ፈተና!
ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው የክብር የእራት ግብዣ ማግሥት ቀራንዮ!
„ስለ ኃጢያትህ ንሰሃ መግባትን አትፍራ።“
ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭
ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
ይህን የምታይ እናት፤ ይህን የሚያዩ ልጆች፤ ይህን የሚመለከት የውጭ ዜጋ ዛሬ ምን ሊሰማው እንደሚችል መገመት ይከብዳል?
መቼ ነው ከሃዘን የኢትዮጵያ እናቶች የሚወጡት? መቼ ነው ከዚህ እጅግ ከሰው በታች የሚያደርጉ ዘግናኝ አገዳደል እና ውርዴት የሚወጣው? እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለት ሁሉ እያሰፈረኝ ነው።
የቄሮ ንጉሥ አቶ ጃዋር መሃመድ ለአሱ ንግሥና የተደረገ የቀረበ ገጸ በረከት ነው የሰው ደም ሊቀርበልት ስለሚገባ። የሚገረምው እና የሚደንቀው በተሰቀለው ወገኔ ዙሪያ ቀርበው የአገዳደሉን ትርኢት እዬተመለከቱ ፌሳታቸው የሆኑ ወገኖቼ ደግሞ መኖራቸው ነው።
ፖሊስ የሚባል የለም ከአቅራቢያው?
ምን ይባላል ይሄ የሰው አገር ወይንስ ምን ይባል? እንዴት ወገነህ እንዲህ ሆኖ ሲንጠለጠል አዬትህ ተኝተህ ታድራለህ? ምግቡስ ከጉሮሮ ይወርዳልን? የአቶ ጃዋር መሃመድ የመሪነት ደረጃ ይሄው ነው።
መሪነት ማለት በዚህ እንዲህ በሆነ መልኩ ይገለጻል። ለዚህ ነው እንግዲህ በብሄራዊ ደረጃ „የቄሮ ምክር ቤት“ ለማቋቋም ጥናት ላይ መሆኑ የተደመጠው። ተረኞቹ ታራጆች ደግሞ ጠብቁ …
ለዚህ አረመኔነት ነው እንግዲህ ከአዲስ አባባ እስከ ባህርዳር ድረስ ሚዲያዎችም፤ ባለስልጣኖችም ሥራ አጥተው ከፍ እና ዝቅ ሲሉ የባጁት፤ ለነገሩ ይህ መጀመሪያው ነው።
ገና የሚፈነዳ ሌላም ነገር ይኖራል። ከዚህ ሌላ ደግሞ ምን ሌላ ልትሉ ትሉኝም ይሆናል፤ ጭካኔ እኮ ሰው መሆን ማለት አይደለም። ሰው ከሰውነት ደረጃ ሲወጣ ነው ጨካኝ የሚሆነው።
አረመኔ ከሆነ ሰው ከወገብ በላይ ህሊናው ወደ አውሬነት ተቀይሯል ማለት ነው። ከግድያ በሆወላ ሊያቀጥሉት፤ ሊቆራርጡት የማይችሉበት በአደባባይ ምን አለና?
ወጣቶቹ የተቀረጹት እኮ እንዲህ እንዲሆን ነው አይደል?
ፈንጅ ይዞ እንኳን ቢገኝ በዚህ መልክ እንዴት የሰው ልጅ ተገድሎ ይንጠለጠላል? ህግ ባለበት አገር? የአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ባለበት ሀገር። ለዚህ ነው ምዕራባውያን አገር የመምራት አቅም የላችሁም የሚል ሃሳብ አላቸው የተባለው።
ከዚህም ባሻገር ኢንቬሰተሮችም ኦሮምያ ከሆነ አንችልም የሚል ነገር እንዳለም በተለያዩ ከተሞች በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሲገልጽ አዳምጫለሁኝ።
እንዴት ሰውን ሰው እንዴት ይፈራዋል? መፈራት በጭካኔ አምሳል በአውዳሚነት አንጻር ከሆነ ሥጋዬ የተቆረሰ ያህል ይሰማኛል። አፍራለሁኝ ለዚህ። ይህ ውርዴት የሁላችንም ነው እንደ ዜጋ።
እንግዲህ እነ ዶር ለማ መገርሳ ባሉበት አገር ነው የሄ የሆነው? እነ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በሚያስተዳደሩት ግዛት ይሄ እጅግ ለህሊና የሚከብድ ጭካኔ የተከናወነው።
እንደ ሴት፤ እንደ እናት፤ እንደ እህት፤ እንደ አገር ይህ ምን መልዕክት ይልካል? ይህን መሰል አውሬነት ለመፍጠር ነበር በተከታታይ አመታት በፌስ ቡክ የተሠራበት።
ይህን የአውሬነት ሥነ - ልቦና በምን ቀመር እና ጥረት ሊወገድ ይችላል? ይሄ ነው የንጉሥ ጆዋር መሃመድ የፖለቲካ ፍልስፍና። በዚህ መልክ ነው ወጣቶቹ በማህበራዊ ሚዲያ የሰለጠኑት።
በእነሱ ምን ይፈረዳል፤ ሰው መግደል ገድሎ ደስታ ማግኘት እዬተማሩ አላደጉም። እኛ የቤት ሥራችን አልሰራነም። ስለዚህ በእነሱ እንዴት ይፈረዳል? ወጣትነት ፈተና ነው።
ይህን ያደረገው ልክ ያጣው፤ ያበጠው፤ መጠን የለሹ በመካሄድ ላይ ያለው ገማና ነው።
ይህ አሰቃቂ ይህ አሳፋሪ ድርጊት በኦሮምያ ክልል ነው የተከናወነው፤ ምክትል ፕሬዚዳንቷም አንስት ናቸው? ኦሮምያ እንግዲህ ሴቶች ወደ ሥልጣን ሲመጡ ይህን ነገር ያስቀራሉ የሚል ሃሳብ ነበረኝ።
በዚህ በሰብዐዊነት ላይ ተግተው ይሰራሉ ብዬ አስብ ነበር። እጅግ ይዘግንናል እራሱ ከዛ ወንበር ለመቀመጥም እጅግ ይሰቀጥጣል፤ ሚዲያ ላይ ቀርቦም ውስጥን ለመናገር ለሴት ባለሥልጣንት እጅግ መርግ ነው።
ሴቶች ወደ ስልጣን ሲመጡ ሆነ በማናቸውም ጉዳይ ፊት ለፊት የመሆን ዕድሉ ከኖራቸው መጀመር የሚገባቸው ከዚህ መሰሉ ሰብዐዊነት ተግባር ላይ መሆን ነበረበት ነገር ግን የሚታዬው ከስብዕ ህሊና ውጪ የሆነ ነገር ነው።
ይህ ድርጊት በ21ኛው ምዕተ ዓመት በዚህ መልኩ መታየቱ ኦሮምያ ላይ ህሊና ላይ ሊሰሩ የሚጋባቸው ነገሮች አለመጀመራቸውን ያመልክታሉ። ሚደያ ላይ በሸበረቀ ወንበር እና ሶፋ ላይ መግለጫ መስጠት ሳይሆን ሰውን ሰው አድርጎ መቅረጽ ነው ሊቀድም የሚገባው።
አውሬ አድርገህ የቀረጸክውን ሰብዕና በአዋጅ በአፍታ እፍ ብለህ ልታበነው አይቻልመ። በዚህ በትጋት እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ሰርተውበታል ጭካኔን ነው ሲያስተማሩ የኖሩት። „ሰው የዘራውን ያጭዳል“ እንዲሉ ነው የሆነው ሁሉ። ብቻ ሰሞናቱ ብዙ ነገሮችን በአደብ እንድንመረምር ሌላ የትምህርት ምዕራፍ ከፍቶልናል።
ገራሚወ ነገር የጭካኔን አባወራ መንፈስን አንግሱልን ነው የሚባለው ጫነው፤ ይህም ደግሞ ሊመረመር ይገባል። አቶ ጀዋር መሃመድ በነገሰ፤ ዘውድ በደፋ በማግሥቱ ወታደሮቹ ይህን ሰርተዋል። መሪነት ይህን በመሰለ ኢ-ሰባዊነትም ይገለፃል።
ይህ በዚህ ይቆማል ተብሎ አይታሰብም። ተልዕኮው እና ሂደቱ ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን የተሸከመ ነው። ብዙ ትብትብ ጉዳዮችን ተጠቃለው እና ተማክለው ያዘለ ነው። ኦህዴድ እኔ በሰብዕና ጉዳዮች ላይ ለአብነት የበቃበት ዘመን ላይ ነው ብዬ አስብ ነበር።
ግን ያ አደቡ እና አቅሙን ምን ብን አድርጎ ወሰደበት?ተደገመበትን ወይንስ ምኑ አዚም አረፈበት? ወይንስ እኛ ሰህተት ውስጥ ነበርን ይሆን? የማዬው ሁሉ ነገር ያ እምነት የጣልኩበት ለአገራዊ አደራ ብቁ ነው ያልኩት የመሠከርኩለት ስንትም መከራ እና ወጀብ የታገስኩለት አልመስለኝ እያለ ነው …
ብቻ ፈቃደ እግዚአብሄር እኛ አንድንማርበት የፈለገበት ዋና መሰረታዊ ጉዳይ እንዳለ እያሰተዋልኩኝ ነው። መቼም ሃይላችን አቅማችን ጸሎት ነው እና በዚህው መጽናት ይገባል። በተረፈ መንግሥተ ጃዋር መሃመድን ያጽናልን ወይንስ ይናድለን? የኔዎቹ የተመቻችሁን ውሰዱ እንደ ምርጫችሁ ... የልብ ስብራቱ በዬቀኑ ሆነ ...
ሰው መሆን ሰው ሆኖ መፈጠር ማለት አይደለም!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
እንጸልይ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ