ልጥፎች

ከዲሴምበር 23, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ነፍስ ይማር ሁላችንም ጠበቂዎች ነን ... መሰሉን ...

ምስል
ዴሞክራሲን ሊኖሩት የፈቀዱት ብቻ ብፁዕን ናቸው። „እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው? ነገርንስ መተርጎም የሚያውቅ ማን ነው?“ መጽሐፈ መክብብ ፰ ቁጥር፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute© Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ለሌላው የተፈቀደ የተስፋ ዘመን ለሌላው ደግሞ የተቀፈደደ የጨለማ ዘመን ነው። አንዱ ያገኘው ያገኘውን ንጹህ አየር ሌላው ሲያገኝ ይቀናበታል። አዬሩን ሰጪ እኮ የነፃነት አዳዩ እኮ እሱ አይደለም። አለመታደል። ዛሬ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች የናፈቃቻቸውን አገራቸው እና ህዝባቸውን ማግኘት እኩል መብት ሆኖ ሳለ ግን ገደብ መጣል ወንጀል ነው። ጥፋት ከኖረም ካለም ቁጭ ብሎ መነጋገር ይቻል ነበር። እንዲህ ከሚሆን?   ·        ው ዶቼ እንዴት ናችሁ ይህን ስጽፍ ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተስፋ እያለቀስኩኝ ነው … የአላዛሯ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ህልም ፈተና የጣለ አዲስ ክስተት ትንሽ ቀደም ባሉ ሰዓታት አነብኵኝ። ማመን ለመቻል ራሴን ከሁኔታው ጋራ ለማዋህድ ጊዜ አስፈለገኝ እና አንድ ሦስት ሰዓት ዘገዬሁኝ። ኢትዮ ሪጅስተር አልከፍትልኝ ካለ ሁለት ሳምንት አልፎታል። ለማረጋገጥ ፈልጌ አልቻልኩኝም። ዘሃበሻን ሰንበት እንዴት ይዟሃል ልል ስገባ፤ ሻማ የበራበት ፎቶ አዬሁኝ። ጹሑፍ እንዲሁ፤ ሥሙን እና ፎቶው አልመጣልሽ አለኝ። እኔ በአካልም በፎቶም አላውቀውም። እማውቀው ብራና ላይ  የብዕሩን ጠብታ ብቻ ነው። እርግጥ ነው እሱም እኔን ያውቃል በዜና፤ እኔም አሱን በዜና አውቀዋለሁኝ። እንድ - ደወልልት ስልክ ተሰጥቶኝ ትደውልልኝ ብሎ አልደወልኩለትም በ2013/2014  ይመስለኛል። እኔ በመደወል፤ በመተዋወቅ ዝንቅ ዝንቅ በማለት ባህል እጅግ ደካማ ነኝ ከምል አልተፈጠርኩበትም። ሰው ደውሎም ራሱ አላነሳም

ውስጥን ለማሳዬት ፍርሃቱ እስከ መቼ?

ምስል
ውስጥን ለማሳዬት ፍርሃቱ እስከ መቼ? "እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው?  ነገርንስ መተርጎም የሚያውቅ ማን ነው?" መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፰፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  23.12.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                           ዛሬ -አላዛሯ ኢትዮጵያ አድማጭ ሙሴ አላት! መነሻ! https://www.youtube.com/watch?v=nWpGmEUIDNc ዋልታ ቲቪ 13/04/2011 ዓ . ም የማታ 1 ፡ 30 ዜና በቀጥታ | Walta TV News Live 7:30 PM 12/22/2018 ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ። ደህና ናችሁ ወይ? አሁን አንድ ዜና አዳመጥኩኝ ከዋልታ ቴሌቪዥን። የሚገርመው አገር ውስጥ የነበሩ ተፎካካሪ / ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች ከሁለት ዓመት በፊት የኦሮሞ እና የአማራ ህዝባዊ ተጋድሎ ሲነሳ ያን ለማርገብ እና ትጥቅ ለማስፈታት እነ ሳጅን በረከት ያሰናዱት አንድ የበረዶ ግግር ጋር ታዳሚ ነበሩ።  ያ ቁም ነገር ሆኖ አብረው የቡና ማህበር መስርተው እንደ ልዝ እንጨት ወይን አይነዱ ወይ አያናዱ ህዝባዊ ተጋድሎውን አቅጣጫ ለውጦ በተኛ ፖለቲካ አስተሳሰብ ልፍስፍስ ብሎ እንዲቀር ሰፊ ድርሻ አበርከተዋል። ተዉ እያልናቸው። ያን ጊዜም እኔ ወጥቼ ሞግቻለሁኝ። መልካም ጅምር ነው ሊበረታታ ይገባዋል ካሉት ወገኖቼ ጋር። ያ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ እና የኦሮሞ ንቅናቄ መሪ የፖለቲካ ድርጅት አለመኖሩን የተረዳው በሁለቱ ክልሎች የተነሳው አብዮታዊ ሞገድ በአንቦ፤ በጎንደር እና በጎጃም የነበረው ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ተጋድሎ በፖለቲካ ድርጅቶች ማንፌሰቶ ውስጥ ያለነበሩ፤ በህዝቡ ማህበራዊ ንቃተ