ልጥፎች

ከጁላይ, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ገዳይ ሃሳብ በአካልም ይሁን በመንፈስ #በታኝ ነው።

  #ገዳይ ሃሳብ በአካልም ይሁን በመንፈስ #በታኝ ነው።   "እግዚአብሄር ቃየልን ወንድምህ አቤል ወዴት አለ አለው፤ ቃየልም በልቡ ትዕቢት የወንድሜ የአቤል ጠባቂ ነኝ አለ። አቤል ንጹሕ ሰውን ሆነ ቃየል ግን ደግ ሰው ወንድሙን አቤልን በመግደል ኃጢያተኛ ሆነ።" (መጸሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ም ፳፰ ቁ ፬ - ፭)   #ምዕራፍ ፲፱።   እንዴት አደራችሁ ማህበረ - ቅንነት።    እኔ አቶ ሽመልስ አብዲሳን ኢትዮጵያዊ #ጎልጉል እላቸዋለሁኝ። ግልጽ እና ቀጥተኛ ሃሳባቸውን ማጋራታቸው መልካም ነገር ነው። አይደለም በአገር ደረጃ በቤተሰብ እንኳን ይህን መሰል ግልጽ እና ቀጥተኝነት ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ትዕቢታዊ ሁነታቸው ግን ይጎፈንነኛል። መታበይ ወንዝ አያሻግርም፤ ሥልጣንንም አያጸናም።    4ሺ ኢትዮጵውያንን በጋራ አሰባስቦ ያለው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ረጅም ጊዜ የወሰደበትን ተልዕኮ ለመቋጨት ስምንት በኽረ አጀንዳወችን የያዘ የመወያያ አቅጣጫ አመልካች ሰነዱን ሰሞኑን አስተዋውቋል። የተሳታፊ ቁጥር እየጨመረ ስለመሆኑም እያደየጥኩ ነው። " ኑ በራችን ክፍት ሆኖ ይጠብቃችኋል" የሚል ዕድምታ እንዳለም አንብቤያለሁኝ።   የሆነ ሆኖ ከዚህ ጋር በተያያዘ ብልፄው እንደ ፓርቲ ለምክክር ኮሚሽኑ አቀረበ የተባለው ሰነድ ደግሞ በአቻነት ወጥቷል። ከውስጥ የተገኜ መረጃ ይሉታል ዘመነኛ ተጽዕኖ ፈጣሪወች ወይንም የዩቱብ ባለቤቶች።    እንደምን የሚስጢር በር ለእነሱ ቧ ብሎ እንደሚከፈት፤ ለሌሎቻችን ደግሞ ክርችምችም እንደሚል በይገባኝም። የክት እና የዘወትር፤ የቤት እና የእዳሪ ልጅነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ልሙድ ነው።   የኦሮምያ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አገራዊ ምክክሩን ተከትሎ፤...

#የ106 ደቂቃወች የምጥ ግልግል #በኒወርክ።

  #የ106 ደቂቃወች የምጥ ግልግል #በኒወርክ ።   "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱።)   #ምዕራፍ ፲፱።   #ጠብታ ። ክብረቶቼ የእኔ አዱኛወቼ፤ የአገሬ ልጆች የእቴጌ ድንቡልቡል የልብ ህሊናወች፤ የእግር ኳስ አፍቃሪወች፤ አትኩራታውያን ሁሉ ምሽቱ፤ አዳሩ፤ ረፋዳው እንዴት ይዟችኋል?    ስለ - ተፈጥሯዊነት፤ ስለ - ጥበብ፤ ስለ - ሰው ልጅ ሐሤት የአሰጣጥ ሥርዓትየሚመስጣችሁ ወገኖቼ፤ በማስተዋል የአርቱ ቤተኛ ለመሆን የመስጠት አቅም ያላችሁ ውዶቼ እግር ኳስ ለእኔ 13ኛው #ፕላኔት ነው። ተክለ - ሁነቱን እዩት ማዕድ ነው። ክብ ነው። እቅፍቅፍ ጥግትግት - ውህድህድ - ያለ የዓለም ማህበረሰብን የሚናፍቅ ሐዋርያ፤ ትንቢተኛም።   እግር ኳስ በፍቅር ተፈጥሮ የጰጰሰ፤ በተፈጥሯዊነት ነብይነትን የተጎናጸፈ ልዩ ስጦታ ነው። ግሎባላይዜሽን - ሲታሰብ፤ ደንበር አልቦሽ እኛዊነት ሲታሰብ፤ አብሮነት - ሲታጭ፤ ህብራዊነት - ሲታለም፤ ዕንባ - ሳቅ - ሲቃ - የጋብቻ አጋጣሚ፤ ቤተሰባዊነት፤ ማህበራዊነት፤ ታዳሚነት - አድማጭነት ሲታለሙ ፌክ ያልሆነ የውስጥ ለውስጥ አገናኝ ነው። ድልድይ ነው የላቀው የእግር ኳስ ቅኔዊ - ጥበቡ፤ ዘለግ ሲል ዊዝደሙ።   በኳስ ውስጥ መሰጠትን፤ ማተኮርን፤ ማስተዋልን፤ የጋራ እና የግል ኃላፊነትን፤ ፖስተኝነትን፤ ቅብዓን፤ ህግን፤ ጥሪን፤ የድንጋጌ አፈፃጸም ሂደትን፤ የትውልድ አገነባብ ሜቶሎጂን፤ ትውልዳዊ ድርሻን፤ ታሪክን - ትውፊትን - አደራን - ስልጣኔን - መኖርን - መታመንን - ሞራልን - ዲስፕሊንን - ድንበር አልቦሽነትን - እድገትን - ስኬትን - መደመጥን - ቅንነትን - ማግስ...

10 ጎል ከመረብ ጋር #የተጋባበት የደረጃ ጨዋታ።

  10 ጎል ከመረብ ጋር #የተጋባበት የደረጃ ጨዋታ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   የመጀመሪያው ግማሽ ጨዋታ በእንግሊዝ 4 ፈረንሳይ ምንም በሆነ ውጤት ፈረንሳዮች ምን ነካቸው የሚል የቤት ሥራ ለተመልካች #ሸልመው ግራ ቀኙ ተጫዋቾች ወደ እረፍት አመሩ።   ከእረፍት መልስ ፈረንሳዮች ተጠናክረው ገብተው ሦስት ጎል አስገቡ። እንግሊዞች #የቅጣት ምት አገኙ እና ከ4 ወደ 5 ከፍ አሉ። ፈረንሳዮች የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለው አንድ በመጨመር ወደ 4 አደጉ። ይህን ጊዜ ጨዋታው ሊራዘም ይችላል የሚል ተስፋ ቢጤም ነበር። ነገር ግን እንግሊዞች 1 አክለው 6 እንዳሉ ጨዋታው #ተጠናቀቀ ።   በደረጃ ጨዋታ ይህን ያህል ጎል በጣም ብዙ ነው። የእንግሊዞች በአርጀንቲና መሸነፍ፣ የፈረንሳይ ደረጃውን ስፔኖች መውሰድ #የመድከም ፣ #የመዛል ሊሆን ይችላል።   በዚህ ጨዋታ #ማፔ ሁለት ጎል አስገብቷል። ቢጠነክር ዛሬ ተጨማሪ ጎሎችንም መጨመር ይችል ነበር። #የወርቅ ጫማዋ ብትቀናው ምኞቴ ነው።   #የወርቅ ቀለበትም ተዘጋጅቷል አሉ። እኔ አይደለም ያልኩት። ቢቢሲ ነው። ነገ ለፍፃሜ አርጀንቲና እና ስፔን ይጋጠማሉ። የነገ ሰው ይበለን። አሜን። ጨዋታው በመደበኛ ጊዜ ነው የተጠናቀቀው። #ደክሟቸዋል #ይረፋ ። የእንግሊዞች የደረጃ ሽልማት እዬተሰጠ ነው። #ሦስተኛ ደረጃ ይዘው።   ጨዋታውን ይህ ዓይነት ነበር ለማለት አልቻልኩም። ደንብ እና ህግ ስለሆነ ብቻ የከወኑት ነው የሚመስለው። #የማይቀርበት ስለሆነ።   ሥርጉተ©ሥላሴ። Sergute©Selassie. 19/07/026

ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር #ህሊናው ሊሆን የሚገባው #ኦርጋኒክ ሰብዕና ያለው አቶ ኦባንግ ሜቶ ነበር።

  ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር #ህሊናው ሊሆን የሚገባው #ኦርጋኒክ ሰብዕና ያለው አቶ ኦባንግ ሜቶ ነበር።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፱።   ኦባንግሻ #ለፈላስፊት ኢትዮጵያ #ኦርጋኒክ ማንነት፣ #ልኩ ኦርጋኒክ ሰብዕናው የሚመጥን ነበር። ሁልጊዜ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት እነቃለሁ። እንደ ነቃሁ የሚያስቀጥል ሃሳብ አዕምሮዬ ካመነጨ ይህንኑ አዲስ ሃሳብ እያጠናሁ ይነጋል።   ዛሬ ሌሊት ኦባንግሻን አሰብኩት #ዘለግ አድርጌ። ሁልጊዜም አስብለታለሁኝ። ምክክሩ ከወደ ጋንቤላ አዲስ "ምክክር" የሚባል ቤቢ አግኝቷል። ስሙም " #ምክክር " ነው። ይደግልን። አሜን።    ከንቲባ ወሮ አዳነች አበቤ የአራስ ወጉን ሲያደርሱ አይቻለሁ። ይህ መልካም ነገር ነው። መልካም ነገርን የማነወር ሰብዕና የለኝም። እንዲለመልም መመኜት እንጂ።    ለነገሩ አንዷ አክስቴ #መልካም ሰው፣ ሌላዋ #ደግ ሰው ይሉኝ ነበር። ጸጥ ያልኩ፣ ያለኝን ሁሉ የምሰጥ የልጅነት ጊዜ ነበረኝ። አዲስ ለተገኜው የጋንቤላው ልዩ ህፃን የተደረገው እንክብካቤ #ማለፊያ ነው። የዓለምን የሚዲያ አውታር ያጨናነቀው የስፔኑ ያማል ታናሽ ወንድም ነው። ብርቅ ድንቅ ደጋፊነቱ ልዩ አትኩሮት ስቧል። ሁለቱንም ዓለም አደነቀ።   ልዩ የሰብአዊነት አቅም የኢትዮጵያ #አንከር አቶ ኦባንግ ሜቶስ? ለአዲሱ ቤቢ ክብር፣ እንክብካቤ ጥሩ ነገር ነው። የትናንቱ የኢትዮጵያ ባለውለታ መኖሩን እንኳን ለማወቅ አለመቻላችን ያሳስባል።   ኦባንግሻን የበላ ጅብ አልጮኽ አለ። አይደለም ኢትዮጵያ #አህጉራችን ሊወክል የሚችል #አብነታዊ ሰብዕና ያለው። አምኖ፣ አገሩ ገብቶ፣ ንጹህ #መታመን ከድቶት እንዲህ ዝግትግት ባለ መረጃ አልቦ...