ልጥፎች

ከኖቬምበር 2, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለመሆኑ አማራ እንደ ኢትዮጵያዊ ሙሉ ዜጋ ይታያልን?

ምስል
ዕውቅና ያልተሰጠው ችግር መፍትሄ ያገኛል  ብዬ አላስብም። „አቤቱ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፤ ችግረኛና ምስኪን ነኝና።“ መዝሙረ ዳዊት ፹፭ ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ ለመሆኑ አማራ እንደ ኢትዮጵያዊ ሙሉ ዜጋ ይታያልን?  ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ·        መነሻ። በመጀመሪያ ነገር በአማራ ፍልስፍና ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እምነቱም ፍላጎቱም የላቸውም። አማራ የሚለው መጠሪያ መስማትም አይፈልጉትም። ይህን ባህርዳር ላይ በቅኔ ተናግረውታል። እኛ አጠቃላዩን ስለምናይ ብቻ ነው ውስጣችን፤ ፍቅራችን፤ አክብሮታችን የምንሰጣቸው እንጂ በነገረ አማራ ያላቸው አቋም እጅግ ከረር ያለ ስለመሆኑ በተለያዬ ጊዜ በሚያደርጉት ንግግር ይገልጡታል። የሚገርመው በቀደመው ጊዜ እንዲያውም ተቆርቋሪነታቸው አመዝኖ ነበር የማዳምጣቸው። እጅግም የሚያሳሳ አቅም ነበራቸው። በአዲሱ ማንነታቸው ውስጥ ግን ልዩ ተልዕኮ የተሰጣቸው ያህል ፊት ሲነሱት ነው እኔ የምመለከታቸው።  ከውስጤ አላዝንም። ይህም ለበጎ ስለመሆኑ ስለማምንበት። አንድ ቀን እንደሚጸጽታቸውም ልብ ልክ ነው። የመጀመሪያ 6 ወር ሥራቸው ላይ በጫን ተደል የቤት ሥራ ክልሉን ሲያጣድፉት ነበር የባጁት። መተንፈሻ እስኪታጣ ድረስ። ሌላ ቦታ የማይሞክሩትን ሁሉ የለማ አብይ አካቢኔ የመሞከሪያ ጣቢያው ለሁሉም ነገር አማራ ክልል ላይ ብቻ ነበር። ይህም ሆኖ እንደ ሰውም አይተው ዕንባውን ለማድመጥ መፍቀድም የአባት። እኔ እንደማስበው እራሱ አዴፓ የሚበላውን ድርጅት ሥሙ ራሱ አሁን ከሆነ የሚመቻቸው አይመስለኝም። እነሱ እራሳቸው ከዞግ ድርጅት ወጥተው ያን ያህል የተንጠራሩ የኦሮሞ ሊሂቃንን ተሸከመው፤ እያባበሉ፤...