ፈተና!
ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው የክብር የእራት ግብዣ ማግሥት ቀራንዮ! „ስለ ኃጢያትህ ንሰሃ መግባትን አትፍራ።“ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ይህን የምታይ እናት፤ ይህን የሚያዩ ልጆች፤ ይህን የሚመለከት የውጭ ዜጋ ዛሬ ምን ሊሰማው እንደሚችል መገመት ይከብዳል? መቼ ነው ከሃዘን የኢትዮጵያ እናቶች የሚወጡት? መቼ ነው ከዚህ እጅግ ከሰው በታች የሚያደርጉ ዘግናኝ አገዳደል እና ውርዴት የሚወጣው? እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለት ሁሉ እያሰፈረኝ ነው። የቄሮ ንጉሥ አቶ ጃዋር መሃመድ ለአሱ ንግሥና የተደረገ የቀረበ ገጸ በረከት ነው የሰው ደም ሊቀርበልት ስለሚገባ። የሚገረምው እና የሚደንቀው በተሰቀለው ወገኔ ዙሪያ ቀርበው የአገዳደሉን ትርኢት እዬተመለከቱ ፌሳታቸው የሆኑ ወገኖቼ ደግሞ መኖራቸው ነው። ፖሊስ የሚባል የለም ከአቅራቢያው? ምን ይባላል ይሄ የሰው አገር ወይንስ ምን ይባል? እንዴት ወገነህ እንዲህ ሆኖ ሲንጠለጠል አዬትህ ተኝተህ ታድራለህ? ምግቡስ ከጉሮሮ ይወርዳልን? የአቶ ጃዋር መሃመድ የመሪነት ደረጃ ይሄው ነው። መሪነት ማለት በዚህ እንዲህ በሆነ መልኩ ይገለጻል። ለዚህ ነው እንግዲህ በብሄራዊ ደረጃ „የቄሮ ምክር ቤት“ ለማቋቋም ጥናት ላይ መሆኑ የተደመጠው። ተረኞቹ ታራጆች ደግሞ ጠብቁ … ለዚህ አረመኔነት ነው እንግዲህ ከአዲስ አባባ እስከ ባህርዳር ድረስ ሚዲያዎችም፤ ባለስልጣኖችም ሥራ አጥተው ከፍ እና ዝቅ ሲሉ የባጁት፤ ለነገሩ ይህ መጀመሪያው ነው። ገና የሚፈነዳ ሌላም ነገር ይኖራል። ከዚህ ሌላ ደግሞ ምን ሌላ ልትሉ ትሉኝም ይሆናል፤ ጭካኔ እኮ ሰው መሆን ማለት አይደለም። ሰው ...