ዕለተ - ትውልዱ 20.12.2019
ዕለተ - ትውልዱ።
በቅንጅት፣ በሰማያዊ ፓርቲ የተሰው። ሁለቱም ፓርቲዎች ሞተዋል። የህግ ባለሙያው ሰማዕት ሳሙኤል አወቀ እና እጩ ሊቅ ሰማዕት ሺብሬ ደስአለኝ ግን አልፈዋል።
ለማይዘልቅ ዓላማ፣ ለማይዘልቅ ግብ፣ ለማይዘልቅ ራዕይ። ትውልዱ በዚህ ይለካል። መገበሩ ያለትርፍ። ነገም ይኽው ነው።
እንደ አገር እንደ ትውልድ ሲታሰብ ግን ትውልድ ተገብሮ ትውልድን ከግብርነት የሚያስቆም ሥርዓት ማፊ ነው።
ማስተዋል ተሰዷል። ከትናንት እስከ ዛሬ ለአንድ ዕጣ ነፍሥ ሥም፣ ዝና ሲባል ትውልድ በራህብ አንጀቱ ይማገዳል። አስታዋሽ የለውም። ቤተሰብ አምጦ ይወልዳል፣ አምጦ ያሳድጋል እንደ አማጠ ያልፋል።
ይህን መከራ ኃላፊነት ወስዶ መልክ ማስያዝ ይቻል ነበር ግን በሩ ተከርችሟል። ውድቀት ክብር ሆኖ ይፎከራል። ትውልድ ያለቀበት የዴሞክራሱ ጥማት ዛሬም ቀራንዮ ላይ ነው።
ድቀት - ስብራት - ውርዴት እንደ ልዕልና ሲንጨበጨብለት መርኽ ተምሶ ሲቀበር ከማዬት በላይ የቁም ሙትነት የለም። እያለን የለለን፣ እዬፈሰስን ያለቀን። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ