሰባቸው እህቶቻችን የሥነ ልቦናም፣ የተደራጀ ህክምና አገልግሎት እንዳላገኙ ከሀበሻ ዩኒቲ ከተጣፈው ጦማር ተረዳሁኝ። በውጫሌ፣ በመርሳ፣ በኡርጌሳ በቆቦ፣ በወልደያ፣ በቆቦ፣ በሃሙሲት፣ የሚገኙ እህቶቻችን የከፋ ግፍ ተፈፅሟባቸዋል። በ4 መሳሪያ የተደፈረች እንዳለችም ጋዜጠኛ ብሥራት መንግሥቱ ይገልፃል። ይህን መከራ የሚሸከም፣ የሚመራ የአማራ ፖለቲካ ደግሞ የለም። በጥቃቅን ትንኝ ጉዳይ ትርምስ ነው እማዬው። የሃሳብ ድህነት አና ብሏል። ለነገሩ በዘመነ ኮረና 100 እስረኛ በአንድ ክፍል የምታሥር አገር? የሆነ ሆኖ ትልቅ ፕሮጀክት ይጠይቃል። የሙያተኛ። ጋዜጠኛው ስልክ ቁጥር ሰጥቷል ሌላ የጨመተ ተከታታይ ተግባር ያልጀመራችሁ እና የምትችሉ እባካችሁን እርዱ። ስልክ 0919195135 የሚገርመኝ የአማራ ህዝብ እስከመቼ በውጭጭ መዋጮ እስከ መቼ ህልውናውን ሊያስቀጥል ይሆን? 2) በድጋሚ ጋሸና ሲያዝ ጋሸና እያንዳንዱ መኖሪያ በእሳት እና በመትረዬስ ነዷል ይላል የዛሬው የፈታ ደይሊ ኒውስ። ከዚህ በተጨማሪ ተመልሰው ሲይዙት ህወኃት መራሹ የትግራይ ህዝባዊ ሠራዊት ሁለት ነፍሰ ጡር እናቶችን፣ አንዲት አዛውንት እናትን ሲደፍር ሁለት ህፃናትን በአደባባይ ረሽኗል ይላል የፈታ ደደይሊ ኒውስ። ሰሞኑን ዘጋቢወቹ ከዛው አካባቢ ነበሩ። ከዚህ ሲኦል ጋር ነው ድርድሩ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20/12/2021 እንበርታ።

#ተስፋችን ጥግ አናሳጣው።

ምስል
  #ተስፋችን ጥግ አናሳጣው።     አንድ ዕውነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። ሰው ሆኖ ተፈጥሮ እኛ እንደ ቅዱስ አድርገን የምናዬውም ሰው ነው። ይህን ግድፈታችን መቀበል ግድ ይለናል። በህይወታችሁ ውስጥ በተለዬ አጋጣሚ በተለዬ ሁኔታ የተለዬ ችሮታ የምትለግሱት// የምትለግሷትም ሰው ናት ብላችሁ ተቀበሉት። መፀሐፈ ሄኖክ ደቂቃን የሚላቸው መላዕክታን መውደቃቸው የምድር ክፋት ምንጭ መሆናቸውን ያመሳጥራል። ይህ ስላልተሰጠኝ አልገባበትም። የጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ህይወት ብቻ ሳይሆን 100 እስረኞች በአንድ ክፍል ውስጥ አታሠር አሳስሮኝ በግል ሜሴጅ ሊስት ውስጥ ላሉ ላቀረቡኝ እህት እና ወንድሞቼ ስልክ ለዶር ሊያ ታደሰ ያቀርብኩትን አቤቱታ ብቻ እሷ ዶር ቴወድሮስ አድህኖም ማለት ናት። ተስፋ አታድርጊያት የሚል መልስ አግኝቻለሁ። ይህ አደገኛ አካሄድ ነው። እኔ በወሮ ቀለብ ስዩም ዙሪያ ፅፌ አወንታዊ መልስ አግኝቻለሁ። በሥራቸው ትጉህ ሰው ናቸው። አፍ እላፊ ሲሄዱ አላዬሁም። ጭምት ናቸው። የተሻለ ሥርዓት ቢኖር እኒህ ሊቅ ጥሩ ህዝባዊነት ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁ። ሁሉን አውግዘን መጠጊያችን ምን ሊሆን ነው? ሁሉን ጠልተን ከማን ጋር ልንኖር ነው። ፍፁም ሰው የለም። ተስፋችን ጥግ አናሳጣው። ሹመታቸው ከቀጠሉት ውስጥ እኔ እንኳን ደስ አለወት ያልኩት ለሳቸው ብቻ ነው። እኔ በዶር ዳንኤል በቀለም ተስፋ ስላለኝ ነው አቤቱታ እማቀርበው። የደነገለ፣ የፀዳ መንፈስ አለ በምለው ሰብዕናም እምታዘበው ዕውነት አለ። ሰው ሰው ነውና። ሰው ሲሳት ደስ ይለኛል። ካልተሳሳተ ያ ሰው ሰው አይደለምና። ደከም ሲልም እንዲሁ። ሰው ሊደክመው ይገባል። ሊያጠፋ ይገባል። ፍፅምና መጠበቅ አይገባም። በተለይ የአማራ ፖለቲካ መሪም፣ ተቋምም ሁነኛም የለውም ይህም ሆኖ ሁሉን ጠል፣ ሁሉን አግላይ ከሆነ አወ

ጎንደር የአፍሪካ የአጤወች ፓላስ፤ የጥቁሮህዝብ የመናጋሻ ርዕሰ ጉልላት የባህል አውራ ናት።

ምስል
  ከአቶ አዳነ ጌትነት ፔጅ ከጎንደር ቱዩብ የተወሰደ።     ጎንደር የአፍሪካ የአጤወች ፓላስ፤ የጥቁሮህዝብ የመናጋሻ ርዕሰ ጉልላት የባህል አውራ ናት። ስለተፈጠርኩባት ሳይሆን ከምድር በላይ ብቻ ሳይሆን ከምድር በታች ታሪኳ ምስክር ነው። ለዚህ ነው ህወኃት በጥርሱ ነክሶ የያዛት። ግን ዓይነታው ጎጃም ቅኔ ሆነላት። ተመስገን። "ጎንደር - ታሪካዊ የመናገሻ ከተማ፤ ▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔ ጎንደር ከአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር 175ኪ.ሜ፣ ከአዲስ አበባ 738ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ታሪካዊ የመናገሻ ከተማ ናት፡፡ ከተማዋ በውስጧ በ17ኛው እና 18ኛው ክፍለ ዘመን የተሰሩ በርካታ ታሪካዊ የመስህብ ሀብቶችን ይዛ በመገኘቷ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ቱሪስቶች ተመራጭ መዳረሻ ናት፡፡ በታሪካዊቷ ከተማ እና አካባቢ የሚገኙ የመስህብ ቦታዎችን እንዲጎበኙ ግብዣችን እያቀረብን ሰለ ጐንደር ያዘጋጀነውን ጹሑፍ አንብበው ለወዳጅዎ ያጋሩት ዘንድ አቅርበንልዎታል፡፡ የጎንደር ስያሜ እና አመሰራረት፤ ▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔ ጎንደር የሚለውን ቃል ለስያሜ እንዴት መጠቀም እንደተጀመረ ብዙ አፈ-ታሪኮች ይነገራሉ፡፡ በርካታ ሰዎች የጐንደር ስያሜ ምንጭ ነው ብለው የሚያምኑት የሚከተለውን አፈ-ታሪክ ነው፡፡ አፈ ታሪኩ በከተማዋ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወንድማማቾች በመካከላቸው የተፈጠረውን የድንበር ጠብ ለመፍታት ወደ ሽማግሌ እንደሄዱ ይተርካል፡፡ ሽማግሌዎችም የወንድማማቾችን ክርክር ከሰሙ በኋላ ለታላቅየው “አንተ በዚህ ተቀመጥ” ብለው ታናሽ ወንድሙን ደግሞ “አንተም ከወንድምህ ጎን እደር” ብለው አስማሟቸው ይላል፡፡ ከዚህ ጀምሮ “ጎን እደር” የሚለው ጐንደር በመባል መጠራት እንደጀመረ አፈ ታሪኩ ያስረዳል፡፡ በሌላ በኩል የጎንደር ስያሜ “ጉንደ ሀገር” ማለት ነው

ዕውነት ብቻን ያስቀራል።

 ዕውነት ብቻን ያስቀራል። ለህሊና ግን ትፍስህት ነው። ለትውልድ የአደራ ሙዚዬም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20/12/2021

ጤናችን።

  ጤናችን። ተርኋሚ መላኩ ብርኃኑ እንዳጋሩት ስትሮክ እየጨረሰን ነው (መላኩ ብርሃኑ) …………………………………… "ይህንን መረጃ ሳነብ ያገኘሁት ነው። ለሁላችንም እንዲጠቅም ወደአማርኛ መልሼዋለሁ። ስትሮክ የዕለት ከዕለት ችግራችን እየሆነና የሁላችንንም ጓዳ እያንኳኳ በመሆኑ መረጃው ይጠቅመናል ብዬ አስባለሁ። እባካችሁ ሼር በማድረግ እውቀት አሸጋግሩ። ምናልባት በዚህ መረጃ የአንድ ሰው ህይወት ታተርፉ ይሆናል። እኔ በበኩሌ ከ8 አመት በፊት ይህ መረጃ ቢኖረኝ ኖሮ ምናልባት ወንድሜን ከሞት የማትረፍ እድል ይኖረኝ ነበር። እሁድ ቀን ጠዋት ነው። ወደጓደኛዬ ኒካ ስነስርአት ለመሄድ ስነሳ ወንድሜ ቀድሞኝ ከቤት ወጥቶ ስለነበር ከቤታችን ደጃፍ የሚገኝ አስፋልት መንገድ ዳር ላይ ተቀምጦ አይቼው ነበር። ከአይኑ እስክጠፋ ቁጭ ባለበት ቦታ ሆኖ ያየኝ እንደነበር ያወቅኩት ርቄ ሄጄ ዘወር ስል ወደኔ አቅጣጫ ያይ እንደነበር በመታዘቤ ነው። ከሁለት ሰአታት በኋላ ፑል በመጫወት ላይ እንዳለ ተዝለፍልፎ ወደቀ ተብሎ ተደወለልኝ። ስደርስ ቤተዛታ ሆስፒታል ገብቶ ስትሬቸር ላይ ተኝቶ አገኘሁት። ሃኪሞች ከሻይ እስኪመለሱ እርዳታ አላገኘም። ቀስ በቀስ ራሱን ሙሉ በሙሉ ሳተ። ችግሩ ምን እንደሆነ አላወቅንም የነገረንም ሃኪም የለም። በመጨረሻ ቤተዛታ ከአቅሜ በላይ ነው አልችልም አለ ……ጥቁር አንበሳ በበኩሉ አልጋ የለኝም ሲል…እኛም ለጭንቅላት ምርመራ የታዘዘልንን ኤምአርአይ ፍለጋ ስንንከራተት ሰአቱ ገፋ። መጨረሻ ላይ ሀያት ሆስፒታል አልጋ ተገኝቶ የፅኑ ህሙማን ጥብቅ ክትትል ክፍል (ICU) ገባ። በዚያው ሁኔታ ሳለ በሶስተኛው ቀን ህይወቱ አለፈ።ገና በ22 አመቱ። ለቤታችን ታላቅ ሃዘን ሆነ። ዛሬ ድረስ ሁኔታውን ሳስበው እንባዬን ማቆም አልችልም። እጅግ የምወደውን

መማር ይታገዳል። መተካትም ይታገዳል። ኢትዮጵያ ወደ ማይምነት ጉዞ የቁልቁሊት እንዲህ ትነጉዳለች። 20.12.2020

ምስል
  ዕለተ - ትውልዱ።     መማር ይታገዳል። መተካትም ይታገዳል። ኢትዮጵያ ወደ ማይምነት ጉዞ የቁልቁሊት እንዲህ ትነጉዳለች። ለስሙ የትምህርት ጉዳይን የሚከታተሉ፣ የወጣቶች፣ የሴቶች ጉዳይን የሚከታተሉ መ/ ቤቶች ተደራጅተዋል። መማር የሚፈቀድላቸው መማር የማይፈቀድላቸው ደግሞ አሉ። የአማራ ልጆች መማር አይፈቀድላቸውም። ይህ #ስውሩ የዚህ #አውሬ ዘመን #ልዩ #መገለጫው ነው። #ለምን ? አመክንዮ ትንተናም፣ አመክንዮ ተጋድሎም ያልተደረገበት የነቀዘ መከራ ነው። ለግዴታ ዘወትር በግንባር ሥጋነት የሚገኜው የአማራ ልጅ ማህይም ይሆን ዘንድ ተበይኖበታል። ይህ የውስጥ አይደለም። ከዚህ የሚነሳ የተጋድሎ ዓይነትም አላዬሁም። ተመስጥሮ የተያዘውን ገመና ገልጦ ይህን ድውይ ዘመቻ የሚያመክን ቁምነገር አላዬሁም፣ አልሰማሁም። የመንግሥት የትምህርት ተቋማቱ በምን ሸፍጥ ላይ እንደ ቆሙ መስታውቱ ዕውነቱ ነው። ዕውቀት የሚሳደድበት፣ የሚታገትበት አገር ኢትዮጵያ። #ወጣቶቹ ሲታገቱ ወላጆች ፈርተው ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንዳይልኩ መሰሪ ዕቅድ ነው። ታናናሾች ትምህርትን #ሃራም ይሉ ዘንድ የተሠራ ሸፍጥ ነው። ትውልድ ቀድሞ የተማረ ይረሸናል፣ ወይ ይታሠራል፣ እጩው ሊቅ ይታገታል ይፈናቀላል። ይህን መርምሮ የሚመጥን አመክንዮዊ አቅም ፈጥሮ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ከመድረስ፣ ከግለሰብ ሰብዕና ግንባታ ጋር እሰጣ ገባ ነው አቅም ሲፈስ ውሎ የሚታደረው። ያሳዝናል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20/12/2020

ዛሬ የምታዮዋቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ነገ የሉም ይፈርሳሉ ወይ ይዋጣሉ ወይ ይከስማሉ። በምኞት ያለውም "የኦሮሞ ብልፅግና" ያው ጠቅላዩ ነው ያሉት ጊዜው ሲደርስ ይረሸናል 20-12.2019

  ዕለተ - ትውልዱ። ዛሬ የምታዮዋቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ነገ የሉም ይፈርሳሉ ወይ ይዋጣሉ ወይ ይከስማሉ። በምኞት ያለውም "የኦሮሞ ብልፅግና" ያው ጠቅላዩ ነው ያሉት ጊዜው ሲደርስ ይረሸናል። ለምን? ትውልዱ ታስቦ ተጠንቶበት፣ ተመክሮበት፣ ህዝብ ተወያይቶበት ፓርቲ አይደራጅም። ለዚህ መሥፈርት የበቃው ባልደራስ ብቻ ነበር በአገር ውስጥም በውጭም ተመክሮበት። እርግጥ ገፊ ምክንያት ቢፈጥረውም። እስካሁን ባለው ተመክሮ ገፊ ጊዜያዊ ነገር ይፈጠራል አንድ የፖለቲካ ድርጅት በግጥምጥሞሽ አህዱ ይባላል ሳይሰክን ይበተናል። ወይ መራራ ስንብት እንደ ቅንጅት ይገጥመዋል። ይህ ክብር ሆኖ ይፎከርበታል። ይህ ማዕረግ ሆኖ ዳንኪራ ይመታበታል። ጉሮ ወሸባዬ ይባልለታል። አሳዛኙ ነገር አማራ የሆኑ ሰብዕናዎች የሚፈጥሯቸው ድርጅቶች መሪዎቻቸው አቅማቸውን፣ ክህሎታቸውን ጥበባቸውን የሚያሰክኑበት ዕድል ማጣት እንደ እኔ ኢትዮጵያ መፍትሄ፣ መድህን እንዳታገኝ ትናንትም ዛሬም የጉሮሮ አጥንት ሆኗል ብዬ አምናለሁኝ። የፖለቲካ ድርጅት መርኽዊ ነው። ከውስጥ የመነጨ ፈቃደኝነትን ይጠይቃል። በነገሮች አስገዳጅነት ሳይሆን በሰከነ ሩቅ ራዕይ ነው ሊፈጠር የሚገባው። ግን አልሆነም። ነገም ሞት አለ፣ ነገም መታሠር አለ፣ ነገም መታገት አለ። ለምን? የንቃተ ህሊና ድርቀት ስላለ። መቻቸል ሲያልፍም አይነካው ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል። ለምን? ከመርኽ ጋር ትውውቁ ሳያውቁ ያወቀ መስሎ በመታዬት የህዝብ መንፈስ ንደት ስንቅ እና ትጥቅ ስለሚሆን። #ለአመክንዮ ፣ #ለመርኽ ፣ #ለዕውነት #ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ለሸፍጥ፣ ለሴራ፣ ለበቀል፣ ለቂም፣ ለግድያ ግን እርግጥ ነው ለግርዶሽ ግድግዳ ወዘተረፈ ፕሮፖጋንዲስት ያስፈልጋል። ሰርክ በታንቡር፣ ሰርክ በጭብጨባ፣ ሠርክ በኦርኬስተር፣ ሠር

ዕለተ - ትውልዱ 20.12.2019

  ዕለተ - ትውልዱ። በቅንጅት፣ በሰማያዊ ፓርቲ የተሰው። ሁለቱም ፓርቲዎች ሞተዋል። የህግ ባለሙያው ሰማዕት ሳሙኤል አወቀ እና እጩ ሊቅ ሰማዕት ሺብሬ ደስአለኝ ግን አልፈዋል። ለማይዘልቅ ዓላማ፣ ለማይዘልቅ ግብ፣ ለማይዘልቅ ራዕይ። ትውልዱ በዚህ ይለካል። መገበሩ ያለትርፍ። ነገም ይኽው ነው። አሁንም ከተንበጫበጨ ዘመን ላይ እንገኛለን። መላቅጥ ውሎ ጉዞ የሌለው። የደላቸው ይኖራሉ። እነሱ ዕለታዊ ናቸው። ስለትናንት፣ ስለ ነገ ግድ የማይሰጣቸው። እንደ አገር እንደ ትውልድ ሲታሰብ ግን ትውልድ ተገብሮ ትውልድን ከግብርነት የሚያስቆም ሥርዓት ማፊ ነው። ማስተዋል ተሰዷል። ከትናንት እስከ ዛሬ ለአንድ ዕጣ ነፍሥ ሥም፣ ዝና ሲባል ትውልድ በራህብ አንጀቱ ይማገዳል። አስታዋሽ የለውም። ቤተሰብ አምጦ ይወልዳል፣ አምጦ ያሳድጋል እንደ አማጠ ያልፋል። ይህን መከራ ኃላፊነት ወስዶ መልክ ማስያዝ ይቻል ነበር ግን በሩ ተከርችሟል። ውድቀት ክብር ሆኖ ይፎከራል። ትውልድ ያለቀበት የዴሞክራሱ ጥማት ዛሬም ቀራንዮ ላይ ነው። ድቀት - ስብራት - ውርዴት እንደ ልዕልና ሲንጨበጨብለት መርኽ ተምሶ ሲቀበር ከማዬት በላይ የቁም ሙትነት የለም። እያለን የለለን፣ እዬፈሰስን ያለቀን። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

20.12.2019 የኦሩሙማ ፀረ አማራነት። የኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክነት።

  የኦሩሙማ ፀረ አማራነት። የኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክነት። ኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክ ነው። እርግጥ ነው ፀረ ሴሜቲክነቱ እንዳይጋለጥ በፀረ አማራነት ብቻ ላይ ያተኮረ ይመስላል። ውስጡ ግን ለቄስ ነው። ኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክ ነው። እውነቱ ይህው ነው። የኦሮሙማው ጠቅሚር አብይ አህመድ ድርብ፣ ንብርብር ተልዕኮ ነው ያላቸው። አረንዛዊ ጉዟቸው ብዙ ቅን ሰዎችን አፍዟል፣ አደንዝዟል ተከታይም አድርጓል። በብዙ ወገኖች ማዘንም የተገባ አይደለም። ሲገባቸው፣ ሲረዱት ወደ መርኽ እና ወደ ዕውነት ይመጣሉ። ይልቅ ወንዝ እያሳሳቀ እንዲሉ በዚህ የዝለት ጉዞ እንደ ቅኑ ዶር አንባቸው መኮነን አይነቱን ወገን ማጣት ግድ ይሆናል። አቅም የነበረው ሁሉ በአንድም በሌላም ዘነዘናውን ቀርቷል። ይህ የመጀመሪያው የጦርነት ዓውድማቸው ነበር፣ ተሳክቶላቸዋልም። የሚሊዮን ፍቅር ተንበርክከው ይዝቁ የነበሩትን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ሁሉ ወጥመድ ውስጥ ባላሰቡት አቅጣጫ እና ሁኔታ አስገብተው፣ ቦርቡረውም ሰርስረውም ዘነዘናቸውን አስቀርተውታል። አሁን እሳቸው ብቻ አማራጭ ተመላኪ ሆነው ጉብ ብለዋል። በሁሉም ዘርፍ፣ በሁሉም ሁኔታ መለመላውን ያልቀረ ተፅዕኖ ፈጣሪ የለም። ቢያንስ በጠላት እንዲተያይ አድርገውታል። ከሞት የሚተርፋ ካሉ እግዚአብሄርን ያመስግኑ። ጉዞው ገና አልተጀመረም። የባጁበት የመጀመሪያው ምንጠራ ላይ ነው። በሦስት እጥፍ ገና ይቀጥላል። ተበቅለውም አይረኩም። ምድማዱ መጥፋት አለበት። መልሶ እንዳይበቅል አድርገው ነው የሚነቅሉት። ቁዘማ ከበዛ "ማቅ አውልቀን ግምጃ እንልበስ " ቲያትር ገዝፎ ይወጣል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ዘርሽ ይምከን ሲላት እሳቸውን አበቀለባት። በቀላል ቀመር መተርጎም አይቻልም። መፀሐፈ ሄኖክ የደፈረው ቅኔ ነበር። መልካቸው እና ሰብዕናቸው ድርጊታቸው እና የአፈፃፀም ሂደቱን

LIVE 🔴ተጠያቂነት የሌለበት መንግሥት እና ሀገራዊ የፋይናንስ ቀውስ || ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ይናገራሉ #Ethi...

ምስል